Saturday, July 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ ገንዘብ ሚኒስቴር ፈቀደ

የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ ገንዘብ ሚኒስቴር ፈቀደ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጀት ይዞ በመግዛት በሥሩ ለሚተዳደሩ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች፣ የሴቶች ንፅናህ መጠበቂያ (ሞዴስ) ለማቅረብ ማቀዱንና ለዚህም የገንዘብ ሚኒስቴር ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ መፍቀዱን የሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ አገልግሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው ከትምህርት ቤት ምገባና ሌሎች ድጋፎች ጋር አብሮ ለአዲሱ ዓመት በሥሩ ለሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ለማሰራጨት አቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ለዚህም የምገባ ኤጀንሲ የ2015 በጀት ዕቅድ ውስጥ እንዳስገባው የቢሮው የሴቶች ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የምገባ ኤጀንሲው ከሁለት ዓመት በፊት በአዋጅ ሲቋቋም የምገባ ፕሮግራም፣ ደብተር፣ ቦርሳና የተለያዩ መማሪያ ቁሳቁሶች ዝቅተኛ የኢኮኖሚ አቅም ላላቸው ተማሪዎች በትምህርት ቤት ይቀርብ ነበር፡፡ እንደ ወ/ሮ ሜሮን ገለጻ የንፅህና መጠበቂያዎች ለሴት ተማሪዎች ማቅረብም በቢሮው ጠቋሚነት አዋጅ ውስጥ ተካቶ የነበረ ሲሆን እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም፡፡

‹‹አቅርቦቱ በባለ ሀብቱ ድጋፍ እንደመቆሙ የምገባና የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት ጥሩ የነበረ ቢሆንም፣ የሴቶች ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦት ላይ ምንም አልተሠራም ነበር፤›› ሲሉ ኃላፊዋ የአዋጁን ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ አለመሆን ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ሜሮን ከሚመሩት የሴቶች ዘርፍ በሰፊው ከጠየቃቸው ጥያቄዎች ለሴቶች በትምህርት ቤት ውስጥ ሞዴስ፣ ሳሙናና ፓንትም በመንግሥት በጀት ተገዝቶ እንደምገባው ፕሮግራም እንዲቀርብ ነበር፡፡ ቢሮው በ2014 ባጠናው ጥናት መሠረት በወር አምስት ቀን እንዲሁም በዓመት 50 ቀን ሴቶች ተማሪዎች በዚህ ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንደሚቀሩ አረጋግጧል፡፡

ለዘጠኝ ወራት ገንዘብ ሚኒስቴርን ሲጠይቁ ቆይተው አሁን ምላሽ ማግኘታቸውን በመናገር፣ ይህ ውሳኔ የመንግሥት የራሱን ወጪ በብዙ እንደሚቀንሰው ወ/ሮ ሜሮን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከ300 ሺሕ እስከ 400 ሺሕ ሴት ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ይገመታል፡፡ በአገር ደረጃ ግን ከቀረጥ ነፃ ያልተደረገ ሲሆን፣ የየክልሉ ኃላፊዎች ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚገባቸው ወ/ሮ ሜሮን ተናግረዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ከወሰናቸው ውሳኔዎች አንደኛው በግል የሴቶችን ንፅህና መጠበቂያ ነጋዴዎች ለሚያስገቡ የጉምሩክ ቀረጥ ከ30 በመቶ ወደ አሥር በመቶ የቀነሰ ሲሆን፣ ከተጨማሪ ታክስ (ሱር ታክስ) ደግሞ ነፃ አድርጓል ሲሉ ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...