Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 13 የቴክኖሎጂ ዘርፎችን አካቶ ሊካሄድ ነው

የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 13 የቴክኖሎጂ ዘርፎችን አካቶ ሊካሄድ ነው

ቀን:

አሥራ ሦስት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎችን ያካተተ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ከጳጉሜን 2 እስከ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ሊካሄድ ነው፡፡

ኤክስፖው ጆርካ ኤቨንትስ ኦርናይዜሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑን፣ ነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ሁለቱ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል፡፡

የቴሌኮም፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂ ክፍያ አማራጮች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ዘርፎች፣ ሶፍትዌር የሚያበለፅጉ ኩባንያዎች፣ ሶላር፣ የሳይበር ደኅንነት፣ ባዮቴክኖሊጂን ጨምሮ አሥራ ሦስት ዘርፎች ላይ ያተኮረ ኤክስፖ መሆኑን የጆርካ ኤቨንት የኮሙዩኒኬሽንና ማርኬቲንግ ኃላፊ አቶ ሳምሶን ኃይለ ኢየሱስ ተናግረዋል፡፡

በኤክስፖው ዓለም አቀፍና ዘመኑ ያፈራቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚተዋወቁበት ሲሆን፣ ከአፍሪካ፣ ከእስያና ከሰሜን አሜሪካ አንጋፋ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ኤክስፖው ምርትና አገልግሎቶችን ከማስተዋወቅ በተጨማሪም፣ በቴክኖሎጂ አፍሪካና ሌላውን የንግድ ዓለም ለማስተዋወቅና ትስስር ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ኤክስፖ በኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎቶች፣ ባለሀብቶች፣ ፖሊሲ አውጪዎችና የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት መድረክ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

አቶ ሳምሶን እንደተናገሩት፣ በኤክስፖው ከ500 በላይ ከአፍሪካ፣ ከእስና ከሰሜን አሜሪካ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዘው የሚሳተፉ ነው፡፡

ከ45,000 በላይ ጎብኚዎችና ገዥዎች ኤክስፖውን ይጎበኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ትስስርን ዕውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው፣ ኤክስፖው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ትስስር ለመፍጠር የሚያግዝና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን የሚያጠናክር መሆኑን፣ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በኢትዮጵያ መካሄድ የአገር ገጽታ ግንባታን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን፣ ለአገር ሰላምና ፀጥታ መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ለኢኮኖሚ ልማት፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድና መሰል ሥራዎች የቴክኖሎጂ ኤክስፖው ትልቅ ድርሻ እንዳለው አስረድተዋል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...