Sunday, December 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአትሌቲክሱ ሰው ተባባሪ ፕሮፌሰር (ዶ/ር) በዛብህ ወልዴ (1952 - 2014)

የአትሌቲክሱ ሰው ተባባሪ ፕሮፌሰር (ዶ/ር) በዛብህ ወልዴ (1952 – 2014)

ቀን:

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ዓለም አደባባይ ላይ ሰንደቅ ዓላማዋ ሲውለበለብና ደስታና ፌሽታ ሲሆን፣ ቀዳሚውን ሙገሳና ምሥጋና አትሌቶች ይወስዳሉ፡፡ በአንፃሩ ለአትሌቲክሱ እስትንፋስ የሆኑ በርካታ ባለሙያዎች ከበስተጀርባ መኖራቸው ዕሙን ነው፡፡ በሌላ በኩል ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዕውቀታቸውን ሲለግሱና በብዕራቸው ተተኪዎችን ሲያስተምሩ ከርመዋል፡፡

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ጎን የማይታጡት ባለሙያው አንደበተ ርቱዕ መሆናቸው የቅርብ ጓደኞቻቸው ይናገራሉ፡፡ እኚህ አንደበተ ርቱዕ ምሁር በዛብህ ወልዴ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ተባባሪ ፕሮፌሰር በዛብህ ወልዴ (ዶ/ር) በኦሊምፒክ እ.ኤ.አ. 2000 ሲድኒ ኦሊምፒክ፣ በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ፣ በዓለም ሻምፒዮና ቤጂንግ 2008፣ ኳታር ዶሃ 2019፣ እንዲሁም በዘንድሮው የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና ላይ አቅንተው የተለመደውን ሙያዊ ድጋፋቸውን አድርገዋል፡፡ የእነዚህ ሁሉ ጊዜያት የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የቁርጥ ቀን ልጅ በዛብህ (ዶ/ር) ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ አንድ ትልቅ የአትሌቲክስ ስፖርት አባት አጣች›› ሲል ሞታቸውን ያሰማው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሲሆን፣ ባለሙያው በአትሌቲክሱ ውስጥ የነበራቸውን ሚና አሥፍሯል፡፡

በዛብህ ወልዴ (ዶ/ር) በቀድሞው የኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ (በአሁኑ አጠራር ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ) እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከመምህርነት እስከ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሁም፣ በትምህርት ክፍል ኃላፊነት ያገለገሉና እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው ድረስ በአትሌቲክስ ስፖርት ሳይንስ ስፔሻላይዝ ያደረጉ ባለሙያዎችን ያፈሩ፣ በስፖርት አስተዳደር ዓለም አቀፍ ኢንስትራክተርነት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ልዩ ልዩ ትምህርታዊ  ጽሑፎችን በማዘጋጀትና በማሳተም ይታወቃሉ፡፡

ከዚህ ባሻገር በስፖርት ሳይንስ ዘርፍ የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን በማማከር፣ በበርካታ ሚዲያዎች ለስፖርት ጠቃሚ ምክረ ሐሳቦችን በማቅረብ በሙያቸው ‹‹አንቱታን›› ካተረፉ ምሁራን ጎራ ቀድመው የሚጠሩ ሰው ነበሩ፡፡

በዛብህ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውስጥ ከ12 ዓመታት በላይ ከዋና ጸሐፊነት ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ታሪክ በመጽሔት መልክ እንዲዘጋጅ በማስተባበርና በመምራት፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዋና ጸሐፊነት፣ እንዲሁም ከአሥር ዓመት በላይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በመሆንና በዓቃቤ ነዋይነት፣ በቴክኒክና ሕክምና ኮሚቴ ሰብሳቢነት፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፕሬዚዳንትነት በመምራት ለበርካታ ዓመታት አገራቸውን አገልግለዋል፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ እጅግ ትልቅ ሥፍራ የነበራቸው አንጋፋውና ስመ ጥሩ የስፖርት ሳይንስ ምሁር በቀድሞው ባሌ ክፍለ አገር ሐምሌ 23 ቀን 1952 ዓ.ም. የተወለዱ ሲሆን፣ በጥቂት ቀናት ሕመም በ62 ዓመታቸው በድንገት ሐሙስ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ተለይተዋል፡፡

ቅዳሜ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ጓደኞቻቸው፣ እንዲሁም የሥራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ተፈጽሟል፡፡ በዛብህ (ዶ/ር) ባለ  ትዳርና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...