Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለዘመን መለወጫ ያልተለወጠው የኑሮ ውድነት

ለዘመን መለወጫ ያልተለወጠው የኑሮ ውድነት

ቀን:

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በድምቀት ከሚከበሩ ዓመታዊ ክብረ በዓሎች መካከል በሁሉም ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የአዲስ ዘመን መለወጫ ነው። አዲስ ዓመትን ከቤተሰብ እስከ ወዳጅ ዘመድ ተሰባስቦ ማክበር የተለመደ ነው። ዘመድ አዝማድ በዓሉን በጋራ የሚያከብረው ለቀኑ የሚሆኑ አልባሳትን፣ ምግብ እና መጠጦች ከወትሮው በተለየ በማዘጋጀት ነው።

የበዓልን ድባብ ከሚፈጥሩ ነገሮች መካከል ዋናው የበዓል ገበያ ነው፡፡ የበዓል ገበያዎች ደግሞ ከሻጭና ገዢ የቀንስ አትቀንስ ንትርክ ጀምሮ የዶሮና የበጉ ጩኸት፣ የቄጤማ፣ የኮባ፣ የጠጅ ሳርና የአሪቲ ሽታዎች በዓሉን ከማስታወስ አልፎ በቦታው ላለ የበዓሉን ድባብ ያደምቃሉ።

የዘንድሮው የዘመን መለወጫ ኢትዮጵያ በበርካታ ችግሮች ውስጥ ተጠፍንጋ ቢሆንም፣ ለመቀበል ሽር ጉድ ማለቷን ግን የቀጠለች ትመስላለች፡፡

እንደ ከዚህ ቀደሙ የተጋነነ የዘመን መለወጫ ሽርጉዱ ባይታይም፣ ሁሉም በአቅሙ ልክ፣ ቤቱንና ራሱን ለመቀየር ታች ላይ ሲል ይታያል፡፡ የ2015 ዓ.ም. ዘመን የሰላም፣ የእርቅና ኢኮኖሚው የተስተካከለ እንዲሆን ምኞት አለ፡፡

በዋናነነትም በሃይማኖትና ባህላዊ ክንውኖች በዓሉን ከሚያደምቁና ከሚያሳምሩት መካከል በጉልህ ይጠቀሳል፡፡ ባህላዊ ክንዋኔው ሁሉም በቤቱ የሚያደርገው የበግ፣ የአዲስ ዓመት መቀበያ የሚደረጉ የዋዜማ ግብይትን ለመጠየቅ ሪፖርተር በተለያዩ የገበያ ማዕከላትን ቅኝት አድርጓል፡፡

ሾላ ገበያ

ከገበያ ማዕከላት መካከል የካ ክፍለ ከተማ የሚገኘገኘው ሾላ ገበያ ተጠቃሽ ነው፡፡ በሾላ ገበያ የዶሮ፣ እንቁላል፣ ቅቤ፣ በግ፣ ፍየል፣ ከብት ሽንኩርትና መሰል የበዓል የሚያደምቁ ነገሮች ለገበያ ቀርበዋል፡፡

በዓልን በሽታ በማወድና ከሩቅ በጠረን ከሚጣሩ የምግብ ዓይነቶች ቅቤ ዋነኛው ነው፡፡ ድሮ ድሮ በግና ፍየል ይገዛበት የነበረውን ገንዘብ በአሁኑ ዘመን ቅቤ እየተሸመተበት እንደሚገኝ ለማየት ችለናል፡፡ በሾላ ገበያ ለጋ፣ መካከለኛና የበሰለ ቅቤ ለሽያጭ ቀርቧል፡፡ ለጋ 900፣ መካከለኛ 850 እና በሳል 800 ብር ለገበያተኞች ቀርቧል፡፡ የቅቤ ዋጋው ከትንሳዔ በዓል ጋር ሲነፃፀር አንድ ኪሎ 470 ብር መሸጡ የሚታወስ ሲሆን በዘንድሮ አዲስ ዓመት በእጥፍ መጨመሩን ያሳያል፡፡ የተወሰኑ ወራት ውስጥ በሚያስደንገጥ ሁኔታ እያሻቀበ የመጣው የቅቤ ዋጋ የገና በዓል የነበረው ገበያ ቢታይ እንኳን በኪሎ እስከ 280 ብር ድረስ መሸጡ ይታወሳል፡፡

ለበዓሉ ከሚያስፈልጉ መሠረታዊ ዓብዓቶች አንዱ ዶሮ ነው፡፡ ወ/ሮ ዓለም ሞላልኝ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በሾላ ገበያ የዶሮ ዋጋ እየጠየቁ አግኝተናቸዋል፡፡ ወ/ሮ ዓለም ስለ በዓል ገበያው ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የኑሮ ውድነት ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡ ለበዓል የተወሰነ የዋጋ ጭማሪ ቢኖረውም በዓልም ባይኖር የሚጨምር እንጂ የሚቀንስ ነገር እንደሌለ ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጦርነቱ፣ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ተከትሎ፣ በበርካታ ዕቃዎች ላይ ጭማሪ መኖሩን ወ/ሮ ዓለም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በነጋዴዎች አሻጥር ምክንያት የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ መኖሩንም የገለጹት መንግሥት አይቶ እንዳላየ መሆን የለበትም በማለት ነው፡፡

የዶሮ ገበያ ከ700 ብር በታች እንደሌለ የገለጹት ወ/ሮ ዓለም አቅም ለሌላቸው ከባድ ሊሆን እንደሚችል ይገልጻሉ፡፡ እንቁላል፣ ዶሮ፣ ቅቤ፣ በግ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ከዓምና ገበያ ጋር ሲነፃፀር ዋጋቸው መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

