Monday, December 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አዲስ የጭነት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በ30 ሚሊዮን ብር ካፒታል ወደ ሥራ ገባ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በሞተር ብስክሌት፣ በቫን፣ በፒካፕ፣ በአይሱዙ፣ በሲኖትራክና በሌሎች የተሽከርካሪ ዓይነቶች የጭነት አገልግሎት ለመስጠት ማስዴል የተሰኘ ድርጅት በ30 ሚሊዮን ብር ካፒታል ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

የጭነት አገልግሎቱን ለመስጠት ማስዴል የተሰኘ መተግበሪያ ማበልፀጉን፣ የጨረታ አማራጮችን ያካተተ መሆኑን ማክሰኞ ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሁሪያ ዓሊ በተገኙበት ሥራውን አስጀምሯል፡፡

መተግበሪያ ከማበልፀግ በተጨማሪ ከአሥር ሺሕ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚያስገኝ ዘርፍ መሆኑን፣ የማስዴል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተዋበ ይላቅ ተናግረዋል፡፡

መተግበሪያውን ከማበልፀግ በተጨማሪ ለደንበኞች ንብረት ደኅንነት ከቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር ውል መገባቱን ገልጸዋል፡፡

በድርጅቱ ጥናት መሠረት በአንድ ዓመት ውስጥ ከአሥር ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ለማግኘት ማቀዱን፣ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስረድተዋል፡፡

እስካሁን ከአንድ ሺሕ በላይ የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦች መመዝገባቸውን፣ ድርጅቱ 40 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ለመመዝገብ ማቀዱን ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የጭነት አገልግሎት ከሚሰጥበት የዋጋ ተመን በማስዴል ድርጅት ደግሞ 30 እና 40 በመቶ በሚቀንስ ዋጋ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ከአዲስ አበባና ዙሪያዋ በተጨማሪ በሌሎች የክልል ከተሞች አገልግሎት ለመስጠት ማቀዳቸውን የተናገሩት አቶ ተዋበ፣ ከተለያዩ ቦታዎች ብዙ ጥያቄዎች እየመጣለቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በምሥራቅ አፍሪካ ለሦስት ዓመታት በኋላ ሥራውን እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡

የማስዴል መተግበሪያ የዋጋ ቅናሽና የንብረት ደኅንነት ከመስጠቱ በተጨማሪ፣ ለቁጥጥርና ለደኅንነት እንዲያመች ተሽከርካሪዎች ላይ ጂፒኤስ ለመግጠም መታቀዱን አክለዋል፡፡

የማስዴል መተግበሪያ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ መሆኑን፣ በቀጣይ በሌሎች የአገር ውስጥ ቋንቋዎች አገልግሎቱን ያሰፋል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች