Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከፍተኛው ፍርድ ቤትና የከተማ አስተዳደሩ በሚወዛገቡበት ይዞታ ላይ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

ከፍተኛው ፍርድ ቤትና የከተማ አስተዳደሩ በሚወዛገቡበት ይዞታ ላይ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

ቀን:

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣንና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር እየተወዛገቡበት ያለው መሬት (ይዞታ) ጉዳይ ላይ ጥናት አድርገው የውሳኔ ሐሳብ አቀረቡ፡፡

ሁለቱ ተቋማት በጋራ የባለሙያዎች ኮሚቴ አዋቅረው ባደረጉት ጥናት፣ ፍርድ ቤቱንና የከተማ አስተዳደሩን የሚያወዛግበው በልደታ ክፍለ ከተማ ተክለ ሃይማኖት አካባቢ የሚገኘው መሬት፣ የሁለቱንም አካላት የግንባታ ፍላጎት ማስተናገድ እንደሚችል ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል፡፡ ለዚህም የቦታ ሽግሽግና የዲዛይን ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ አጥኚዎቹ ጠቁመዋል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች በዚህ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በቅርቡ ተወያይተው አቋም እንደሚይዙ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ተናኜ ጥላሁን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የፍርድ ቤቱ አመራሮች ፍርድ ቤቱ ለግንባታ ያሰበው ቦታ ጉዳይ ላይ የሚወያዩ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን በ2011 ዓ.ም. የተቀበለው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ ከሦስት ወራት በፊት ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ መክኖበታል፡፡ ካርታውን አምክኖ የሊዝ ውሉን ያቋረጠው የልደታ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት፣ ለፍርድ ቤቱ የተሰጠው 2.1 ሔክታር መሬት ‹‹አጥር ከማጠር ባለፈ ቦታው አሁንም ባዶ›› መሆኑን በምክንያትነት ጠቅሷል፡፡

ፍርድ ቤቱ 2.1 ሔክታር መሬቱን ከተቀበለ በኋላ ግንባታ ሳይጀምር የቆየው በጀት ባለመፈቀዱ ሲሆን፣ በ2015 ዓ.ም. በጀት ግን ለሕንፃው ግንባታ 885 ሚሊዮን ብር ፀድቆለታል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰፊ መሬት ተሰጥቶ ዝግጅት ካጠናቀቀ በኋላ መሬቱን እንደነጠቀ ያስታወሱት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በባለሙያ ማስጠናቱን ነሐሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በተካሄደው የፌዴራል ዳኝነት ዓመታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ይህንን መሬት የፈለገው በከተማዋ በ38 ቢሮዎችን በአንድነት የሚይዝ ዲስትሪክትና ሕንፃዎች ለመገንባት ለያዘው ፕሮጀክት ነው፡፡

ጥናቱን ካካሄዱት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ኢንጂነር)፣ ጥናቱ ሲጀመር ሁለት አማራጮች ቀርበው እንደነበር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ሊገነባ ያሰባቸው ሕንፃዎች ከፍርድ ቤቱ ሕንፃ አንፃር በከፍታ የሚበልጡ መሆኑን መስፍን (ኢንጂነር) አስረድተዋል፡፡ አንደኛው አማራጭ የነበረው የፍርድ ቤቱ ፕሮጀክት ባለበት ሆኖ የከተማ አስተዳደሩ የሚገነባቸውን የተለያዩ ረዥም ሕንፃዎች በድልድይ ማገናኘት እንደነበር አስታውቀዋል፡፡ ይህም ከፍተኛ ፍርድ ቤቱን በሁለት ሕንፃዎች መሀል ያለ አነስተኛ ሕንፃ ያደርገዋል፡፡

ይኼ አማራጭ በፍርድ ቤቱ ለሥራው የሚያስፈልገውን ፕራይቬሲ የማይሰጥ ነው፣ የሕንፃው ገጽታም ጥሩ አይሆንም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህ አማራጭ ተቀባይነት አለማግኘቱን ገልጸዋል፡፡

ሁለተኛው አማራጭ ፍርድ ቤቱ ከግንባታ ሳይቱ ሳይወጣ ነግር ግን አሁን ካለበት ቦታ ሽግሽግ እንዲያደርግ የሚመክር ሲሆን፣ በውሳኔ ሐሳብነት የቀረበውም ይህ አማራጭ ነው፡፡

እንደ መስፍን (ኢንጂነር) ገለጻ፣ ፍርድ ቤቱ መጀመርያ ይዞት የነበረው ቦታ ዝቅ ያለ በመሆኑ ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ የዲዛይን ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ‹‹የከተማ አስተዳደሩ ደግሞ ለዲዛይኑ ማሻሻያ የሚያስፈልገውን ወጪ እሸፍናለሁ ብሏል፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሁን ያለበትንና ልደታ አካባቢ የሚገኘውን ከ50 ዓመት በፊት የተገነባ ሕንፃ ለመተካት ተክለ ሃይማኖት አካባቢ በሚገኘው መሬት ላይ ባለ ዘጠኝ ወለል፣ እንዲሁም ከምድር በታች ሦስት ወለሎች ያሉት ሕንፃ ለመገንባት ዲዛይን አሠርቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ያቀደው የሕንፃ ግንባታ ለማጠናቀቅ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽ አማካይነት የተዘጋጀው የዲዛይን ሥራ የተጠናቀቀው በ2013 ዓ.ም. ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ የዲዛይን ሥራን ለማጠናቀቅና የተሰጠውን ቦታ ለማጠር አሥር ሚሊዮን ብር ገደማ ወጪ አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ደቦ ቱንካ (ኢንጂነር)፣ ሁለቱ ተቋማት አጥንተው ያቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ በሰነድ ደረጃ እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል፡፡

‹‹መልሱን እየጠበቅን ነው፣ ሁለቱንም የሚያቻችልና ጥሩ ይሆናል ብለን እንጠብቃለን፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...