በወርኃ መስከረም መሬቷ በአደይ አበባ አሸብርቃ ስለምትታይና በተለይም ዕንቁ የመሰለ አበባ ስለምታወጣ መሬቷን ዕንቁጣጣሽ፣ ዕንቁ የመሰለ አበባ አስገኘሽ ለማለት ዕንቁጣጣሽ መባሏን የቅርስ ባለሙያው መምህር ዓለሙ ኃይሌ ይገልጻሉ፡፡ አያይዘው አቧራ፣ ቡላ የነበረው መሬት በዝናቡ ኃይል ለምልሞ ተመልከቱኝ፣ ተመልከቱኝ የምትል ያሸበረቀች፣ አበባ የተንቆጠቆጠች ሆነች የሚል ለዕንቁጣጣሽ ስያሜ መነሻ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ፡፡ ገጣሚና ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ በግጥሙ የመስከረም መባቻን እንዲህ ገልጿታል፡፡
ኢዮሃ! አበባ ፈነዳ
ፀሐይ ወጣ ጮራ።
ዝናም ዘንቦ አባራ።
ዛፍ አብቦ አፈራ።
ክረምት መጣ ሄደ
ዘመን ተወለደ።
ዓለም አዲስ ሆነ።