Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  [አብሮ የሚኖረው ወንድማቸው በተደጋጋሚ እየደወለ መሆኑን የተመለከቱት ክቡር ሚኒስትሩ በስተመጨረሻ የእጅ ስልካቸውን አንስተው ሃሎ አሉ]

  • ሃሎ… ስብሰባ ላይ ሆኜ ነው ያላነሳሁት …በሰላም ነው?
  • ሰላም ነው። ልንገርህ ብዬ ነው…
  • ምንድነው ምትነግረኝ? 
  • ዛሬ አልመጣም፣ እንዳትጠብቀኝ ልነግርህ ነው።
  • ምን ማለት ነው? ወደ አገር ቤት ልትመለስ ነው? 
  • እንደዚያ እንኳ አይደለም።
  • እና ምን ሆነህ ነው? 
  • አድራለሁ። 
  • ምን?
  • ማለቴ ሊያሳድሩኝ ነው። 
  • ማነው የሚያሳድርህ? የት ነው ያለኸው?
  • ፖሊስ ጣቢያ ነው። 
  • ምን አድርገህ ነው። የትኛው ፖሊስ ጣቢያ ነው? 
  • መታወቂያ እንደጠፋብኝ ላስመስክር ብዬ ጠዋት የሄድኩበት ጣቢያ ነው ያለሁት።
  • ምን አድርገህ ነው ከሰው ተጣላህ?
  • ኧረ በጭራሽ!
  • ምን ተፈጠረ ታዲያ?
  • አልያዝክም ተብዬ ነው። 
  • ምን?
  • የታደሰ መታወቂያ። 
  • ምን?
  • አዎ። እንደዚያ ነው።
  • የመጣሁት ላስመሰክር ነው ብለህ አታስረዳቸውም እንዴ?
  • አልኩኝ፣ ሞከርኩ።
  • እና…
  • አልሆነማ!
  • ምን ምላሽ ሰጡህ?
  • እስኪመረመር ድረስ ነው ያሉኝ።
  • እስኪመረመር ምን አሉ? 
  • እዚሁ እደር! 

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከባለቤታቸው ጋር ስለአገር ጉዳይ እያወጉ ነው]

