Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ ለ49ሺሕ ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ሥልጠና ሊሰጥ ነው

በአዲስ አበባ ለ49ሺሕ ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ሥልጠና ሊሰጥ ነው

ቀን:

ከአሥራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርታቸውን ላቋረጡ ወጣቶች የሥራ ልምምድ የሚሰጥ ‹‹ብቃት›› የተሰኘ ፕሮጀክት ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ 49 ሺሕ ወጣቶችም ሥልጠና ያገኛሉ ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ በፌደራል ደረጃ 70 ሺሕ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚደረግ መሆኑም፣ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ እንደተናገሩት፣ ፕሮጀክቱ በመላው ኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ከሥልጠናው ተጠቃሚዎች ከሚሆኑት ወጣቶች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በአዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡

‹‹ብቃት›› የተሰኘው ፕሮጀክት በሁሉም ክፍላተ ከተሞችና በ36 ወረዳዎች የሚተገበር እንደሚሆን፣ ወጣቶቸ የሥራ ልምምድ የሚያደርጉበት ድርጅቶች መለየታቸውንና  ከ1,500 በላይ ተቋሞች ፍቃደኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ የትራንስፖርት ዘርፍ፣ ኢንዱስትሪዎችና ሌሎችም ተቋሞች ለወጣቶች የሥራ ልምምድ ሥልጠና ለመስጠት ፍቃደኛና ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከ12ኛ ክፍል ካቋረጡና ከ18 እስከ 25 የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ወጣቶች 80 በመቶ ያህሉ ሥራ አጥ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ የሙከራ ጊዜ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 400 ወጣቶች መመዝገባቸውንና ከእነዚህ ውስጥ 186 ወጣቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን የፕሮጀክቱ ባህሪ በድርጅቶች ላይ ወጣቶቹ ተሰማርተው የሥራ ላይ ልምምድ የሚያደርጉበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ሥራ ላይ ልምምድ ሥልጠናው 60 በመቶ ተሳታፊዎች ሴት ወጣቶች መሆናቸውንም አክለዋል፡፡

በ36 ወረዳዎች ተግባራዊ በሚደረገው የሥራ ላይ ልምምድ ሥልጠና፣ በ2015 ዓ.ም. ከ12 ሺሕ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉ መሆኑን ምክትል ከንቲባው አስረድተዋል፡፡

እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ከ27,000 በላይ ወጣቶችን መመዝገባቸውን የገለጹት አቶ ጃንጥራር፣ ለ21,000 ያህሉ የክህሎት ሥልጠና የሚወስዱበት ሁኔታ ተመቻችቷል ብለዋል፡፡

ብቃት የተሰኘው ፕሮጀክት ዓላማ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ የከተማ ወጣቶችን በተለያዩ የግል ድርጅቶች ገብተው የሥራ ልምድ እንዲያገኙ ማስቻል ዓላማው ነው፡፡

ሥልጠናው የሕይወት፣ የቴክኒክ፣ መሠረታዊ የኮምፒዩተር፣ ሥራ አፈላለግ ክህሎቶችን የሚያገኙበት ሥልጠና ለሦስት ዓመት የሚቆይ ሲሆን፣ በ‹‹ብቃት›› ፕሮጀክት ለሠልጣኞች በቀን 90 ብር በወር ሲሰላ 1980 ብር የትራንስፖርትና የምሳ አበል የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የስድስት ወሩን ሥልጠና ያጠናቀቁ ሠልጣኞች ለተጨማሪ ሦስት ወራት ክፍያው እንደሚቀጥል፣ ልጆች ላላቸው ሴት ወጣቶች ተጨማሪ በወር 600 ብር ድጎማ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...