Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልገቢው ለበጎ ተግባር የሚውለው ‹‹የራስ መንገድ›› ፊልም

ገቢው ለበጎ ተግባር የሚውለው ‹‹የራስ መንገድ›› ፊልም

ቀን:

ለአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት የኪነ ጥበብ ዘርፍ ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ በተለይም የሰው ልጅን አዕምሮ ለማንቃትና ከተለያዩ ድብርቶች ለማውጣት ዘርፉ ጉልህ ሚና አለው፡፡  

ይህንን ሚና ለመጫወትና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በቀላሉ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ‹‹ኅብረት ለበጎ›› የተሰኘ ሆስፒታል ለማስገንባት በአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

በገቢው የግንባታውን ወጪ ለመሸፈን አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ)፣ ሮማን በፍቃዱ፣ ፍፁም ፀጋዬና ሌሎች አርቲስቶች የሚሳተፉበት ‹‹የራስ መንገድ›› የተሰኘ ፊልም ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ምሽት ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ለዕይታ ይቀርባል፡፡

የፊልሙን ይዘትና አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ ረቡዕ ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በብሔራዊ ቴአትር የፊልሙ ደራሲ፣ ዳይሬክተርና ተዋናይ ሰለሞን ቦጋለ፣ ተዋናይ ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ)፣ የፊልሙ ፕሮዲውሰርና የአሚዩዚንግ ፕሮሞንሽና ኤቨንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤት በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ገቢው ለበጎ ተግባር የሚውለው ‹‹የራስ መንገድ›› ፊልም | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ እንደገለጸው፣ ኅብረት ለበጎ ፋውንዴሽንን ዕውን ለማድረግ ‹‹የራስ መንገድ›› ፊልምን ጨምሮ 14 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ተነድፈው እየተሠራ ነው፡፡

‹‹የራስ መንገድ›› ፊልም ይዘቱ የሚያጠነጥነው ቤተሰብ ላይ መሆኑን፣ ፊልሙም ለአገር ውስጥ ዕይታ ለማቅረብ ብቻ ሳይሆን ለኢንተርናሽናል ፌስቲቫሎች ጭምር ለማቅረብ የታሰበ መሆኑን አርቲስት ሰለሞን አስረድቷል፡፡

ለፊልሙም የሚሆኑ ግብዓቶች ከውጭ አገር መምጣቱን ያስታወሰው አርቲስቱ፣ ፊልሙ ኢንተርናሽናል ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል ብሏል፡፡

የፊልሙ ቀረፃ ብቻ 19 ቀናት እንደፈጀ ፊልሙንም ለማሠራት ሌት ተቀን መሯሯጣቸውን፣ እስካሁን በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ዘርፍ ከተጀመረ ከ100 ዓመታት በላይ ቢቆጠርም፣ ይህንን ያህል ሥራ ግን ተሠርቷል ለማለት እንደሚያስቸግር አብራርቷል፡፡

ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል ለዕይታ የሚቀርበው ፊልም ቲኬት 2,000 ሺሕ ብር እየተሸጠ ሲሆን፣ ቲኬቱም በአሜዚንግ ፕሮሞሽን ኢንተርናሽናል ቢሮ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ፊልሙ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ለዕይታ የሚቀርብ ሲሆን፣ በተለይም የፊልም ኢንዱስትሪውን ከማሳደግ አኳያ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብሏል፡፡

በስካይ ላይት ሆቴል ለዕይታ የሚቀርበውን ፊልም ለማሳየት 2,000 ሺሕ ያህል ቲኬት መዘጋጀቱን፣ እስካሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በለገጣፎ ለገዳዲ ከመንግሥት በተሰጠ መሬት ላይ ሆስፒታሉን ለመገንባት ሁለት ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተናግሯል፡፡

ለሆስፒታሉ ግንባታም ስድስት ሔክታር መሬት መረከባቸውን፣ ሆስፒታሉንም ገንብቶ ለማጠናቀቅ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል የሚለውን ለመመለስ የሆስፒታሉ ዲዛይኑ እንደ አዲስ ስለሚሠራ ለጊዜው አልታወቀም ብለዋል፡፡

‹‹የራስ መንገድ›› ፊልም ተሠርቶ ከተጠናቀቀ የቆየ ቢሆንም፣ አንዳንድ ነገሮችን ለማስተካከል ሲባል ፊልሙ ለዕይታ ሳይቀርብ መቆየቱን የፊልሙ ፕሮዲውሰር አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡

የፊልሙ ገቢ በከፊል ለሆስፒታሉ ግንባታ እንደሚውል፣ ይህም ግምት ውስጥ የገባው ዋናው ምክንያት አብዛኛው ሕፃናትና እናቶች በተለያዩ በሽታ ተይዘው ለመታከም ሲቸገሩ ማየት የተለመደ በመሆኑ እንደሆነ አርቲስት ሳምሶን (ቤቢ) ተናግሯል፡፡

‹‹የሆስፒታሉ ግንባታ በተወሰኑ ግለሰቦች አቅም ብቻ የሚከናወን አይደለም፤›› ያለው አርቲስት ሳምሶን፣ ይህንንም ታሳቢ በማድረግ በውጭ አገርም ሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሆስፒታሉ ግንባታ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ ከ68 በላይ ፊልሞችን፣ ከ16 በላይ የመድረክ ቴአትሮችን፣ ከስምንት በላይ ተከታታይ የቴሌቪዥንና በርካታ የሬድዮ ድራማዎችን የተጫወተው አርቲስት ሰለሞን፣ ከሰባት በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገሮች ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡

በሩዋንዳ ፊልም ፌስቲቫል በግሩፕ ሽልማቶችን መቀበሉ፣ ከልዩ ልዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቅናና የምሥጋና ሽልማትና ሰርተፍኬቶችን ማግኘቱ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...