Tuesday, March 5, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

 • በል ዳቦውን ባርከህ ቁረስልንና በዓሉን እናክብር፡፡
 • ጥሩ ወዲህ አምጪው…
 • በል መርቅ…
 • ከዓመት ዓመት ያድርሰን…
 • ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው?
 • ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ… አልሰማሽም እንዴ?
 • ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን ዋጋ አለው? በደንብ መርቅ እንጂ?
 • ሌላ ምን ብዬ ልመርቅ?
 • አገራችንን ሰላም ያድርግልን… ካለንበት ጦርነት ያውጣን… በል እንጂ?
 • ተይ …ተይ… እሱ ይቅር፡፡
 • እንዴ ለምን?
 • ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይመጣም፡፡
 • ኧረ ፖለቲካህን ተውና መርቀህ ዳቦውን ቁረስልን፡፡
 • አንቺው እኮ ነሽ አላስቆርስ ያልሽው፡፡
 • እኔ ደግሞ ምን አደግረኩ? ከመቀመጫዬ አልተነሳሁ፡፡
 • ካለሽበት ሆነሽ ጣልቃ እየገባሽ አይደለም እንዴ?
 • በል አሁን ጭቅጭቁን ተወውና ዳቦውን ቁረስንልን፡፡
 • መቆረሱ የት ይቀራል ብለሽ ነው… ይኸው…
 • ኧረ ተው… አታሳንሰው?
 • አሳነስኩት እንዴ?
 • አደቀቅከው እንጂ፡፡
 • ለሁሉም እንዲዳረስ ብዬ ነዋ፡፡
 • ኤዲያ… ፈርፍረህ ጨረሰው እኮ…
 • ዛሬ ምን ነክቶሻል…
 • ኤዲያ… ጨርሶ በቢላ የተቆረሰ አይመስልም እኮ?
 • እና በምን የተቆረሰ መሰለ?
 • በድሮን!

[ክቡር ሚኒስትሩ በእረፍት ቀናቸው ከአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ወዳጃቸው ጋር ፖለቲካዊ ጨዋታ ላይ ናቸው። ወዳጃቸው በኢሕአዴግና በእናንተ ፓርቲ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም እያለ እየተከራከራቸው ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር፣ እኛ ኢሕአዴግ አይደለንም በስማችን ጥሩን የምትሉት ነገር ይገርመኛል፡፡
 • ምኑ አስገረመህ? እውነት አይደለም እንዴ?
 • ለእኔ የተቀየረ ነገር የለም፣ ያው ናችሁ።
 • ሞቶ ከተቀበረ ድርጅት ጋር እንዴት ታመሳስለናለህ? ትክክል አይደለህም፡፡
 • እኔ እኮ ሞቶ መቀበሩን አልካድኩም።
 • ታዲያ ምንድነው የምትለው?
 • ወራሾች ናችሁ ነው የምለው።
 • እንዴት?
 • ከስም ለውጥ በስተቀር ሁሉ ነገራችሁ ተመሳሳይ ነው።
 • እስኪ ምናችን ነው የሚመሳሰለው?
 • ለምሳሌ ርዕዮተ ዓለማችሁ ከስም ለውጥ በስተቀር ተመሳሳይ ነው፣ እሱ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው ይላል፣ እናንተ ስሙን መደመር በሚል ቀይራችሁ አመጣችሁት።
 • አትሳሳት፣ መደመር እኛ የፈጠርነውና የእኛ ብቻ ነው።
 • እኔ ግን አልስማማም።
 • እስኪ ንገረኝ፣ መደመር የሚል ርዕዮ ተዓለም በዓለም ላይ ሰምተህ ታውቃለህ?
 • ስያሜውማ አዲስ ነው፣ ነገር ግን በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ ሁለቱም አንድ ናቸው።
 • እንዴት አንድ ሊሆኑ ይችላሉ?
 • አብዮታዊ ዴሞክራሲ መላ ማኅበረሰቡን አንድ ላይ በማነቃነቅ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ለውጥ አመጣለሁ ነው የሚለው።
 • ታዲያ?
 • እናንተም በመደመር ሁሉም ነገር ይለወጣል፣ መፍትሔ ያገኛል ነው የምትሉት፡፡
 • እንዲሁ ለማመሳሰል ፈልገህ እንጂ በጭራሽ አንድ አይደሉም።
 • አይ… ያው ናችሁ፣ አስፈላጊ ከሆነ ሌላ ምሳሌም ልጠቅስልህ እችላለሁ።
 • ጥቀስ።
 • ለምሳሌ ኢሕአዴግ የመስኖ ልማት የሚለውን እናንተ የበጋ ስንዴ ልማት በሚል ለወጥ አድርጋችሁ አመጣችሁት።
 • ኦኦ… ሌላስ የምታመሳስለው የለህም?
 • አለኝ… ካዳመጥከኝ መቀጠል እችላለሁ።
 • ኧረ ቀጥል… ቀጥል…
 • ለምሳሌ ሰሞኑን ያመጣችሁት አዲስ ነገር…
 • ምን…?
 • በፊት ኢሕአዴግ አንድ ነገር ይጀምርና የልማት ቱሩፋት ነው ይለን ነበር፡፡
 • እኛስ?
 • እናንተ ደግሞ እሱን ቀየር አድርጋችሁ ብቅ ብላችኋል።
 • ምን ብለን?
 • የሌማት ቱሩፋት፡፡
 • ልፋ ሲልህ ነው።
 • እንዴት ?
 • ቢያንስ አንድ የማያመሳስለን ነገር አለ፡፡
 • ምን?
 • እኛ ቅምጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሉንም።
 • ቅምጥ ማለት?
 • ስንፈልግ ብቻ የሚቃወሙን በጀት የምንቆርጥላቸው ፓርቲዎች ማለቴ ነው!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...

ምርጫ ቦርድ ፓርላማው ያፀደቀለትን 304 ሚሊዮን ብር አለማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ሰኔ 2016 ዓ.ም. በአራት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ ነው የሚደንቀው? የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ? በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን...

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...