Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹የሐድይ ነፈራ›› ፕሮጀክት አሁናዊ ገጽታ

‹‹የሐድይ ነፈራ›› ፕሮጀክት አሁናዊ ገጽታ

ቀን:

‹‹ሐድይ ነፈራ›› በሐዲያ ብሔር የተለያዩ ባህላዊ ሥርዓተ ክዋኔዎች የሚከወኑበት ቦታ ነው፡፡

ይህንን ሥፍራ የብሔሩን ማኅበረ ባህላዊ እሴቶች አኗኗርን መሠረት በዞኑ ሆሳዕና ከተማ በተለምዶ ጎፈር ሜዳ ተብሎ በሚጠራው የውኃ ግድብ አካባቢ በሚገኘውና ለዚሁ ተብሎ ተለይቶ የተከለለ ሥፍራ ሲሆን፣ መጠሪያ ስያሜውም ‹‹ሐድይ ነፈራ›› ይባላል፡፡

‹‹ሐድይ ነፈራ›› በሐዲያ ብሔር ባህል የዘመን መለወጫ የ‹‹ያሆዴ›› ክብረ በዓልን የበዓሉ ተሳታፊዎች ተሰባስበው በተለያዩ ሥርዓተ ክዋኔዎች በአንድነት የሚያከብሩበት ነው፡፡

በዞኑ በዓመቱ በሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ ሐድይ ነፈራን አንዱ አካል አድርጎ እያለማ እንደሚገኝ የዞኑ አስተዳደር ገልጾ፣ በዚህም ሥፍራውን በመከለል የብሔሩን ባህላዊ እሴቶች የአኗኗር ሥርዓት ያካተቱ የተለያዩ ግንባታዎች በምዕራፍ ተከፋፍለው እየተገነቡ እንደሚገኙ አክሏል፡፡

እየተገባደደ የሚገኘው የ‹‹ሐድይ ነፈራ›› ፕሮጀክት
እየተገባደደ የሚገኘው የ‹‹ሐድይ ነፈራ›› ፕሮጀክት

ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቀው ፕሮጀክቱ፣ በ50 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ ሥራው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑንና ግንባታውም የብሔሩን ‹‹ያሆዴ›› በዓልና ሌሎች የተለያዩ ባህላዊ ሥርዓቶችን መከወን በሚያስችል መልኩ መከናወኑን አስታውቋል፡፡

የ‹‹ያሆዴ›› ክብረ በዓል ሲከበር የበዓሉ ተሳታፊዎች መቀመጫ ቦታ፣ ለተለያዩ ሥርዓቶች መከወኛ መድረኮች፣ የባህል ሽማግሌዎች ባህላዊ ምርቃትና የዕርቅ ሥነ ሥርዓት የሚፈጽሙበት ሥፍራ በግንባታው ውስጥ ከተካተቱት ይገኝበታል፡፡

የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራና ጨዋታዎች የሚከናወኑበት ሥፍራ፣ የፈረስ መጋለቢያ፣ ሳቴ (ችቦ) የሚቀጣጠልበትና የተለያዩ የብሔሩን ባህላዊ ጉዳዮች ለማከናወን የሚያስችሉና የቱሪስት መስህብ በመሆን መዝናኛ ሥፍራዎች ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

ግንባታው በቅርቡ ተጠናቆ ለመጪው የሐዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ‹‹ያሆዴ›› ክበረ በዓል ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...