Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጦርነቱ የመምህራንን ጥያቄ በጊዜ ለመመለስ እንቅፋት መሆኑን ማኅበሩ አስታወቀ

ጦርነቱ የመምህራንን ጥያቄ በጊዜ ለመመለስ እንቅፋት መሆኑን ማኅበሩ አስታወቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተለያዩ ጊዜያት እየተፈጠረ ያለው ጦርነት፣ መምህራን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንቅፋት እንደሆነ ገለጸ፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቴ (ዶ/ር) ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በተለያዩ ጊዜያት የዩኒቨርሲቲ መምህራን በዋነኝነት እያነሱ ላሉት ጥያቄዎች፣ ‹‹ጦርነቱ ያጠላበት ጥላ አለ›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ ይህ ባይሆንም ጥያቄዎቹ ተወስደው መታየት ያለባቸው እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

የማማከር፣ የምርምርና የትርፍ ሰዓት ክፍያ በዩኒቨርሲቲዎች ወጥነት እንዲኖራቸው የተነሱት ጥያቄዎችን ጨምሮ ምንም ጦርነት ውስጥ ቢኮንም የተመለሱ አሉ ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አሁንም ቅሬታ ያለበት የሥራ ምዘናና ደረጃ (Job Evaluation and Grading -JEG) ላይ ያሉት ምላሾች አያረኩም፡፡ ስለዚህም ጥያቄዎቹ ይቀጥላሉ ሲሉም አክለው ገልጸዋል፡፡

‹‹የመምህራን ጥያቄ አንዴ ከተነሳ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ምላሽ ይኖረዋል፤›› ሲሉ ዮሐንስ (ዶ/ር) ከዚህ በፊት በ1961፣ 1985 እና በ2001 ዓ.ም. ላይ ይነሱ የነበሩ የቤት ጥያቄዎች በ2008 ዓ.ም. መልስ ማግኘታቸውን እያጣቀሱ ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የዩኒቨርሲቲ መምህራን ደመወዝ በቂ እንዳልሆነ መናገራቸውን በማስታወስ፣ እንዴት እንደሚፈታ መወያየትና መስማማት ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ማኅበሩ ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ ተማሪዎችንና መምህራንን ከማገዝ አኳያ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ማኅበሩ እንደ አዲስ ያገረሸው ጦርነት እንዳሳሰበው በመግለጫው ተናግሮ፣ ጦርነቱም በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ለሰላም የማስተባበር ኃላፊነት እንዲቀጥል፣ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንዲቀጥል አያይዞ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የማኅበሩን መግለጫ ሲያነሱ እንደተናገሩት፣ ከፌደራል መንግሥት በኩል ተነግሮ የነበረው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመደራደር ፍላጎት በሁሉም አካሎች ተነሳሽነት ተወስዶ ተግባራዊ እንዲሆንም ጠይቀዋል፡፡ ለትግራይ ሕዝብም ማኅበሩ የሰብዓዊ ድጋፉና ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዲቀጥል ሲል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

‹‹የአንድ አገር ዜጎች ሆነን እያለን መግባባት አቅቶን መሳቂያ ሆነን መቀጠል የለብንም፤›› ብለዋል፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንያት ለትምህርት ይውል የነበረው ሀብት እየወደመ እንደሚገኝና መምህራንና ተማሪዎችም ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ ከትምህርት ገበታቸው እየተነሱ ነው ሲል ገልጿል፡፡

በአገሪቱ ከ700,000 በላይ መምህራንና ከ30 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከመዋለ ሕፃናት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ በጦርነቱ ምክንያትም በርካታ ትምህር ቤቶች ሙሉ በሙሉና በከፊል መውደማቸውን ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን፣ ማኅበሩም ይህ እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ያስጠናው ጥናት እንደሚያሳየው በጦርነቱ ምክንያት ለወደሙ የትምህርት መሠረተ ልማቶች ከ2.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ መልሶ ለመገንባት ያስፈልጋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...