Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቆቦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በጦርነት የወደሙ ንብረቶችን ለመተካት ችግር እንደሆነበት አስታወቀ

የቆቦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በጦርነት የወደሙ ንብረቶችን ለመተካት ችግር እንደሆነበት አስታወቀ

ቀን:

  • በጦርነቱ ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች ወድመዋል

የቆቦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ንብረቶችን እንደ አዲስ ለመተካትና ከዚህ በፊት ይሰጥ የነበረውን የትምህርት አገልግሎት ወጥ በሆነ መንገድ ለመስጠት ችግር እንደሆነበት አስታወቀ፡፡

የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ደሳለኝ አደም እንደገለጹት፣ ኮሌጁ የትምህርት አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርከታ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ለቁምነገር እንዲበቁ አድርጓል፡፡

ኮሌጁ በማኑፋክቸሪነግ፣ በኢንዱስትሪያል፣ በኢኮኖሚክስ በኢንፍራስትራክቸርና መሠረተ ልማትና በተለያዩ ሙያዎች የትምህርት አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹት አቶ ደሳለኝ፣ በተግባር ለመስጠት የሚጠቀምባቸውን ግብዓቶች ሙሉ ለሙሉ በጦርነቱ በመውደሙ መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡

የወደሙት ንብረቶች በገንዘብ ሲሠላ ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መሆናቸውንና እነዚህንም ንብረቶች እንደ አዲስ ለመተካት መንግሥትንም ሆነ የሚመለከታቸውን አካላት መጠየቃቸውን አክለዋል፡፡

የኮሌጁ ንብረት ከመውደሙ በፊት ማሽነሪ የሚጠቀሙ ትምህርቶችን የሚወስዱ ተማሪዎች እንደነበሩት ያስታወሱት ዋና ዲኑ፣ ከእነዚህም መካከል 238 ተማሪዎችን በመቀበል የንድፈ ሐሳብ ትምህርት እንዲያገኙ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

የንድፈ ሐሳብ ትምህርት ካገኙ 238 ተማሪዎች መካከልም 193 የሚሆኑት ተማሪዎች ግንቦት 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ማስመረቁን አብራርተዋል፡፡

ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት የተግባር ትምህርት ይሰጥበት የነበረውን ማሽነሪ በጦርነቱ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ በመውደሙ የተግባር ትምህርት እየሰጠ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ የብረታ ብረት፣ የእንጨት ሥራ፣ የአውቶሞቲቭ፣ የኤሌክትሮኒክስና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች መውደማቸውን፣ ይህንንም ለመመለስ ረዥም ጊዜ እንደሚፈጅና በቂ የሆነ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡

በ2015 የትምህርት ዘመን የተግባር ሥልጠና የማይጠይቁ ትምህርቶችን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸው፣ ይህንንም ተደራሽ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሰናዳት ክልሉን መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን ኮሌጁ በርካታ ያገለገሉ ኮምፒዩተሮችን በመግዛት፣ የአይሲቲ ትምህርት ለመስጠት ቅድመ ሁኔታዎች ማመቻቸቱን የተናገሩት አቶ ደሳለኝ፣ ኮሌጁ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት ለመስጠት አምስት ዓመታት ያህል እንደሚፈጅበት ጠቁመዋል፡፡

ኮሌጁ አገልግሎት የሚሰጥባቸው አብዛኛው ማሽነሪዎች ከውጭ አገር የሚመጡ መሆናቸውን፣ እነዚህን ማሽነሪዎች ለማግኘት ረዥም ጊዜ እንደሚፈልግ ጠቁመዋል፡፡  

በፌዴራል ደረጃ ከ13 ተቋማት ጋር መተሳሰራቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዓይነት ወደ 51 የሚሆኑ ግብዓቶን ደሴ ከተማ ላይ እንዳስረከቧቸው አስታውሰዋል፡፡

በክልል ደረጃ ደግሞ 673,000 በላይ የሚሆን ገንዘብ ማግኘታቸውን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ፣ ያሉትን ችግሮች በመረዳትና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ መንግሥት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኮሌጁ 1,500 በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳለው፣ ይሁን እንጂ በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ንብረቶች እስኪተኩ ድረስ 500 የሚሆኑ ተማሪዎችን ለማስተናገድ የሚሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...