የዶሮ ዋጋ አነስተኛ የሚባለው 450 እስከ 500 ብር ጥሪ በሾላ ገበያ ይጠራል፡፡ መካከለኛ 550 እስከ 600 እና ትልቅ የሚባለው ከ650 እስከ 800 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በዚሁ ገበያ ከዶሮ በተጨማሪ በግ፣ ፍየል ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ በጎች የሚመጡት ከዱበር ወላይታ፣ ጊንጪ፣ አርባ ጉጉና ወሊሶ ናቸው፡፡

አነስተኛ በግ 4500 እስከ 5,000፣ መካከለኛ 5,500 እስከ 6,500 እና ትልቅ የሚባለው በግ ከ7,000 ብር ጀምሮ እስከ 10,000 ብር ለገበያ መቅረቡን አቶ ተስፋሁን ታደለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ዋጋው ከአምና ጭማሪ ማሳየቱን የገለጹት አቶ ተስፋሁን፣ የነዳጅ መናር ሌሎች ነገሮች ለዋጋው መጨመር ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሽንኩርት በኪሎ ከ40 ብር እስከ 50 ብር ሲሆን፣ ነጭ ሽንኩርት ከ160 ብር ጀምሮ እስከ 180 ብር ጀምሮ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ የዘይት ዋጋ ከወትሮው የዋጋ ጭማሪ ያላሳየ ሲሆን፣ ኦማር የሚባለው 1,050 ሌሎችም እንደ የደረጃቸው 980 ብር እና ከዚያ በታች እየተሸጡ ይገኛል፡፡

የዶሮ ዋጋ እንደ መጣባቸው አካባቢዎች የሚለያይ ሲሆን፣ የወላይታ ዋጋው ከፍ እንደሚል ነጋዴዎች ነግረውናል፡፡ የሐበሻ ዶሮ ከ600 ብርና ከዚያ በላይ በሾላ ገበያ እየተሸጠ ሲሆን፣ ድቅል ዶሮዎች ደግሞ 750 ብር ጀምሮ ከዚያ በላይ እየተሸጡ ይገኛል፡፡ እንቁላል ከቦታ ቦታ የሚለያይ ሲሆን ከ10.50 ብር ጀምሮ እስከ 12 ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሚገኝ የተለያዩ የእንቁላል አከፋፋዮችን ነግረውናል፡፡

ሳሪስ ገበያ

በሳሪስ ገበያና አካባቢው ደግሞ የበግ ዋጋ ትንሹ ከ5,000 ብር፣ መካከለኛ ከ6,500 ብር ጀምሮ ሲሆን፣ ትልቅ የሚባለው ከ8,000 ብር ጀምሮና ከዚያ በላይ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ የዶሮ ገበያው ደግሞ የሐበሻ ከ500 ብር፣ ድቅል ዶሮ ደግሞ ከ650 ብር ጀምሮ ትልቅ ዶሮ ከ700 ብርና ከዚያ በላይ እየተሸጠ እንደሚገኝ ሪፖርተር ገበያውን ቃኝቷል፡፡

ቅቤ በኪሎ ከ750 ጀምሮ እስከ 800 ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን፣ ሽንኩርት 35 ብር እስከ 45 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ታዝበናል፡፡ የፍየል ዋጋም በተመሳሳይ መልኩ ትንሽ የሚባለው ከ6,000 ብር ጀምሮ እስከ 11,000 እየተሸጠ እንደሚገኝ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በቄራ ገበያ ቀይ ሽንኩርት በኪሎ ከ45 እስከ 55 ብር ሲሆን፣ ነጭ ሽንኩርት ደግሞ ከ160 እስከ 170 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

እንቁላል ከ11 እስከ 12 ብር ሲሆን ቅቤ ደግሞ ከ700 እስከ 850 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በዘንድሮ የበዓል ዋዜማ የበዓል ግብይት ያልሆነው ቲማቲም በሾላ ገበያ 60፣ በሳሪስ ገበያ 70፣ በቄራ ገበያ ደግሞ በኪሎ 50 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

የ2014 ዘመን መለወጫ ገበያ ከ2015 ዓ.ም. ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ለአብነት ያህል በሾላ ገበያ አምና ቅቤ ሲሸጥ የነበረው ለጋ 500 ብር፣ መካከለኛ 460 እና በሳል 450 ብር ሲሸጥ እንደነበር ይታወሳል፡፡

2015ን ለመቀበል ጥቂት ቀናት በቀሩት ደግሞ ከ150 እና ከዚያ በላይ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በሌላ በኩል የዘይት ዋጋ አምና ሲሸጥ የነበረው ከ550 እስከ 620 ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ ከ980 እስከ 1,050 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

የበግ ዋጋ አምና በዚህ ሰሞን ትንሽ የሚባለው 2,800 እስከ 3,000፣ መካከለኛ 4,500 እስ 5,000 ብር ትልቅ የሚባለው 6,000 እስከ 8,000 ብር እና ከዚያ በላይ ተሸጧል፡፡

ከዘንድሮ የዘመን መለወጫ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ከታየባቸው መካከል በግ ዋነኛው ነው፡፡ የዋጋ ጭማሪ ብዙም ያልታየባቸው የበዓል ግብዓቶች መካከል ሽንኩርት ሲሆን ዓምና ከ40 ብር ጀምሮ ተሸጧል፡፡

ነጭ ሽንኩርት በኪሎ ከ90 ብር ጀምሮ እስከ 120 ብር በለዓምናው ዘመን መለወጫ የተሸጠ ሲሆን በዘንድሮ ደግሞ ከ160 እስከ 180 ብር በኪሎ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...