Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበራያ ቆቦ የቁም እንስሳትን የሚያጠቃው አባ ሰንጋ በሽታ ምልክት እየታየ መሆኑ ተጠቆመ

በራያ ቆቦ የቁም እንስሳትን የሚያጠቃው አባ ሰንጋ በሽታ ምልክት እየታየ መሆኑ ተጠቆመ

ቀን:

በአማራ ክልል በራያ ቆቦ የአባ ሰንጋ በሽታ ምልክት እየታየ በመሆኑ ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን፣ የራያ ቆቦ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የራያ ቆቦ እንስሳት ጤና ቡድን መሪ አቶ ተስፋው ምሥራቅ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አማራ ክልልን የሚያዋስኑ ድንበር አካባቢዎች የአባ ሰንጋ በሽታ በመከሰቱ በርካታ የቁም እንስሳት (ከብቶች) ሞተዋል፡፡

በሽታው ከእንስሳት ወደ ሰው የመተላለፍ አቅም ስላለው ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ተስፋው፣ ይህንንም ታሳቢ በማድረግ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ክትባት ሊሰጥ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ዋጃ አካባቢም በሽታው መከሰቱንና ቁጥራቸው የማይታወቁ የቁም እንስሳቶች መሞታቸውን፣ አሁንም ቢሆን እንደ ትልቅ ችግር እየታየ ያለው ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ የቁም እንስሳት ምን ያህሉ ተከትበዋ የሚለው ባለመታወቁ የተነሳ፣ ወረርሽኙ በከተማዋ በቀላሉ ሊገባ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

ከራያ ቆቦ ወደ ትግራይ ክልል መግቢያ ቦታዎች ላይ ወረርሽኙ ተከስቷል ያሉት ቡድን መሪው፣ በሽታው የተከሰቱባቸው ቦታዎች ላይ ገብቶ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ተቋሙ ችግር ውስጥ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የራያ ቆቦ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት በጦርነት ምክንያት የማይገባባቸው አሥር ቀበሌዎች እንዳሉ፣ በእነዚህም ቦታዎቸ 112,814 የቁም እንስሳቶች መኖራቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

በጦርነቱ የተነሳ እነዚህ ቦታዎች ላይ ገብቶ አገልግሎት ለመስጠት መቸገራቸውን፣ የቁም እንስሳቶቹም በወረርሽኙ የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በሽታው በአንድ ቦታ ላይ እስከ 60 ዓመታት ያህል የመቆየት አቅም እንዳለውና በበሽታ የሞተን እንስሳት አቃጥሎ መቅበር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

በራያ ቆቦ ከ350 ሺሕ በላይ የሚሆኑ የቁም እንስሳት (ከብቶች) እንዳሉ የራያ ቆቦ የእንስሳት ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አያሌው ማሞ ተናግረዋል፡፡

እነዚህን የቁም እንስሳት (ከብቶች) ከወረርሽኙ ለመታደግ በቂ የሚባል ሥራ አለመሠራቱን የገለጹት ኃላፊው፣ ‹‹በዚህም ምክንያት በሽታው ቀላል በተባለ መልኩ እንስሳቶቹን ሊያጠቃ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

የቁም እንስሳቱም በወረርሽኙ ከመጠቃታቸው በፊት ክትባት ለመስጠት በቂ የሆነ ክትባት አለመኖሩንና ይህንንም ችግር ለመፍታት የሚመለከተው አካል ድረስ በመሄድ በር ማንኳኳታቸውን አስረድተዋል፡፡

የአማራ ክልል የእንስሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጋሻው ሙጄ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የአባ ሰንጋ በሽታ የሚነሳበት ወቅት ስለሚታወቅ ከወዲሁ ክትባት ይሰጣል፡፡

ከመስከረም እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት ውስጥ በሽታው ሊነሳ እንደሚችል የገለጹት ጋሻው (ዶ/ር)፣ ‹‹ይሁን እንጂ በእነዚህ ወራት ላይ ከፍተኛ የሆነ ዝናብ የሚጥል ከሆነ ወረርሽኙ ላይታይ ይችላል፤›› ብለዋል፡፡

እንደ ጋሻው (ዶ/ር) ገለጻም፣ በሽታው ድርቅ በሚከሰትበት ጊዜ የሚታይ እንደሆነ፣ በዚህም ወቅት ወረርሽኙ በስፋት በመሠራጨት በርካታ የቁም እንስሳቶችን ሊያጠቃ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

ወረርሽኙም የተከሰተባቸውን ቦታዎች ለመቆጣጠር ከቦታ ቦታ የቁም እንስሳቶች እንዳይዘዋወሩ ማድረግ ትልቅ አማራጭ ነው ያሉት ኃላፊው፣ ‹‹ይህንንም በማድረግ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፈውን በሽታ መግታት ይቻላል፤›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡   

አባ ሰንጋ ወረርሽኝ በትግራይ ክልል መከሰቱንና በርካታ የቁም እንስሳቶች መሞታቸውን በወቅቱ ተገልጻል፡፡

አባሰ ንጋ (ቆረባ) በሽታ በቀላሉ ወደ ሰዎች የሚዛመት ሲሆን፣ ሦስት ዓይነት አባ ሰንጋ በሽታዎች በሰዎች ላይ ይከሰታሉ፡፡ እነሱም የቆዳ አባ ሰንጋ፣ የመተንፈሻ አካል አባ ሰንጋና የጨጓራ አባ ሰንጋ በመባል ይታወቃሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...