Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየፓን አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ አዲስ በተከፈተው የሳይንስ ሙዚየም ተጀመረ

የፓን አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ አዲስ በተከፈተው የሳይንስ ሙዚየም ተጀመረ

ቀን:

  • በ6.78 ሔክታር ላይ የተገነባው የሳይንስ ሙዚየም ተከፈተ

ለኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነውና ለሁት ቀናት የሚካሄደው አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንሰ ኮንፈረንስ (ፓን አፍሪካ 2022)፣ አዲስ በተገነባው የሳይንስ ሙዚየም ማክሰኞ መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡

አፍሪካን ማብቃት ‹‹Empowering Africa›› በሚል መሪ ቃል የተከፈተው ፓን አፍሪካን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ዋና ዓላማው፣ ተመራማሪዎች፣ ተወዳዳሪ ሳይንቲስቶች፣ መሐንዲሶችና ነጋዴዎችን ማቀራረብና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በኢንዱስትሪዎች፣ በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ ውሳኔ ሰጪ አካላት፣ ተቀራራርበው የሚወያዩበት መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ በኮንፈረንሱ ጥሩ አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች በአኅጉር ደረጃ ውይይት እንደሚደረግባቸውም አክሏል፡፡

ኮንፈረንሱ በአፍሪካ ዘላቂ ልማት በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣ በጤና፣ በፋይናንስ፣ በአገልግሎት፣ በአካባቢያዊ መረጃ፣ በማኑፋክቸሪንግና በሌሎችም የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ የሚያስችል መድረክ እንደሚፈጥርም ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኮንፈረንሱን የከፈቱትና በ6.78 ሔክታር ቦታ ላይ የተገነባውን የሳይንስ ሙዚየም መርቀው የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ‹‹የቴክኖሎጂ ዕድገት ለሰው ልጅ ትልቅ ተግዳሮት የሆኑበትን ነገሮች በቀላሉ እንዲሠራ ያደርጉታል፡፡ ኢትዮጵያም ጋራ ብልፅግና ለማምጣት ሁሉን አቀፍ የለውጥ አብዮት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ከኢኮኖሚ አዙሪት ውስጥ ለመውጣት፣ ዕድገትን አፋጥኖ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ኢትዮጵያም ከሁለት ዓመታት በፊት ከሥጋት ነፃ የሆነ የዳታ ሽግግር የሚደረግበት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አቋቁማ ውጤታማ ሥራ በመሥራት ላይ ናት፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ምንም ጥርጥር የለኝም፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እየሠራነውና እያስመዘገብን ያለው ውጤት፣ ለሌሎች አፍሪካ አገሮች ሞዴል ይሆናል፤›› በማለት፣ በሁለት ዓመታት ውስጥ የተገኘውን ውጤት አሞካሽተዋል፡፡

ፓን አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ሁሉም የአፍሪካ አገሮች ለመማማር፣ ለመተባባርና ለመገናኘት የሚጠቀሙበት መድረክ እንደሚሆንና ለአፍሪካ ዕድገትና ብልፅግና ወሳኝ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኃላፊ መሐመድ አኩዌቲ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በክብ ቅርፅ በ6.78 ሔክታር ቦታ ላይ የተገነባውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በዕለቱ ተመርቆ ተከፈተው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሁለት ግዙፍ ሕንፃዎችን የያዘ ሲሆን፣ 132 ሜትር ስፋት እንዳለው የተገለጸው፣ ትልቁ ሕንፃ በ15 ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መሆኑም ተነግሯል፡፡ የሕንፃው የመጨረሻ ጣሪያ ሳር የተተከለበት፣ አዲስ አበባን በተወሰነ ገጽታ ለማየት የሚያስችል አረንጓዴ ሥፍራ ያለው ነው፡፡

በሙዚየሙ ውስጥ ቋሚና ጊዜያዊ ዓውደ ርዕይ ማሳያዎች ያሉት ሲሆን፣ ከፀሐይ ብርሃን፣ የኤሌክትክ ኃይል ማግኘት የሚያስችሉ ሶላር ፓናሎች ተገጥመውለታል፡፡

በሙዚየሙ አጠገብ በጉልላት (ዶም) የተሠራ የአምፊ ቴአትር ማሳያም ተገንብቷል፡፡ ከኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ድርጅት ከፍ ብሎ ከታላቁ ቤተ መንግሥት በስተግራ ከሸራተን አዲስ ሆቴል አጥር አንስቶ የተካለለው የሳይንስ ሙዚየም፣ ከሥነ ሕንፃ ውበቱ በተጨማሪ፣ ዙሪያውን የተሠሩ መንገዶችና የተተከሉ የተለያዩ ዛፎች፣ አበባዎችና የሳር ተክሎች ልዩ ውበት ሰጥተውታል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...