Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየተሽከርካሪ አደጋ በአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ - ጎተራ ማሳለጫ መንገድ

የተሽከርካሪ አደጋ በአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ መንገድ

ቀን:

በይፋ ለትራፊክ ክፍት ከሆነ  የ15 ቀናት ያህል ጊዜ ባስቆጠረው የአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ መንገድ፣ ረቡዕ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ከአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ ይጓዝ የነበረ ባለተሳቢ ከባድ መኪና ባደረሰው አደጋ በአካባቢው በነበሩ ሰባት ተሽከርካሪዎችና በመንገድ ዳር መብራት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡ ከአሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት በተነሳ በሰው ሕይወትና አካል ላይ እየደረሰ ካለው ጉዳት ባሻገር በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ውድመት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተገንብቶ ነሐሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በይፋ ለትራፊክ ክፍት በተደረገው የአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ መንገድ ላይ ተደጋጋሚ አደጋዎች እየደረሱ ይገኛሉ፡፡ በሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ንጋት ላይ የደረሰ የትራፊክ አደጋም አንዱ ነው፡፡ የትራፊክ አደጋው በሰው ሕይወትና አካል ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ፣ ከፍተኛ መዋለ ነዋይ ፈሶባቸው የተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ለብልሽት እየተጋለጡ መሆኑን የሚገልጸው ባለሥልጣኑ፣ አሽከርካሪዎችና እግረኞች የትራፊክ ሕግና ደንብ አክብረው በመንቀሳቀስ ራሳቸውን ከአደጋና ከህሊና ፀፀት፣ የሰው ልጅ ሕይወትንና የመንገድ ሀብትን ደግሞ ከውድመት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የተሽከርካሪ አደጋ በአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ - ጎተራ ማሳለጫ መንገድ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

(ምንጭ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...