Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትክለቦች ‹‹ማንነት››ን መነሻ ያደረገ ስያሜ እንዲቀይሩ ተጠየቀ

ክለቦች ‹‹ማንነት››ን መነሻ ያደረገ ስያሜ እንዲቀይሩ ተጠየቀ

ቀን:

  • ካፍ ክለቦችን የሚመለከት አዲስ ደንብ ማውጣቱ ተሰማ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቦች ‹‹ማንነት››ን መነሻ ያደረገ ስያሜያቸውን እንዲቀይሩ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም፣ እስካሁን ባለው ስያሜያቸውን እንዲቀይሩ ጥያቄ ከቀረበላቸው ክለቦች መካከል፣ ከቀድሞ ‹‹መከላከያ›› መቻል ውጭ ብዙዎቹ ምላሽ አለመስጠታቸው ተገለጸ፡፡

ፌዴሬሽኑ ካለፈው ዓመት ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የብዙዎቹ ክለቦች ስያሜ ብሔርና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ በመሆኑ፣ ስያሜያቸውን እንዲቀይሩ፣ ካልሆነ ግን በአዲሱ የውድድር ዓመት (2015) መመዝገብ እንደማይችል ነው ሲያስጠነቅቅ የቆየው፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት የተመሠረተው የፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር በተመሳሳይ፣ ከስያሜ ጋር በተያያዘ ክለቦች ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት አዲስ መመርያና ደንብ ማዘጋጀቱ ቢነገርም፣ አሁን ባለው ሁኔታ ግን የመመርያው ተፈጻሚነት ጥያቄ ላይ መውደቁ ጭምር የሚናገሩ አሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የዘንድሮው ውድድር የሚጀምረው መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በመሆኑ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የክለቦችን ስያሜ አስመልክቶ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፣ ስያሜያቸውን እንዲቀይሩ ጥያቄ የሚነሳባቸው ክለቦች መመርያውን ማክበር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ ይሁንና ሪፖርተር በዚህ ጉዳይ ያነጋገራቸው የፌዴሬሽን አመራሮች በበኩላቸው፣ ‹‹አሁን ላይ ብዙዎቹ ክለቦች ስያሜያቸውን ለመቀየር ዝግጁ አይደሉም፣ ምክንያቱም የቀጣዩ ዓመት የጨዋታ መርሐ ግብር ሊጀመር የቀረው በቀናት የሚቆጠር ጊዜ እንደመሆኑ መጠን ክለቦቹ ከመመዝገባቸው በፊት ፍላጎት ሊያሳዩ በተገባ ነበር፤›› ብለዋል፡፡

አመራሮቹ አክለው እንደሚናገሩት ከሆነ፣ በዚህ ምክንያት እስካሁን የክለቦቹን ማንነት ግልጽ ባያደርጉም ስያሜያቸውንና ዓርማቸውን የመጠቀም መብት ያላቸው ሁለት ክለቦች ብቻ መሆናቸውን ግን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ የተቀሩት በሙሉ ስያሜያቸውንም ሆነ ዓርማቸውን መጠቀም የሚያስችል መብት ለመጠቀም ገና ብዙ እንደሚቀራቸው ጭምር ተናግረዋል፡፡ 

በሌላ በኩል የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሽን (ካፍ) ክለቦች ተቋማዊ አደረጃጀታቸውን የሚገልጽ ፈቃድ (ክለብ ላይሰንሲንግ) ለማግኘት አዲስ መሥፈርት ማውጣቱን ይፋ አድርጓል፡፡ አሁን ባለው ከፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ የካፍን መሥፈርት ያሟሉ ብቸኛ ክለቦች ስለመሆናቸው ጭምር ተነግሯል፡፡

ካፍ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ከሆነ፣ በፕሪሚየር ሊግ ደረጃ ለሚጫወቱ ክለቦች በመሥፈርትነት ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ፣ ክለቦች ዕድሜያቸው ከ13፣ ከ15 እና ከ18 ዓመት በታች የታዳጊ ወጣት ፕሮጀክቶችን መያዝ እንደሚጠበቅባቸው የሚያስገድድ ነው፡፡

የራሳቸው አልያም በአማራጭነት ለጨዋታ የሚጠቀሙበት ወይም የሚያስመዘግቡት ስታዲየም፣ በቢሮ ደረጃ የተሟላ ጽሕፈት ቤት፣ በየደረጃው ለያዟቸው ቡድኖች ለእያንዳንዱ የራሱ አሠልጣኝ፣ የቡድን መሪ፣ ምክትል አሠልጣኝ፣ የበረኛ አሠልጣኝ እንዲሁም በትክክለኛ የሒሳብ ባለሙያ የተረጋገጠ የፋይናንስ ሪፖርትና ቡድኖቹን በባለቤትነት የሚያስዳድራቸው አካል ሊኖር እንዲገባም የካፍ አዲሱ መመርያ ያስረዳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...