Tuesday, January 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጃፓን መንግሥት አሥር ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችን ሊለግስ ነው

የጃፓን መንግሥት አሥር ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችን ሊለግስ ነው

ቀን:

ድጋፍ የሚሹ ተብለው በተለዩ በአፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች የእናቶችንና የሕፃናትን ጤና ለማሻሻል የሚያግዙ የተሟላ የሕክምና ቁሳቁስ ያላቸው አሥር ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችን ለመለገስ የሚያስችል ስምምነት የጃፓን መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተፈራረመ፡፡

3.5 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡት እነዚሁ ክሊኒኮች ከሚይዟቸው ቁሳቁሶች መካከል፣ አልትራሳውንድና ኤሌክትሮ ካርዲዮግራፍን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ የሕክምና መሣሪያዎች ይገኙበታል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር ስብሰባ አዳራሽ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ስምምነቱን በኢትዮጵያ ወገን ሆነው የፈረሙት የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሪት ሰመሬታ ሰዋስው ሲሆኑ፣ በጃፓን መንግሥት በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሚስዝ ኢቶ ታካኦ ናቸው፡፡

በሥነ ሥርዓቱም ላይ የጃፓን አምባሳደር ይህ ዓይነቱ ድጋፍ የእናቶችንና የሕፃናቱን ጤና ከማሻሻሉ ባሻገር የሚሞቱ እናቶችንና ሕፃናትን ቁጥር እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያና ጃፓን ከ1970ዎቹ ጀምሮ የኢኮኖሚ አጋርነታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፤›› ያሉት ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሪት ሰመሬታ ሰዋስው ናቸው፡፡ በተለይም በመሠረተ ልማት፣ በግብርና ምርታማነት፣ በሰው ሀብት ልማትና በግሉ ዘርፍ ዕድገት ዙሪያ ትኩረት አድርገው እየሠሩ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡

እንደ ሚኒስትር ደኤታዋ አነጋገር፣ ባለፉት ሁለት አሠርታት የእናቶችንና የሕፃናትን ሞት ለመቀነስ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እየሠራች ነው፡፡ ይሁን እንጂ ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ ለማድረግ ብዙ ይቀራል፡፡

የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በድርቅና በግጭቶች ምክንያት ለተቸገሩ ማኅበረሰቦች እየተሰጡ ያሉ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ እንዲቀጥሉ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ለተግባራዊነቱም የጤና ባለሙያዎችን ያካተቱ ተንቀሳቃሽ ቡድኖችን ግጭቶች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች በማሰማራት የሕይወት አድን ሥራ መከናወኑንና በእንቅስቃሴው የአጋር ድርጅቶች ዕገዛና ትብብር ለሥራው ስኬት አስተዋጽኦ ማበርከቱን አውስተዋል፡፡

የአገሪቱ የስትራቴጂክ ዕቅድ አካል የሆነውን፣ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ፍትሐዊነትን የተላበሰ አገልግሎት ለመስጠት አስቸጋሪ ለሆኑ አካባቢዎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ አሥር ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችን የጃፓን መንግሥት ለመለገስ መስማማቱ ምሥጋና ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ሊያ፣ ድጋፉ ለነፍሰ ጡርና ለሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ለሕፃናት አገልግሎት እንደሚውልም አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነው አገር አቀፍ ፍትሐዊ የጤና ተደራሽነት ዙሪያ ላይ ያተኮረ የዳሰሳ ጥናት ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት እንደሚካሄድ ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር ጥናቱን በሁሉም አካባቢዎች የሚያካሂደው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሲሆን፣ ሥራውም የሚከናወነው በተቀመጠው ደረጃ መሠረት መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...