Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየካላዘር ሕሙማንን ተስፋ የፈነጠቀው አዲሱ ሕክምና

የካላዘር ሕሙማንን ተስፋ የፈነጠቀው አዲሱ ሕክምና

ቀን:

ካላዘር ወይም ቁንጭር ይሉታል፡፡ በሳይንሳዊ ስሙ ‹‹ቬሴራል ሊስማናሊስ›› የሚባለው ይህ  በሽታ በተለይ አፍንጫን በማቁሰል የበሽታው ተጠቂዎች ከሕመማቸው በላይ እንዲገለሉና ሠርተው እንዳይኖሩ ምክንያት ሆኗል፡፡

ከተዘነጉ የሐሩር በሽታዎች የሚመደበው ካላዘር፣ ከወባ ቀጥሎ ገዳይ የሆነ በሽታም ነው፡፡ በሽታው በወቅቱ ካልታከመ ለከፍተኛ ጉዳት ይዳርጋል፡፡

በዓለም በየዓመቱ በበሽታው ከሚያዙ ሰዎች ከ50 ሺሕ እስከ 90 ሺሕ ያህሉ ውስጥ የምሥራቅ አፍሪካዎቹ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ዑጋንዳ ከፍተኛውን የሕሙማን ቁጥር እንደሚይዙ በተለያዩ ጊዜያት በዘርፉ ላይ የተሠሩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

- Advertisement -

ችግሩን ለመቅረፍ በዓለም ጤና ድርጅት መመርያ መሠረት በተለያዩ የጤናው ዘርፍ አካላት የተለያዩ ሕክምናው ላይ ያተኮሩ ጥናቶችና ምርምሮች ተሠርተዋል፡፡ ከእነዚህም አንዱ ትኩረት በተነፈጉ በሽታዎች ዙሪያ የሚሠራው ዲኤንዲ ኢንሺዬቲቭና ተባባሪዎቹ ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ያለውን ችግር መሠረት አድርገው በሠሩት ምርምር መሠረት፣ ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረጉት አዲሱ የተቀናጀ የካላዛር በሽታ ሕክምና ይገኝበታል፡፡

‹‹ክሊኒካል ኢንፊክሺየስ ዲዚዝ›› ለኅትመት ባበቃው ጥናቱ አዲሱ የካላዘር ሕክምና ከዚህ ቀደም ሲሰጥ የነበረውን ሕክምና የሚያሻሽል ውጤታማ እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳቱ አነስተኛ ነው፡፡

በሱዳን በኩል ለተካሄደው ጥናት ዋና ተመራማሪ የሆኑት የካርቱም ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቻንስለር አህመድ ሙሳ (ፕሮፌሰር) እንደገለጹት፣ በአዲሱ የተቀናጀ የካላዘር ሕክምና በምሥራቅ አፍሪካ በበሽታው የሚጠቁ ሕሙማንን ከመታደጉም በላይ ስቃይንና ከባባድ ክትባቶችን ያስቀራል፡፡

በተጎሳቆሉ፣ ደረቃማና ከፊል ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን፣ በተለይም ከ15 ዓመት በታች ያሉ ታዳጊ ሕፃናትን የሚያጠቃውን ካላዛር ለማከም እስካሁን የተሄደበት ነባሩ ሕክምና፣ ሕሙማን ለበርካታ ቀናት በሆስፒታል እንዲቆዩ፣ ከሥራና ከትምህርት እንዲስተጓጎሉ ሲያደርግ መቆየቱን ሙሳ (ፕሮፌሰር) አስታውሰው፣ አዲሱ ሕክምና የነባሩ ችግሮችን ያስቀራል ብለዋል፡፡

ከቀደመው ሕክምና ሲነፃፀር የሆስፒታል ቆይታን 18 በመቶ እንደሚቀንስና ውጤታማነቱም 91 በመቶ እንደሆነ ይፋ የተደረገው የተቀናጀ የካላዘር ሕክምና ዕውን ለማድረግ ጥናቱ የተሠራው በኬንያ፣ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በዑጋንዳ ነው፡፡

በአፍሪ ካዲያ ኮንሰርትየም የተሠራው ጥናትም እ.ኤ.አ. በ2017 የተጀመረው ክሊኒካዊ ጥናት አካል ሲሆን፣ በውጤቱም መሠረት አዲሱ ሕክምና ለአብዛኞቹ የካላዘር ሕሙማን ሕፃናት ውጤታማ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያና በሱዳን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የበሽታው የማገርሸት አቅምም በአራት በመቶ ይቀንሳል፡፡

በክሊኒካል ኢንፌክሺየስ ዲዚዝ ዘገባ መሠረት፣ አዲሱ የካላዛር ሕክምና በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሠራ ነው፡፡

የኬንያ ጤና ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ፕትሪክ አምት (ዶ/ር) እንደሚሉትም፣ እ.ኤ.አ. በ2025 በካላዛር ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችን በ60 በመቶ ለመቀነስ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት አዲሱ ሕክምና ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡

ምርምሩም በመርፌ የሚሰጡ ሕክምናዎችን ሙሉ ለሙሉ በሚቀርበትና በአፍ ብቻ በሚወሰዱ መድኃኒቶች በሚተካበት ዙሪያ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ከዚህ ቀደም በተሠራ ምርምር የኤችአይቪና የካላዘር ጥምር ሕመም ያለባቸው ሰዎች የተሻለ መድኃኒት ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...