Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለስፖርት ማኅበራት ማስጠንቀቂያ ሰጠ

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለስፖርት ማኅበራት ማስጠንቀቂያ ሰጠ

ቀን:

አለመግባባቶች በመመርያው መሠረት መፍትሔ ሊያገኙ ይገባል ብሏል

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ተመዝግበውና ሕጋዊ ዕውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የስፖርት ማኅበራት፣ እንደየስፖርቱ ዓይነትና ባህሪ እንዲዋቀሩ ሲደረግ፣ በዋናነት ስፖርቱን እንዲያስፋፉና እንዲያሳድጉ መሆኑን በመግለጽ፣ ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚነሱ አለመግባባቶችና ውዝግቦች በመመርያው መሠረት መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ ጠቁሞ፣ አላስፈላጊ ችግር እየፈጠሩ የሚወዛገቡ ማኅበራትን አስጠነቀቀ፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፣ በአገር አቀፍ የስፖርት ማኅበራት ከአመራሮች ምርጫ ጋር በተገናኘ እየተደመጡ በሚገኙ ችግሮች ዙሪያ ማብራያ ሰጥቷል፡፡

‹‹አገር አቀፍ የስፖርት ማኅበራት ተመዝግበውና ዕውቅና አግኝተው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል ሲባል፣ ስፖርቱን እንዲያስፋፉና እንዲያሳድጉ እንጂ፣ የአመራሮች ምርጫና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አጀንዳ እያዘጋጁ ውዝግብ ለመፍጠር አይደለም፤›› ያለው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ የስፖርት አስተዳደሩ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያ በሆነ አግባብ የሚመራበት ወጥ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀፅ 37 1/ነ/ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ አገር አቀፍ የስፖርት ማኅበራት ስለሚቋቋበት ሁኔታ ለመወሰን ቁጥር 50/2014 መመርያ ተሻሽሎ ወጥቷል፡፡

የተሻሻለው መመርያ ዓለም አቀፍ የስፖርት ሕግና የአገሪቱን ሕጎች ባከበረ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን የስታወሰው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ መመርያው ከመውጣቱ በፊት የስፖርት ባለድርሻ አካላት መክረውበት፣ ግብዓት ሰጥተው ሥራ ላይ እንዲውል የተደረገ በመሆኑ፣ በተለይ ከአመራር ምርጫ ጋር ተያይዞ አላስፈላጊ ችግር እየፈጠሩ የሚወዛገቡ ማኅበራት ልብ ሊሉት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

የስፖርት ማኅበራት የአመራሮች ምርጫ የሚከናወነው፣ ማኅበራቱ ተስማምተው የተቀበሉት መመርያን መነሻ አድርገው ሊሆን እንደሚገባ ያሳሰበው ሚኒስቴሩ፣ ‹‹ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ባላቸው የውስጥ መመርያና ደንቦችን በማዘጋጀት በጉባዔያቸው ባጸደቁት ደንብ የሚመሩ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ መሆኑ እየታወቀ በአንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ፕሮግራሞች ‹‹ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አዋጅን በመመርያ አገደ›› የሚለው ከእውነታ የራቀ መሆኑን በድጋሚ ሊያውቁት ይገባል፤›› በማለት ነው ጉዳዩን ያብራራው፡፡

ይሁንና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ጋር በተያያዘ እንደ ችግር እየተጠቀሱ የሚገኙትን፣ የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴና የምርጫ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ምርጫው ተዓማኒና ገለልተኛ ይሆን ዘንድ የኮሚቴ አባላቱ ከምርጫ መመርያው ይዘት በመነሳት፤ ‹‹ገለልተኛ ናቸው፣ አይደሉም›› በሚለው ላይ ግን ምንም ያለው ነገር የለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...