Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅአምስተኛው የታሪክ አጋጣሚ እንዳይባክን

አምስተኛው የታሪክ አጋጣሚ እንዳይባክን

ቀን:

የመጀመሪያው፣ አፄ ኃይለ ሥላሴ ራስ ተፈሪ በነበሩበት የ1920ዎቹ  አዕምሮና ብርሃንና ሰላም የተባሉት ጋዜጦች የነበሩበት ዘመን ነው። ጋዜጦቹን ዛሬ ተመልሶ የሚያገላብጣቸው አንባቢ ይካሄድ በነበረው ሕያው ውይይት ይመሰጣል። ራስ ተፈሪ ወደ አፄነት ባደረጉት ጉዞና ከ1928 የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሒደት ጋር በተያያዘ ተዳፍነው አበቁ።

ሁለተኛው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ከመቀላቀሏ በፊት በአስመራ የነበሩት ጋዜጦችና የዴሞክራሲ አየር ነበር። የኤርትራ መቀላቀል ሲፈጸም ጋዜጦቹ በአፄያዊው አዲስ ዘመን ሥርዓትና አያያዝ ገብተው አከተሙ። ሦስተኛው በ1960ዎቹ ማብቂያ ላይ በደርግ የተከፈቱት የመወያያ መድረኮች (የውይይት ክበቦችና ለአደባባይ ውይይት የተከፈቱት የመንግሥት ጋዜጦች ራዲዮና ቴሌቪዥን ….) ነበሩ። በሚያሳዝንና በሚያሳፍር መንገድ ተጨማሪ የጥላቻና የግጭት ማራመጃ መሣሪያዎች ጭምር ሆኑ። ደርጉ ይህንኑ አሳቦ ጠረቀማቸው። ይሁንና ደግሞ እንዲወያዩ የተጠሩት የወቅቱ ተዋናዮች በውል ሳይጠቀሙበት ያባከኑት አጋጣሚና ለመክሰሙ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱት ጥርቀማም እንደነበር ላለማስታወስ አይቻልም።

አራተኛው በ1997 ምርጫ ወቅት ሽው ያለው የዴሞክራሲ አየር ነበር። በአቶ መለስ ዜናዊ በሚመራው ኢሕአዴግና በወቅቱ ‹‹ቅንጅት›› በተባለው ቡድን ተዋናዮች የይዋጣልን ክንድ ተደቁሶ እንደ ሦስተኛው አጋጣሚ ተጠረቀመ። የዓብይ (ዶ/ር) አመራር የከፈተው የዴሞክራሲ ሽውታ በዚሁ አምስተኛው የታሪክ አጋጣሚ ይሆናል። የዛሬው የፖለቲካ መሪዎች ልሂቃንና ተዋናዮች ሊያባክኑት የማይገባቸው አምስተኛው የታሪክ አጋጣሚ ነው።

በመጨረሻም ደግሞ ግን ስንቱ የአፍሪካ መሪ የዴሞክራሲን ሰንደቅ ለስንት ጊዜ እያውለበለበ እንደመጣና ለስንት ጊዜ ሕዝብን አስጨብጭቦ ለስንት ጊዜ ከአምባገነንና ሥልጣነ-ገነን አገዛዞች ጫማ ሥር እንደደፈቀው ይታወቃል።…

  • አንዳርጋቸው አሰግድ ‹‹ቅን ፍላጎት እስካለ መንገድ አለ›› ክብሩቡክስ
   

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...