Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትበኮሎምቢያ ካሊ በተደረገው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አገሩንና ሕዝቡን ያኮራው የአትሌቲክስ ቡድን

በኮሎምቢያ ካሊ በተደረገው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አገሩንና ሕዝቡን ያኮራው የአትሌቲክስ ቡድን

ቀን:

በኮሎምቢያ ካሊ በተደረገው ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎ ውጤት ላስመገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድኑ ሽልማት ተበረከተ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተሳተፉበት የሽልማት መርሐ ግብር 3.2 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

የባህል ስፖርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ የወርቅ ሜዳሊያ ላስመዘገቡ አትሌቶች 300 ሺሕ፣ የብር ሜዳሊያ ላስመዘገቡ ደግሞ 200 ሺሕ፣ ለነሐስ ሜዳሊያ 100 ሺሕ፣ እንዲሁም ዲፕሎማ ላስመዘገቡ አትሌቶች የ50 ሺሕ ብርና ለተሳታፊዎች 30 ሺሕ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

- Advertisement -

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ፣ ለወርቅ ሜዳሊያ 200 ሺሕ፣ ለብር ሜዳሊያ 150 ሺሕ፣ ለነሐስ ሜዳሊያ 75 ሺሕ፣ ዲፕሎማ ላስመዘገቡ አትሌቶች ደግሞ የ50 ሺሕ ብር የገንዘብ ሽልማት ማበርከቱ ታውቋል፡፡

በስካይ ላይት ሆቴል በተደረገው የሽልማት አሰጣጥ መርሐ ግብር ላይ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የባልህና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳና የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...