Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየሙዚቀኛ ዓለማየሁ እሸቴ አንደኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ ‹‹አዲስ አበባ ቤቴ›› በሚል ኮንሰርት...

የሙዚቀኛ ዓለማየሁ እሸቴ አንደኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ ‹‹አዲስ አበባ ቤቴ›› በሚል ኮንሰርት ሊዘከር ነው

ቀን:

  • በአርቲስቱ ሕይወት ዙሪያ ያጠነጠነ መጽሐፍም ይመረቃል

ሙዚቀኛ ዓለማየሁ እሸቴ ከዚህ ዓለም የተለየበትን የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ ‹‹አዲስ አበባ ቤቴ›› በሚል ኮንሰርትና በሕይወቱ ዙሪያ በተጻፈው መጽሐፍ ምርቃት ለመዘከር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዘርፎች ማኅበራት ኅብረት አስታወቀ፡፡

ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል የሚካሄደውን የመታሰቢያ ኮንሰርትና ‹‹ዓለማየሁ እሸቴ፣ አዲስ አበባ ቤቴ›› በሚል የተዘጋጀው መጽሐፍ ምረቃን አስመልክቶ በተዘጋጀ መግለጫ እንደተገለጸው፣ የሙዚቃ ኮንሰርቱ በኅብረቱ፣ በዓለማየሁ ቤተስቦች፣ በወዳጆቹና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ትብብር የሚቀርብ ነው፡፡

ኮንሰርቱ ዓለማየሁ ለጥበቡ ያበረከትውን ጥረት ለመዘከርና ጥበቡን ለተተኪው ትውልድ ለማሳየት የሚቀርብ መሆኑን የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ዳዊት ይፍሩ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የዓለማየሁ እሸቴን ግጥም፣ ዜማና ቅንብር ዘመን ተሻጋሪነት ለማሳየት፣ የጥበብ ውጤቶች ለወጣትና ለማሳየት፣ የጥበብ ባለሙያዎች በመተባበር ያላቸውን አቅም የሚያሳዩበት መድረክ ስለሆነ፣ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የሚሳተፉ ድምፃዊያንና ሙዚቀኞች በማኅበሩ የተሰባሰቡ ሲሆን፣ በራስ ተነሳሽነት በነፃ የሚቀርብ ዝግጅት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ለመድረክ ግንባታ፣ ድምፅና መብራት እንዲሁም የሆቴል ኪራይና መስተንግዶ ወጪዎች በሙሉ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚሸፈኑ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ይህን ዓይነት ዝግጅት ለአንጋፋዎች፣ ዘመን ተሻጋሪ የጥበብ ሥራ ላበረከቱ ሙያተኞች በተከታታይ የሚቀርብ መሆኑን፣ ይህም እርስ በእርስ ለመሞጋገስ አንድ አርቲስት ሲሞት ሳይሆን በሕይወት ዘመኑ አበባ በእጁ የሚሰጥበት፣ በሒደትም በኑሮ የተጎዱና በሕመም የሚሰቃዩ አርቲስቶች የሚደገፉበት የምዕራፍ መጀመሪያና ላለመተባበር አዝማሚያ ያሳዩ የሚማሩበት መድረክ እንደሚሆን ያላቸውን እምነትም አሳውቀዋል፡፡

መድረኩ ዓለማየሁ እሸቴ በሙያው የተከበረ፣ በኑሮው የተሳካለት፣ በድርሰቶቹና ቅንብሮቹ እንዲሁም የመድረክ አቀራረቡ ለተተኪው ትውልድ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን በገሀድ የሚታይበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል በሚሰናዳው ‹‹በዓለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ›› ኮንሰርትና የመጽሐፍ ምረቃ ላይ ወዳጆቹ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አርቲስት ዓለማየሁ እሸቴ ነሐሴ 27 ቀን 2013 ባደረበት የልብ ሕመም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል። ከ300 በላይ የሙዚቃ ሥራዎችን ያበረከተው ዓለማየሁ፣ በአድናቂዎቹ “ጌሪ ኮፐር”፣ “ኢትዮጵያዊው ኤልቪስ”፣ “ዓለማየሁ ቴክሱ፣ ነጭ ነው ፈረሱ” በሚል  ይጠራ ነበር፡፡ በዓለም አቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያን ሙዚቃ በማቅረብ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምጻዊው፣ ለመጀመርያ ጊዜ በ1955 ዓ.ም በፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ ውስጥ በመቀጠር ነበር የሙዚቃ ስራውን የጀመረው፡፡ በሙዚቃ ስራዎቹም ‹‹ኤልቪስ ፕሪስሊ›› የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቶት ነበር።

ሰኔ 10 ቀን 1934 ዓ.ም. አዲስ አበባ የተወለደው ድምፃዊ ዓለማየሁ፣ በተለይ “ተማር ልጄ” እና “አዲስ አበባ ቤቴ” በሚሉት የሙዚቃ ስራዎቹ ታዋቂነትንና ተወዳጅነትን አትረፏል፡፡ የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ ከፍ ወዳለ ደረጃ ካደረሱት ድምፃውያን መካከልም አንዱ ነው።

የጥላሁን ገሰሰን ዘፈኖችም ይጫወት የነበረው አርቲስቱ፣ “ስቀሽ አታስቂኝ”፣ “ እንደ አሞራ”፣ “ ማን ይሆን ትልቅ ሰው”፣ “ምሽቱ ደመቀ”፣ “የወይን ሃረጊቱ”፣ “የሰው ቤት የሰው ነው”፣ “ደንየው ደነባ”፣ “ትማርኪያለሽ”፣ “ወልደሽ ተኪ እናቴ”፣ “ማሪኝ ፡ ብየሻለሁ” የሚሉት ሙዚቃዎቹ ከታዋቂ ስራዎቹ መካከል ናቸው።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...