ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ‹‹በብሔራዊ ሙዚየም›› በተካሄደው የቅርሶች ዓውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ የተናገሩት፡፡ ፕሬዚዳንቷ አገሪቷ ያላትን የቅርስ ሀብት ዓይነት፣ ስብጥርና ክምችት የሚመጥን ሙዚየም መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተውበታል፡፡ የሚገነባው ሙዚየምም በቅርስ ጥናትና ጥበቃ የስብስብ ክፍል የሚገኙ ዘመን ያስቆጠሩ የአርኪዮሎጂ ግኝት ስብስቦችን ለመጠበቅ፣ ለማኅበረሰቡ ለማሳወቅና ለማስጎብኘት ይረዳልም ብለዋል፡፡