Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየቀነኒሳ የለንደን አምስተኛ የማራቶን ተሳትፎና ለክብረ ወሰን የምትጠበቀው የዓለም ዘርፍ

የቀነኒሳ የለንደን አምስተኛ የማራቶን ተሳትፎና ለክብረ ወሰን የምትጠበቀው የዓለም ዘርፍ

ቀን:

ከኦሊምፒክ ጨዋታ ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዲሁም ከአኅጉራዊ ውድድሮች ሳይተናነስ እየደመቀ የመጣው የጎዳና ሩጫ አዳዲስ ክስተቶችን እያስመለከተ ይገኛል።

ቀድሞ አትሌቶች ሩጫን በቤት ውስጥ የመም ውድድሮች ያደርጉ የነበረውን ልምድ ትተው፣ በቀጥታ ፊታቸውን ወደ ጎዳና ውድድሮች እያዞሩ የመጡበት ወቅት ከሆነ ሰነባብቷል። በአትሌቲክሱ ስኬትን መጎናፀፍ የቻሉ በርካታ አትሌቶች መነሻቸውን በአጭርና በመካከለኛ ርቅት፣ በረዥም ርቀት በአምስትና በአሥር ሺሕ ሜትር ላይ ከተሳተፉ በኋላ መዳረሻቸው የጎዳና ሩጫ ነበር።

ሆኖም በተለይ በየዓመቱ በሚሰናዱት የግል የቤት ውስጥ ውድድር አዘጋጆች የረዥም ርቀቶችን ከቴሌቪዥን መብት ጋር ተያይዞ ቀስ በቀስ ከውድድር ወጪ ማድረጋቸውን ተከትሎና የጎዳና ሩጫ አቋራጭ የገንዘብ ማግኛ ምንጭ በመሆኑ የአትሌቶችን ቀልብ መግዛት አስችሎታል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ለ42ኛ ጊዜ ዛሬ እሑድ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚከናወነው የለንደን ማራቶን የምንጊዜም የረዥም ርቀት ፈርጡን ቀነኒሳ በቀለና ተስፋ የተጣለባት የግማሽ ማራቶን ንግሥቷ የዓለም ዘርፍ የኋላን ጨምሮ በማራቶን ፈጣን ሰዓት ያላቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለንደን ከትመዋል። በዛሬው የለንደን ማራቶን ውድድር ላይ የሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ የረዥም ርቀት  ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ ይገኝበታል።

እ.ኤ.አ. በ2019 የበርሊን ማራቶንን 2፡01፡41 በሆነ ሰዓት ከዓለም የማራቶን ሪከርድ ባለቤት ኢሉድ ኪፕቾጌ 2፡01፡39 በ2 ሰከንድ ብቻ ዘግይቶ በማጠናቀቅ የዓለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት በእጁ መያዝ መቻሉ ይታወሳል። ቀነኒሳ በ2020 የለንደን ማራቶን በጡንቻ ጉዳት ምክንያት ከውድድሩ ራሱን ማግለሉ የሚታወስ ነው። በ2014 በፓሪስ የማራቶን ተሳትፎ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቀነኒሳ ከ13 በላይ የማራቶን ውድድሮች ላይ ተሳትፏል።

ቀነኒሳ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ በለንደን ማራቶን የሚሳተፍ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በ2016፣ 2017፣ 2018 እና 2020 ዓ.ም. ተሳትፎ ነበር። በ2017 በለንደንን ማራቶን የተሳትፈው ቀነኒሳ 2፡05፡57 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። አትሌቱ በ2018 የለንደን ማራቶን 2፡08፡53 በመግባት ስድስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀበት ጊዜ ይታወሳል። በተደጋጋሚ በጉዳት ምክንያት ከውድድር እየራቀ የሚገኘው ቀነኒሳ፣ የዛሬው ውድድር ላይ ክብረ ወሰን ይሰብራል ተብሎ ባይገመትም በውድድሩን ግን ያሸንፋል የሚል ግምት ተቀምጧል።

የ40 ዓመቱ ቀነኒሳ የዘንድሮ የለንደን ማራቶን ተሳትፎ የመጨረሻው ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ቢነሳም፣ ጉዳት ካልፈተነው በመጪው ለንደን ማራቶን መሳተፉ አይቀርም የሚሉም አልጠፉም።

በዛሬው የለንደን ማራቶን ከሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚካፈሉ ሲሆን፣ በተለይ በሴቶች በግማሽ ማራቶንና በማራቶን ውጤታማነቷ የምትታወቀው የዓለም ዘርፍ የኋላ ከፍተኛ ግምት ካገኙ አትሌቶች መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። በመም ውድድሮች እምብዛም ያልገፋችበት የዓለም ዘርፍ፣ 11 የግማሽ ማራቶን ውድድሮች ላይ ተካፍላ፣ ስምንቱን በአንደኛነት ማጠናቀቅ ችላለች። በሦስት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድሮችንም በበላይነት ስታጠናቅቅ፣ ዘንድሮ በስፔን በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር 29:14 በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን በእጇ መጨበጥ ችላለች።

ከወራት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በጀርመን ሀምቡርግ ማራቶን የተካፈለችው የዓለም ዘርፍ፣ 2:17:23 በመግባት የብሔራዊና የቦታውን ክብረ ወሰን ጭምር ጨብጣ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ባለፈው ነሐሴ በሰሜን አየርላንድ አንትሪምኮስት ግማሽ ማራቶን 1:04:22 በአንደኝነት ማጠናቀቋን ተከትሎ፣ አሁን ያለችበት ወቅታዊ አቋም ለሁለተኛ ጊዜ በምትወዳደርበትን የለንደን ማራቶን በበላይነት ትወጣዋለች የሚል አስተያየት እየተሰጠ ይገኛል።

በሌላ በኩል ሦስተኛውን የዓለም የማራቶን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበው ብርሃኑ ለገሠ፣ የ2021 ለንደንን ማራቶን አሸናፊው ሲሳይ ለማ እንዲሁም ከሰባት በላይ የማራቶን ውድድር ላይ ተካፍላ ስድስቱን በአንደኛነት ማጠናቀቅ የቻለችው አሸቴ በከሬ በዛሬው የለንደን ማራቶን ከሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...