Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአማራ ክልል የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል ፈጣን ምላሽ የሚያገኘው ሰላም ከተፈጠረ ብቻ መሆኑ...

በአማራ ክልል የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል ፈጣን ምላሽ የሚያገኘው ሰላም ከተፈጠረ ብቻ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

ከአላማጣና ተከዜ የኃይል ማሠራጫ ጣቢያዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኙ የነበሩት የሰሜን ወሎ፣ ዋግህምራ፣ ወልቃይት፣ ሁመራ፣ ባዕከርና ዳንሻ አካባቢዎች፣ ከሕወሓት ጋር ሰለም ካልተፈጠረ በስተቀር፣ ከሌላ መስመር ጋር ለማገናኘት ቢያንስ ስድስት ወራት እንደሚወስድ ተገለጸ፡፡

በሐምሌ 2013 ዓ.ም. የሕወሓት ታጣቂዎች ወደ አማራና አፋር ክልል መግባታቸውን ተከትሎ፣ የኃይል አቅርቦት መነሻዎቻቸው በሕወሓት ቁጥጥር ሥራ ካሉ አካባቢዎች ያገኙ የነበሩት በርካታ ቦታዎች፣ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ ሆነው ከዓመት በላይ መዝለቃቸው ይታወሳል፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ለረዥም ጊዜ የተቋረጠባቸውን የተወሰኑ አካባቢዎች ችግር ለመቅረፍ ከሕወሓት ጋር ያለው ግንኙነት ካልተስተካከለ፣ በወልዲያ ከተማ እየተገነባ ያለው የሰብስቴሽን ግንባታ ተጠናቆ ኃይል ለማቅረብ ቢያንስ ስድስት ወራትን እንደሚጠይቅ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኰንን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ይህ በወልዲያ እየተገነባ ያለውና ከዓላማጣ የሚመጣውን መሰመር ይተካል የተባለለት የ66 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ፣ አሁን ባላው ሁኔታ በአጭሩ ተገንብቶ ካላለቀ ሌላ አማራጭ እንደሌለ  አቶ ሞገስ አክለው ገልጸዋል፡፡

የማሰራጫ ጣቢያዎቹ በቁጥጥር ሥር ከመሆናቸው ባለፈ፣ በዋግኸምራና ሰሜን ወሎ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ያገኙበት የነበረው ሰብስቴሽ በሕወሓት ታጣቂዎች ተነቅሎ መወሰዱን ኮርፖሬሽኑ ተናግሯል፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ በሰሜኑ ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውን የወልቃይትና ሴቲት ሁመራ ዞን አካባቢዎች ይሸፍናል የተባለውና ከጎንደር-ዳንሻ፣ ባዕከር እስከ ሁመራ እንደሚገነባ ታስቦ የነበረው የ132 ሺሕ ኪሎ ቮልት ተሻካሚ መስመር፣ እንደታሰበለት መሄድ እንዳልቻለ፣ ሪፖርተር ከወራት በፊት መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በሰሜን ወሎና ዋግህምራ አካበቢ የሚኖሩ ዜጎች የመሠረተ ልማት ጥያቄ እንዲመለስላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርቡ ይደመጣል፡፡

ለአብነት ያህል ለ13 ወራት ያክል ያለመብራት እንደቆዩ በመግለጽ ‹‹ይህን ያክል በጨለማ ስንቆይ መንግሥት ያለ ሁሉ አይመስለንም፣ ዛሬ ነገ ይመጣል እያልን ጊዜ እየቆጠርን በተስፋ እየኖርን ነው፤›› በማለት ለሪፖርተር የተናገሩት መኰንን ጌታቸው የተባሉ የራያ ቆቦ ነዋሪ ናቸው፡፡

ኮሚቴ በማቋቋም ችግሩን ለሚመለከተው አካል አቅርበው መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ የሚናገሩት አቶ መኰንን፣ መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ መመለስ ካልቻለ እንዴት አስተዳድረዋለሁ ብሎ ይናገራል ሲሉ ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ኤሌክትሪክ ከመጥፋቱ ባሻገር በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት አለመኖሩና እየቀረበ ያለውም ነዳጅ ውድ በመሆኑ፣ የኑሮ ሁኔታቸው የተምታታና የተጎሳቆለ እንደሆነ አክለው አብራርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...