አምባሳደር ተፈራ ሻውል፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጰያ ጉዳይ በተደጋጋሚ እያሳየ ያለውን አቋም አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የተናገሩት፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃነት ምልክት ነች ያሉት አምሳደሩ፣ ‹‹አለማጎንበሳችንና አለመታዘዛችን ያማቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን እንደ ምንም ብሎ ማሸነፍ ማለት አፍሪካን በሙሉ ወደ አፋቸው ሥር እንዳስገቡ ነው የሚያምኑት፤ ይህ ደግሞ የማይደረግ ነው፤›› ሲሉም አክለውበታል፡፡