Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

“‹መቻቻል› የተሰኘው ቃል ሽምግልና ቢያሳምር ይመረጣል”

ትኩስ ፅሁፎች

አንድ ጥንታዊ ፈላስፋ ‹‹ጨቅጫቃ የሆነችውን ሚስት ታግሶ የሚኖር ባል ጊንጦችን በሚያጠምድ ሰው ይመስላል›› ብሏል፡፡ ‹‹ነዝናዛ ሚስትና በዝናም የሚያፈስ ቤት አንድ ናቸው›› ሲባልም ሰምተናል፡፡ መቼም ነገር በሴት ላይ እየጠረረ ሔደ እንጂ ወንዱ ‹‹ብፁዕ ወቅዱስ›› እንከንም የሌለበት ለመሆኑ ምስክርነት አንሰጥም፡፡ ‹‹የሰነፍ ባሏን ደካማነት ታግሳ የምትኖር ሚስት ብረት በተሸከመ እንጨት ትመስላለች፤ ሰነፍ ባልና የመቃ ምርኩዝ አንድ ናቸው›› ብንል ብያኔውን የተደላደለ ሳያደርገው የሚቀር አይመስልም፡፡

ሆኖም ‹‹አንዱ በአንዱ ሲስቅ ጀምበር ጥልቅ›› እንዳይሆን ነገር በምሳሌ ማበራከቱ ለትዳር የሚያበረክተው እምብዛም አስተዋጽኦ የለምና ‹‹መቻቻል›› የተሰኘው ቃል ሽምግልና ቢያሳምር ይመረጣል፡፡ ትዳር ዋዛ አይደለምና! የጓዳ ንትርክ በሦስት ጉልቻ ዙርያ ብቻ በአንዲት ጐጆ ተገድቦ አይቀርም፡፡ በአደባባይ ሕይወት ላይም ይህ ነው የማይባል ጫና ሊቆልል እንደሚበቃ የሥነ ጋብቻ መማክር ይናገራሉ፡፡

በዓለም ዙርያ ያሉ የሥነ ጋብቻ ጠበብት በመዛግብት ጥናቶቻቸው እንዳሰፈሩት፣ አንድ በሽያጭ ውክልና ሊቀጠር የሚሻ ግለሰብ ማመልከቻ ሲያስገባ ያ ቀጣሪ ድርጅት የአመልካቹን የሙያ ብቃት የሚፈትሸው ከትምህርት ደረጃውና ከሥራ ችሎታው ብቻ በመነሳት አይደለም፡፡ ይልቁንም ትዳሩ ያማረ፣ ጋብቻው የሰመረ መሆን አለመሆኑን ጨምሮ ይመረምራል፡፡ ‹‹ለምን?›› ቢባል ትዳሩ ያላማረ ጋብቻው ያልሰመረ ከሆነ ምናልባት ያን ክቡድ የሆነውን የኩባንያ ውክልና ተግባር በንቃት ሊያከናውን ይሳነው ይሆናል በማለት ነው፡፡

  • አሸናፊ ዘደቡብ አዲስ አበባ ‹‹ጋብቻና ሕይወት›› (1982)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች