Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበዕድሳት ምክንያት የተዘጋው የአዲስ አበባ ስታዲየም በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል

በዕድሳት ምክንያት የተዘጋው የአዲስ አበባ ስታዲየም በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል

ቀን:

የአደይ አበባ ስታዲየም ግንባታ በሚፈለገው ልክ እየተከናወነ እንዳልሆነ ተገልጿል

ከስፖርታዊ ክንውኖች ባሻገር ሃይማኖታዊ በዓላትንና የተለያዩ ዝግጅቶችን በማስተናገድ ጭምር አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ለአዲስ አበባና አካባቢዋ በብቸኝነት ውበትና ድምቀት ሆኖ ስለመቆየቱም ይነገራል፡፡

በ1930ዎቹ መጨረሻ በቀድሞ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተገነባውና በንጉሠ ነገሥቱ ስም ይጠራ የነበረው የአዲስ አበባ ስታዲየም፣ በ1954፣ በ1960 እና በ1968 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተከናወነውን የአፍሪካ ዋንጫ አስተናግዷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የ1991 ዓ.ም. የአፍሪካ ወጣቶች እግር ኳስ ዋንጫ ያስተናገደ ሲሆን፣ በወቅቱ የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን በሻምፒዮናው አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ በአርጀንቲና አስተናጋጅነት በ1993 ዓ.ም. በተከናወነው የዓለም ወጣቶች እግር ኳስ ዋንጫ ላይ ተሳትፎ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ እንዲሁም ስታዲየሙ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ማስተናገዱ አይዘነጋም፡፡  

ይሁን እንጂ ስታዲየሙ፣ ከወቅቱ ጋር ሊያራምደው የሚችለውን ዕድሳት ባለማግኘቱ ከደረጃ በታች ነው በሚል፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከሦስት ዓመታት በፊት ባስተላለፈበት ዕገዳ ምክንያት ማናቸውንም አኅጉራዊም ይሁን ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ሳያስተናግድ ቆይቷል፡፡

ውሳኔው ከአዲስ አበባ ስታዲየም በተጨማሪ በባህር ዳር፣ በሐዋሳና በመቐለ ከተሞች በተሻለ የጥራት ደረጃ ተገንብተዋል ተብሎ ሲነገርላቸው የነበሩ ስታዲየሞችን ያካተተ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጎረቤት አገር ስታዲየሞችን መጠቀም ግዴታ ሆኖበት በስደት እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ላለፉት ሦስት ዓመታት ስፖርታዊ ክንውኖችን ማስተናገድ ሳይችል የቆየው የአዲስ አበባ ስታዲየም፣ አሁን ላይ ዘግይቶም ቢሆን ከክብር እንግዶች (ቪአይቪ) እና ከሚዲያ ክፍሎች በስተቀር ሌሎቹ፣ ካፍ ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት የማሻሻያ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የማሻሻያ ግንባታውን አስመልክቶ መግለጫ እንደሚሰጥ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ስታዲየሙን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማደስ በሰኔ 2014 ዓ.ም. ሚኒስቴሩ፣ ከተቋራጩ ጋር መስማማቱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የስታዲየሙ የዕድሳት ሥራ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን መነገሩ አይዘነጋም፡፡

ስታዲየሙ አሁን ላይ የመጫወቻ ሜዳው፣ የተጫዋቾች፣ የዳኞችና ኮሚሽነሮች መልበሻና መታጠቢያ ክፍሎች፣ የተመልካቾች መፀዳጃ ቤቶች (ለሁለቱም ፆታ)  ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የማሻሻያ ግንባታው ተጠናቋል፡፡ እንደ ምንጮቹ ከሆነ የቀረው የክብር እንግዶችና የሚዲያ ክፍሎች በዚህ ሳምንት ወይም በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት ይሆናሉ፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔ ዓለም አካባቢ በቻይናው ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ አማካይነት በመገንባት ላይ የሚገኘው የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም፣ የፕሮጀክቱ ምዕራፍ ሁለት ማጠናቀቂያ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑ ቢነገርም፣ ግንባታው በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት በሚፈለገው ልክ እየተከናወነ አለመሆኑ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡

ተቋራጩ ዓምና ከዓለም የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ የዋጋ ጭማሪ ማስተካከያ እንዲደረግለት ጥያቄ አቅርቦ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ አሁን ላይ የፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ ቆሟል እንዳይባል ካልሆነ በስተቀር፣ ግንባታው የወትሮ ዓይነት እንዳልሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኃላፊዎችን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...