Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየሊጉ አክሲዮን ማኅበር በገንዘብ እጥረት በቪዲዮ የተደገፈ ዳኝነት ለመተግበር አልቻልኩም አለ

የሊጉ አክሲዮን ማኅበር በገንዘብ እጥረት በቪዲዮ የተደገፈ ዳኝነት ለመተግበር አልቻልኩም አለ

ቀን:

  • ዳኝነቱን ለመተግበር 25 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ2015 ውድድር ዓመት ከዳኝነት ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ፣ በቪዲዮ የተደገፈ ዳኝነት ለመስጠት ባጋጠመው የገንዘብ ችግር ምክንያት ቴክኖሎጂውን መተግበር እንደማይችል አስታወቀ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በዕድሳት ላይ የሚገኘውን አዲስ አበባ ስታዲየም ጨምሮ በተመረጡ አራት የክልል ስታዲየሞች የሚከናወን እንደሚሆንም ይፋ አድርጓል፡፡

አክሲዮን ማኅበሩ ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን በሐያት ሬጀንሲ ሆቴል አከናውኗል፡፡ ጉባዔው ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል፣ በቪዲዮ የተደገፈ የእግር ኳስ ዳኝነትን በዚህ ዓመት ለመተግበር የሚያስችለውን አሠራር መዘርጋት አንዱ ነበረ፡፡ ነገር ግን ቴክኖሎጂውን የሚያቀርበው ድርጅት፣ እንዲከፈለው የጠየቀው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ዘንድሮ ቴክኖሎጂውን ላለመጠቀም መወሰኑን የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አክሲዮን ማኅበሩ ቀደም ሲል ግልጽ ጨረታ በማውጣት ሁለት ድርጅቶች እንደቀረቡ፣ ይሁንና ከቀረቡት ድርጅቶች አሸናፊው ድርጅት ቴክኖሎጂውን ወደ መሬት ለማውረድ አክሲዮን ማኅበሩ 25 ሚሊዮን ብር እንዲከፍለው ስለመጠየቁ ጭምር ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም አክሲዮን ማኅበሩ በጉባዔው የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ከማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ጋር የተገናኙ አሠራሮችን ለማዘመን መምከሩም ተገልጿል፡፡ በኮቪድ ምክንያት ከስታዲየም የራቀውን ተመልካች ለመመለስ አክሲዮን ማኅበሩና ክለቦች የተቀናጀ ሥራ መሥራት እንደሚኖርባቸው ጉባዔው አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...