Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየሱዳኑ ክለብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው ግጥሚያ ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆንለት ጥያቄ አቀረበ

የሱዳኑ ክለብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው ግጥሚያ ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆንለት ጥያቄ አቀረበ

ቀን:

  • የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታ እንዲያስተናግዱ ሦስት ከተሞች ተመረጡ

የሱዳኑ አልሂላል ኦምዱርማን እግር ኳስ ክለብ ለአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ፣ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚያደርገው ግጥሚያ ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆንለት፣ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጥያቄ ማቅረቡ ታወቀ፡፡ ክለቡ ከደኅንነት ጋር በተገናኘ ሥጋት እንዳለው አስታውቋል፡፡

ክለቡ በይፋዊ ድረ ገጹ እንደገለጸው ከሆነ፣ አል ሂላል ኦምዱርማን እግር ኳስ ክለብ፣ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሊደረግ የታሰበው ውድድር ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆንለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የሚያደርገው አል ሂላል ኦምዱርማን እግር ኳስ ክለብ፣ ለጥያቄው መነሻ የሆነው፣ በሰሜን ኢትዮጵያ እንደገና ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ የደህንነት ሥጋት ያደረበት መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ለማግኘት የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ኃላፊዎችን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ ለአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግና ለአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከተማ፣ በሜዳቸው የሚያደርጉትን ጨዋታ እንዲያስተናግድ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በጊዜያዊነት ፈቃድ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደሚጀመር የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር፣ የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ በሦስት ከተሞች እንደሚያከናውን የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ፡፡ በማሻሻያ ግንባታ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ስታዲየም፣ በአዲሱ የውድድር ዓመትም የሊጉን ጨዋታ ያስተናግዳል ወይስ አያስተናግድም የሚለው ጉዳይ አሁንም እንዳለየለት የሚያረጋግጡ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር ባለፈው ዓርብ ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፣ የ2015 የውድድር ዓመት የጨዋታ መርሐ ግብር የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በሦስት የክልል ከተሞች፣ ማለትም በባህር ዳር፣ በድሬዳዋና በአዳማ ከተሞች በሚገኙ ስታዲየሞች ይከናወናል ብሏል፡፡ የሊጉ አክሲዮን ማኅበር በዕድሳት ላይ ስለሚገኘው የአዲስ አበባ ስታዲየም ጉዳይ ምንም ያለው ነገር የለም፡፡

የማሻሻያ ግምባታውን በሚመለከት ለአዲስ አበባ ስታዲየም ቅርበት ያላቸው ነገር ግን ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ባለሙያዎች ለሪፖርተር እንደሚገልጹት ከሆነ፣ ‹‹ስታዲየሙ የፕሪሚየር ሊጉ የ2014 የውድድር ዓመት የመጨረሻውን ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር እንደሚያስተናግድ ነው፡፡ በ2015 የሚደረገው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግም የሚጀመርባው ስታዲየሞች ሲገለጹ፣ የአዲስ አበባ ስታዲየም በመጀመሪያው ዝረዝሩ አለመካተቱ ጥያቄ ሆኖብናል፤›› በማለት የስታዲየሙ ግምባታ ምን ያህል እየተጓተተ እንዳለ ከዚህ በላይ ማሳያ ሊኖር እንደማይችል ያስረዳሉ፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...