Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን የሴቶች ሚና እስከ ምን?  

 ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን የሴቶች ሚና እስከ ምን?  

ቀን:

ሴቶችን በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በባለቤትነት ቢሠሩ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ሲገለጽ ይስተዋላል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃም ከመፈክርነት አልፎ ብዙ ዓለም አቀፍ ሕጎችን ተቀብለው ከሚያፀድቁት አገሮች ተርታ ኢትዮጵያ ትገኝበታለች፡፡

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የማኅበረሰብ ክፍል የሚሆኑ ሴቶች የተጠቃሚነት፣ የመብት፣ የባለቤትነትና የፍትሕ ጉዳይ አሁንም እንዳልተመለሱ ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዓለም አቀፍ ደረጃ  ሴቶች በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አጀንዳው መፅደቁ ይታወቃል፡፡

 የፀደቀውን አጀንዳ  ሴቶች በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ዋና ተዋናይ የማድረግ፣ የጦርነትና ግጭትን ቅድመ መከላከል እንዲሠሩ ሁኔታዎችን የማመቻቸት፣  የመፍትሔ ግብዓት ላይ ሐሳባቸው እንዲሰማ የሚደግፍ ነው፡፡

ሴቶች በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ በባለቤትነት እንዲሳተፉ የተባበሩት መንግሥታት ፀደቀውን አጀንዳ ኢትዮጵያ ከተቀበለች 22 ዓመታት አስቆጥራለች፡፡ 

ይሁን እንጂ አጀንዳው ሳይተገበር ቢቆይም፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት ርዕሰ ጉዳዩ እንዲነሳ ምክንያት  መሆኑ  የዘርፉ ተዋናዮች ሲገልጹ ይሰማል።

ምክር ቤቱ በዋናነት ጦርነትና  ግጭት ከመከሰቱ በፊት  የሚያሠጉ ነገሮችን  ሲታዩ ቅድመ የመከላከል ሥራ ሴቶች እንዲሠሩ የሚያበረታታ ነው።

በዋናነት  በግጭት ምክንያት  ሴቶች ለችግሮች ተጋላጭ  ስለሆኑ  ቅድመ መከላከል ላይና ችግሮች ተከስተው ሲገኙ ደግሞ ከለላ እንዲያገኙ የሚደግፍ ነው።

አጀንዳው ማኅበረሰቡ እንዲያውቀውና ሴቶችን የሚያነቁና ግንዛቤ የሚሰጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም በጋራ እንዲሠሩ ያመላክታል፡፡

ከእነዚህም  የሲቪል የማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከል የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሴቶች ማኅበር አንዱ ነው፡፡

ማኅበሩ ከኢንተርኒውስ ጋር በመተባበር የሰላምና ፀጥታ አጀንዳን በተመለከተ ለሴት ጋዜጠኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም  ሰሞኑን አካሂዷል፡፡

ማኅበሩ ‹‹በሰላም ግንባታና በግጭት አፈታት ላይ የሴቶች ሚና አዘጋገብ›› በሚል ርዕስ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም. መድረክ  አዘጋጅቶ ነበር፡፡

የሕግ ባለሙያና በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ እየሠሩ የሚገኙት ሳምራዊት ጣሰው እንደተናገሩት፣ ሴቶች በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮችን በባለቤትነት እንዲሠሩ ቢደረጉ ችግሮችን መፍታት ይቻላል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታና ደኅንነት ምክር ቤት ያፀደቀውን የሴቶች ሰላምና ደኅንነት ላይ የሚደነግገውን ሕግ ኢትዮጵያ ከሁለት አሠርታት በፊት ተቀብላ ብታፀድቅም፣ ተግባራዊ ሳይደረግ መቆየቱን ያስረዳሉ፡፡

ፖሊሲና ስትራቴጂ ተቀርፆለት ሳይተገበር መቆየቱን የሚናገሩት ሳምራዊት፣ በዚህም አንድን የማኅበረሰብ አካል ያገለለ አሠራር ጊዜውን ጠብቆ ግጭት መፍጠሩ እንደማይቀር ገልጸዋል፡፡

ሴቶች ግጭትን በማረጋጋት፣ ሰላምን በማምጣት ትልቅ ሚና ቢኖራቸውም፣ ቦታቸው ማግኘት ባለመቻላቸው ሳይፈጸም መቅረቱን ተናግረዋል፡፡

ለምሳሌነት ያነሱት በትግራይ ክልልና በፌዴራል መንግሥት የሚደረገው ድርድር ሲሆን፣ አሁንም የሴቶች ተሳትፎ አስፈላጊነቱ ወይም ግዴታነቱ ከግምት ያስገባ ውሳኔ እንዳልታየ ተናግረዋል፡፡

በሁለቱም ወገን የአደራዳሪ ቡድን አባላት የተገለጹ መሆኑን፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ሰብስቡ የተባዕቶች ነው ብለዋል፡፡ ይህም የሴቶችን ድምፅ ያፈነና ተገቢውን ቦታ መነፈጋቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡

ከውሳኔው ጀርባ የታየውም በማኅበራዊ፣ በፖለቲካና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ለሴቶች እኩል መድረክ ያለመሰጠቱን አስረድተዋል፡፡

ባለሙያዋ እንዳስረዱት፣ የተጀመሩ ብዙ ሥራዎች እንዳሉ፣ ሴቶች በሰላምና በፀጥታ ጉዳይ ላይ እንዲሳተፉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የትግበራ ማዕቀፍ አዘጋጅቷል፡፡

አሁንም  ሴቶች ሰላም ለማምጣት ትልቅ ግፊት ማድረግ እንዳለባቸውና ተባብረው ድምፃቸውን ማሰማት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

 በሚደረገው የሰላም ድርድር ሴቶችን ያላሳተፈና የማይስተካከል ከሆነ ሁከቱ እንደሚቀጥል ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የቦርድ አባል ወ/ሮ መልካም ሰው ሰለሞን በበኩላቸው፣ በሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ሴቶች ከተጎጂነት ባለፈ  በሰላም ውይይትና ድርድር ወቅት ተሳታፊ አልነበሩም፡፡

ሰላምን ለማምጣት፣ ለመወያየት የማኅበረሰቡ 50 በመቶ ሴቶች በመሆናቸው የግድ መሳተፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ 

በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ መድረክ ሴቶች ባለመብቃታቸው ግጭቶች ሲከሰቱ በግንባር ቀደምትነት ተጎጂ መሆናቸውን፣ ይህንን ለመፍታት እነሱን ከማብቃት በተጨማሪ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይን በማኅበረሰቡ ዘንድ ለማስረፅ  ሴቶች የግድ በባለቤትነት እንዲሠሩ መደረግ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...