Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየአስከፊው ድርቅ ሥጋት በአፍሪካ ቀንድ

የአስከፊው ድርቅ ሥጋት በአፍሪካ ቀንድ

ቀን:

የአፍሪካ ቀንድ፣ ድርቅ፣ ረሃብ፣ ተራድ የአስከፊው ድርቅ ሥጋት በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ቀንድ ከድርቅ አልፋታ ካለ ከአራት አሠርታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ድርቁም ወደ አስከፊነት እየተሸጋገረ ከሰው እስከ እንስሳት መልክዓ ምድሩን ጨምሮ ዋጋ እያስከፈለ ነው፡፡ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ኬንያን፣ ጂቡቲን የሚያካልለው የአፍሪካ ቀንድ ለድርቅ አደጋ ለመታደግ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ለጋሽ ተቋማትና አገሮች በየጊዜው ድጋፍ ከመስጠት አልተቆጠቡም፡፡ከሦስት ዓመት ወዲህ በተከታታይ በአካባቢው አገሮች በኢትዮጵያ ደቡብ ምሥራቅና ደቡብ፣ በሶማሊያና በሰሜን ምሥራቃዊ ኬንያ የዝናብ ወቅት ለተከታታይ ዓመታት መቅረቱ የዝናብ ዕጥረት መከሰቱ አስከፊው ድርቅ እንዲያንዣብብ አድርጎታል፡፡ ሪሊፍዌብ ኢንተርናሽናል እንደዘገበው፣ በአፍሪካ ቀንድ ከመጪው ጥቅምት እስከ ታኅሣሥ ወራት የዝናብ መጠኑ ዝቅተኛ ሊሆን እንደሚችል ተንብየዋል፡፡ ይህም በመሆኑ በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ማኅበረሰቦች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ከ1970ዎቹ አጋማሽ ወዲህ የከፋ ድርቅ ላጋጠመው የአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊው ዝናብ እንደቀደሙት ዓመታት ላይመጣ እንደሚችል የአየር ትንበያ ባለሙያዎች ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሶማሊያ በከፊል በሚቀጥሉት ወራት በቸነፈር ትመታለች›› ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማስጠንቀቁን የዘገበው ቪኦኤ፣ የተጎጂዎች ቁጥር ግምት ከአሥር ዓመታት በፊት ከነበረው የከፋ እንደሚሆን ይጠበቃል ብሏል። እ.ኤ.አ. በ2011 በተከሰተው በዚሁ ቸነፈር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕፃናትን ጨምሮ ሕይወት መቅጠፉን ተመልክቷል፡፡ኬር ኢንተርናሽናል ባሠራጨው መረጃ በሦስቱ አገሮች የሚገኙ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለአስከፊ የረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል፡፡ የረሃብ አደጋው በተለይ እናቶችና ሕፃናትን የበለጠ ማጥቃቱን የገለጸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በበኩሉ፣ በአሁኑ ወቅት በኬንያ 942 ሺሕ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናትና 135 ሺሕ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች በከፍተኛ የምግብ እጥረት በሽታ መጠቃታቸውን እንዲሁም አስቸኳይ ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸው አመልክቷል። የአሜሪካ የዓለም የልማት ተራድዖ ድርጅት እ.ኤ.አ. ከ2020 ጀምሮ 1.3 ቢሊዮን ዶላር መስጠቱ የተዘገበ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባዔ ላይ የተገኙት የአሜሪካ ፕሬዚንት ጆ ባይደን በተለያዩ አገሮች የተከሰተውን ረሃብ ለመቋቋም አሥር ቢሊዮን ዶላር እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸውን ቪኦኤ የዘገበ ሲሆን፣ ምን ያህሉ ለአፍሪካ ቀንድ እንደሚውል አለመታወቁንም ገልጿል፡፡ በምግብ ደኅንነትና ሥነ ምግብ ላይ የሚሠራው ዓለም አቀፋዊ ተቋም (ኤፍ.ኤስ.ኤን.ደብሊው.ጂ) ባወጣው የድርቅ ልዩ ዘገባ መሠረት ከ8.9 ሚሊዮን በላይ የአርብቶ አደር ቤተሰቦች ለምግብና ለኑሮ የሚተማመኑባቸው ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት ድርቁ ገድሎባቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ 3.5 ሚሊዮን፣ በኬንያ 2.4 ሚሊዮንና በሶማሊያ 3.5 ሚሊዮን የሚደርሱ ከብቶች በመሞታቸው ከእነሱ የሚገኘው 120 ሚሊዮን ሊትር ወተት እንዲታጣ ሆኗል። በክልሉ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 1.6 ሚሊዮን ሕፃናት በቀን አንድ ብርጭቆ ወተት ሳይኖራቸው መቅረታቸውን በምሕፃሩ ፋኦ ተብሎ የሚታወቀው የምግብና የእርሻ ድርጅት ገልጿል። አስከፊው ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች አርብቶ አደር ማኅበረሰቦች ላይ የህልውና ሥጋት ነው። ልምድ እንደሚያሳየው አንድ የአርብቶ አደር ቤተሰብ በድርቅ ምክንያት መንጋውን መልሶ ለመገንባት ቢያንስ አምስት ዓመታት ይወስዳል። ነገር ግን በዚህ ድርቅ ወቅት ብዙ ቤተሰቦች ከብቶቻቸውን በሙሉ በማጣታቸውና ድርቅ በአፍሪካ ቀንድ እየበዛና እየጠነከረ በመምጣቱ አንዳንዶች አርብቶ አደሩን አካባቢውን ለቀው ሊወጡ ይችላሉ።የዩክሬን ጦርነትን ጨምሮ በማክሮ ኢኮኖሚ ያሉት ተግዳሮቶች፣ የሰብል ምርት ከአማካይ በታች መሆንና በዓለም አቀፍ ገበያ የምግብና የነዳጅ ዋጋ መጨመር በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የምግብ ዋጋ እንዲንር አድርጎታል፡፡ በሶማሊያ በድርቅ በተከሰቱ አካባቢዎች የምግብ ዋጋ እ.ኤ.አ. በ2017 ድርቅ እና በ2011 በተከሰተው ረሃብ ከተመዘገበው ደረጃ በልጦ መገኘቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም የዋጋ ቁጥጥር አመልክቷል። በኢትዮጵያ ዓምና ከጥር እስከ ሰኔ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ የአገር ውስጥ የምግብ ፍጆታ ዋጋ ከ33 በመቶ በላይ ጨምሯል ሲልም ገልጿል። የዋጋ ንረቱ ቤተሰቦች መሠረታዊ ዕቃዎችን እንኳን መግዛት እንዳይችሉ በማድረጉ ለምግብና ሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎችን ለመግዛት ሀብት ንብረታቸውን እንዲሸጡ እያስገደዳቸው ነው።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...