Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ሥርዓት ባለመኖሩ ወደ ካንሰር ሳይቀየር ማከም እንዳልተቻለ ተገለጸ

የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ሥርዓት ባለመኖሩ ወደ ካንሰር ሳይቀየር ማከም እንዳልተቻለ ተገለጸ

ቀን:

የጡት ካንሰር በማኅበረሰቡ ውስጥ እየተሠራጨ እንደሚገኝና አገር አቀፍ ቅድመ የምርመራና የሕክምና አገልግሎት አለመኖሩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ተደራሽና የተጠናከረ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ሥርዓት እንዳልተዘረጋ፣ በሽታው ወደ ካንሰርነት ሳይቀየር ቀድሞ ለማከም አስቸጋሪ መሆኑን፣ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ‹‹ፓዮኔር ዲያግኖስቲክ ሴንተር›› ባዘጋጀው የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫና የልየታ ዘመቻ ላይ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ሕክምና ማዕከል ኃላፊ ኤዶም ሰይፉ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ‹‹እንደ አገር የጡት ካንሰር ሕክምና ወደ ካንሰርነት ከማደጉ በፊት በሽታውን የማግኘት ዕድላችን አነስተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም የተደራጀና የተጠናከረ የጡት ካንሰር ምርመራ በኢትዮጵያ ሥርዓት ያልተዘጋጀለት በመሆኑ ችግሩ የጎላ ሊሆን ችሏል፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሌሎች የሕመም ዓይነቶች የአሠራር፣ የአተገባበር ሥርዓትና አገልግሎቶች እንዳላቸው፣ ነገር ግን የጡት ካንሰር በሽታ ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡

አንድ ዓመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ‹‹አልስክሮኔል›› በሚባል ፕሮጀክት በቸርችል ጤና ጣቢያ ብቻ የጡትና የማኅፀን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በሥርዓት ደረጃ በተጠናከረ ሁኔታ ጅማሮን የሚያሳይ መሆኑን የገለጹት ኤዶም (ዶ/ር)፣ እስካሁን በጥሩ ሒደቶች ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

ፓዮኔር ዳያግኖስቲክ ሴንተር በበጎ ፈቃደኝነት ከመስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ጡት ካንሰር ልየታና የምርመራ ማድረግ መጀመሩን ያነሱት ኃላፊዋ፣ ቅድመ ደካሞች ከክፍያ ነፃ መደረጉን፣ ያለውን ችግር በተወሰነ መንገድ ይቀንሳል ብለዋል፡፡

የዓለም የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን ምክንያት በማድረግ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫና የቅድመ ካንሰር የልየታ ምርመራ ዘመቻ ከትናንት ከመስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ይሰጣል ተብሏል፡፡

የማዕከሉ ባለቤትና መሥራች አቶ ብሩክ ፈቃዱ እንደተናገሩት፣ አዲስ መሣሪያ በመጠቀም ከመስከረም 21 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 21 ድረስ ለአንድ ወር የሚቆይ ሙሉ ምርመራ በማዕከሉ ውስጥ በነፃ ይሰጣል፡፡

በዚህ የምርመራ ማሽን የሚደረግ የቅድመ ካንሰር ልየታ በ3ዲ ዕይታ በመታገዝ ካንሰሩ ሳይስፋፋና ሳይሠራጭ፣ እንዲሁም ምልክት ማሳየት ከመጀመሩ በፊት ሕመሙን በአጭሩ ታክመው መዳን እንዲችሉ ይጠቅማል ብለዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት ዳይሬክተር  መሠረት ዘለዓለም (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በአገራችን ኢትዮጵያ በአሳሳቢነቱ በሁለተኛ ደረጃ  በተቀመጠው የጡት ካንሰር ሕመም ምክንያት፣ በዓመት ከ40 ሺሕ በላይ ሴቶች  ሕይወታቸው እንደሚያልፍ ገልጸዋል፡፡

ዕድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ሴቶች ቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግን ልምድ ሊያደርጉ እንደሚገባና የነፃ ምርመራ ዕድል ሲገኝ መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡

የፓዮኔር ዲያግኖስቲክ ማዕከል አቅም ለሌላቸውና ለተመረጡ መሥሪያ ቤቶች በነፃ በመስጠት፣ እንዲሁም ለመንግሥት ሠራተኞች የ50 በመቶ ቅናሽ በማድረግ መጀመራቸውን የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፍሬገነት ጌታቸው ገልጸዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...