Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየዘላቂ ደስታ መሠረቶች

የዘላቂ ደስታ መሠረቶች

ቀን:

የመኖሪያ ክፍላቸው በሰከነ ድባብ የተሞላ ነው። በክፍሉ ውስጥ ዘርዘር ተደርገው የተቀመጡ ቁሳቁሶች ምቹና ቀለል ያሉ ናቸው። የዕቃዎቹ አቀማመጥ ለስለስ ካለው የግድግዳ ቀለም ጋር ተዋህዶ ክፍሉን ሰፋ አድርጎታል። መጋረጃውን ዘልቆ የሚገባው ነፋሻ አየር የሆነ ዓይነት ማራኪ ጠረን ያዘለ ይመስላል። ዳላይ ላማው ከተለመደው መቀመጫቸው ላይ በፍፁም እርጋታ ተቀምጠዋል። ደስተኝነትን ርዕስ አድርገን በመወያየት ላይ ነበርን።

‹‹ደስታን በመሻት ውስጣዊ ጉዞ ውስጥ መታለፍ ያለባቸው የተለያዩ ደረጃዎች አሉ።›› በማለት አስተምህሯቸውን ጀመሩ ‹‹በቡዲዝም መንፈሳዊ ፍልስፍና ውስጥ ፍፁማዊ ደስታ ምሉዕ ይሆን ዘንድ አራት ደረጃዎች በመሠረታዊነት መታለፍ እንዳለባቸው ይታመናል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎች ዓለማዊውን ሀብትና ዓለማዊውን እርካታ ማወቅ ነው። በእነዚህ ደረጃዎች ላይ ተመሥርቶ መንፈሳዊነትን የመሻት ለውጥ ይከተላል። በቡዲዝም ፍልስፍና ደስታን መሻት የመጨረሻው እርከን ፍፁማዊውን ተገልጾና አብርሆ መሻት ነው። እነዚህ አራት ደረጃዎች ተሟልተው ሲገኙ ከስቃይ ነፃ የሆነ ምሉዕ ደስታ ይፈጠራል።››

 ዳላይ ላማው ንግግራቸውን ገታ አድርገው ራሳቸውን አደላደሉና ሻያቸውን በእርጋታ ተጎነጩ። ‹‹…ሆኖም ለጊዜው ውስብስብ የሆኑትን መንፈሳዊ ጉዳዮች ወደ ጎን አድርገን ደስተኝነትን በጥልቀት ስናጤን በደስታ የተሞላ ሕይወት ለመምራት የሚያስፈልጉ መሠረታዊ አውታሮች እንዳሉ እንረዳለን።

‹‹መልካም ጤንነት በደስታ የተሞላ ሕይወት ለመምራት ከሚያስፈልጉ ነገሮች ውስጥ የመጀመሪያው ነው። ከዚህ በተጨማሪም መሠረታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያስችል ሀብትና ቁሳቁስም ያስፈልጋል። አወንታዊ የሆነ ማኅበራዊ ሕይወትና የእርስ በርስ ግንኙነትም በደስታ የተሞላ ሕይወት ለመምራት የሚያስፈልግ ሌላኛው መሠረት ነው።››

‹‹በርግጥ እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ቅድመ ሁኔታዎች አስፈላጊ የሕይወት መሠረቶች እንደሆኑ እሙን ቢሆንም፣ እነዚህን እሴቶች በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋልና የተሟላ ሕይወት ለመምራት ወሳኙ ነገር አዕምሮ ወይም ውስጣዊ አመለካከት ነው።››
‹‹ሀብት፣ ቁሳቁስ፣ ዝናና ሞያዊ ስኬት በእጅጉ አስፈላጊ  የሕይወት ገጽታዎች ቢሆኑም፣ ትክክለኛው የሕይወት አመለካከትና የማመዛዘን አቅም ከሌለ እንደ ውድ ሀብት የምንቆጥራቸው እሴቶች ሁሉ ዋጋ ቢስ የሕይወት ገፀ በረከቶች ይሆናሉ።››
‹‹ሁሉም ሰው እንደሚያውቀው የዚህ ዘመን ማኅበረሰብ ከመቼውም ጊዜ በላቀ በሀብትና በቴክኖሎጂ የናጠጠ ማኅበረሰብ ነው። በማኅበረሰባችን ውስጥ የሚፈጠሩ ሀብታሞች ታይቶ በማያውቅ መልኩ እየተበራከቱ ነው። ሆኖም በዚህ ሀብታም ማኅበረሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ ደስታ ቢስ ባለፀጋዎች ቁጥርም በአስደንጋጭ መልኩ እያሻቀበ ይገኛል። በስኬት ከተሞላው የታይታ ሕይወታቸው ሥር አሳዛኝ የብስጭትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት በሚፈጥር ብሎም ለከባድ የመጠጥና የአደንዛዥ ዕፅ ሱሶች በሚዳርግ የአዕምሮ ሁከት የሚሰቃዩ ግለሰቦች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ከዚህም ከከፋ በዚህ የአዕምሮ ሁከት ተሰላችተው ሕይወታቸውን የሚያጠፉ ግለሰቦች ቁጥር ከዕለት ዕለት እየተበራከተ ይገኛል።››

ዳላይ ላማው ንግግራቸው አቋርጠው ለተወሰኑ ደቂቃዎች ትክ ብለው ሲመለከቱኝ ቆዩና ሐሳባቸውን እንዲህ ሲሉ አጠናቀቁ ‹‹አእምሮን መግራት እስካልቻልክ ድረስ ማንኛውንም ዓይነት ውጫዊ ፀጋ ብትጎናፀፍ ደስታ ርቆ ከተቀመጠ መና ይሆንብሃል። አእምሮህን ገርተህ ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት በውስጥህ ለማስረፅ ከቻልክ ዓለማዊውን ሀብት ቢርቅህ እንኳ የደስተኝነት በር ክፍት እንደሆነ ይጠብቅሀል።››

  • የደስታ ጎዳና አዕምሮን ማሠልጠን የቡድሂዝም የሕይወት ፍልስፍና

ትርጉም በዳኜ መላኩ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...