  • እየሆነ ያለው ነገር ግራ አጋብቶኛል።
  • ምኑ ነው ግራ ያጋባሽ? 
  • የሰሜኑ ጦርነት ሁኔታ ሊገባኝ አልቻለም።
  • ለምን? 
  • አንደኛው ምክንያት መንግሥት ምንም ዓይነት መረጃ እየሰጠ ባለመሆኑ ነው። 
  • ሌላኛው ምክንያትስ? 
  • ሌላኛው ደግሞ ከሰሜኑ ኃይል እየወጣ ያለው ተከታታይ መረጃ ነው ግራ ያጋባኝ።
  • ከሰሜኑ ኃይል የወጣው መረጃ እንዴት ግራ አጋባሽ?
  • በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ወታደሮችን ደመሰስኩ ይሉና አፍታም ሳይቆዩ የሚቃረን መረጃ ያወጣሉ። 
  • ምን ብለው?
  • በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ተከፈተብን። ተከበብን ይላሉ።
  • እሱማ አንዱ የሚከተሉት የውጊያ ስልት ነው።
  • እንዴት?
  • ደመሰስን ሲሉ ደምሰስን ማለታቸው አይደለም።
  • እ? 
  • አለን ማለታቸው ነው።
  • ለማን ነው አለን የሚሉት?
  • ለምዕራባውያኑ ደጋፊዎቻቸው። 
  • ደመሰስን ካሉ በኋላ ተጠቃን የሚሉትስ ለምንድነው? 
  • ተጠቃን ሲሉ ተጠቃን ማለታቸው አይደለም። 
  • ምን ማለታቸው ነው ታዲያ?
  • ምነው ዝም አላችሁ ማለታቸው ነው።
  • ማንን?
  • ምዕራባዊያኑን። 
  • ምዕራባዊያኑ ምን እንዲያደርጉላቸው? 
  • በሰሜኑ ውጊያ የጦር ወንጀል ሳይፈጸም አይቀርም የሚል መግለጫ እንዲያወጡ ወይም …
  • ወይም ምን?
  • በሰብዓዊነት ላይ ጥቃት መፈጸሙን የሚያመላክቱ መረጃዎች እየደረሱን ብለው መግለጫ እንዲያወጡ ወይም…
  • ሌላ ምን?
  • የሰብዓዊ ዕርዳታ ካልገባ መቶ ሺሕ ሕዝብ በረሃብ ሊያልቅ ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሮብናል የሚል መግለጫ እንዲያወጡላቸው። 
  • ይህ ለእነሱ ምን ይጠቅማቸዋል? 
  • ለእነሱማ የጦርነቱ አካል ነው። 
  • እንዴት? 
  • ማዕቀብ እንዲጣል። ይህ ካልሆነላቸው ደግሞ ሌላ የሚታደጋቸው ነገር እንዲመጣ ሊሆን ይችላል።
  • ምን ሊመጣ ይችላል?
  • ዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ። 
  • አሜሪካ ግን በተደጋጋሚ ስለኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት መከበር መግለጫ እያወጣች ነው። 
  • እሱም የጦርነቱ አካል ነው። 
  • እንዴት? 
  • የዚህ ጦርነት መጨረሻ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን ይፈትናል ማለቷ ነው። በተጨማሪ ደግሞ…
  • በተጨማሪ ምን?
  • ይህ አደጋ ከመጣ እኔ የለሁበትም፣ ከደሙ ንፁህ ነኝ ማለቷ ነው። 
  • ታዲያ መንግሥት ይህንን እያወቀ ለምን ዝም አለ?
  • ከባለፈው ስህተቱ ትምህርት ወስዶ። 
  • ምን ተማረ? 
  • ዝምታ።
  • ዝምታ መፍትሔ ይሆናል እንዴ? 
  • ዝምታ ብቻውን አይደለም።
  • ሌላ ምን አለ? 
  • ምታ በዝምታ!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  በሰባት የመንግሥት ተቋማት ላይ ሰፊ የወንጀል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ

  በስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ተወስኗል ከ1.4 ቢሊዮን...

  ጎህ ቤቶች ባንክ ወደ ቤት ልማት ለመግባት ብሔራዊ ባንክን ፈቃድ ጠየቀ

  በስምንት ወራት ውስጥ 7.9 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታውቋል ኢትዮጵያ ውስጥ...

  ሒጂራ ባንክ የ143 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አስመዘገበ

  በኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ ባንክ አገልግሎት ለመስጠት ወደ...

  ወጋገን ባንክ ከገጠመው ቀውስ በማገገም በ2014 የሒሳብ ዓመት የተሻለ ትርፍ አገኘ

  ለሁለት ዓመታት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸው ከተስተጓጎለባቸው...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...

  ወጋገን ባንክ ከገጠመው ቀውስ በማገገም በ2014 የሒሳብ ዓመት የተሻለ ትርፍ አገኘ

  ለሁለት ዓመታት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸው ከተስተጓጎለባቸው...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው እርጅና የተጫጫናቸው አጎታቸውን ለመጠየቅ ቢሄዱም ሚኒስትሩ ራሳቸው ተጠያቂ ሆነዋል]

  ዛሬ እንዴት ትዝ አልኩህ ክቡር ሚኒስትር? ልትመዛት ያሰብካት ነገር አለች ማለት ነው? እንዴት? ክቡር ሚኒስትር ብለህ ጠራኸኛ?! ክቡር ሚኒስትር አይደለህም እንዴ? እንደዚያ ብለህ በጠራኸኝ ቁጥር አንድ ያልተዋጠለህን ነገር ታነሳለህ።...

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት። እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም...

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...