Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየውጭ አገር ጉዞን ያስቀራል የተባለው የስትሮክና የስፓይን ማዕከል

የውጭ አገር ጉዞን ያስቀራል የተባለው የስትሮክና የስፓይን ማዕከል

ቀን:

ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች አንዱ የሆነው ስትሮክ፣ በአገር ውስጥ የሚያክመው አክሶን የስትሮክና የስፓይን ማዕከል አገልግሎት መሰጠት ጀመረ፡፡

ማዕከሉ ከ2.5 እስከ ሦስት ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደተደረገበት፣ ለአንጎል ቀዶ ሕክምና የሚውለው መሣሪያ ብቻ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንደተገዛ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ.ም. የማዕከሉ አገልግሎት ማስጀመርያ ላይ ተገልጿል፡፡

የአክሶን ስትሮክና ስፓይን ማዕከል አጋር መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወንደወሰን ገብረ አማኑኤል (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ማዕከሉ ባለፉት ስድስትና ሰባት ወራት ውስጥ የድንገተኛ ክፍል፣ የቋንቋ ቴራፒዎችን፣ የአካል ቴራፒዎችንና ሌሎች ባለሙያዎችን ሲያሠለጥን ቆይቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በኢትዮጵያ ስትሮክ፣ ካንሰርና ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እየተስፋፉ መሆኑን የገለጹት ወንደወሰን (ዶ/ር)፣ በወባ፣ ቲቢና ኤችአይቪ በሽታዎች ከሚሞቱት ይልቅ በስትሮክ የሚሞቱት ቁጥር እንደሚያሻቅብ ተናግረዋል፡፡

ከ50 እስከ 70 ዓመት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ከሚገድሉ በሽታዎች ውስጥ ስትሮክ የሚጠቀስ መሆኑን፣ በሽታውን መከላከልና ማከም እንደሚገባም ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያለች አገር በመሆኗ በስትሮክ የሚመጣውን ሞት 80 በመቶ በመከላከል መቀነስ እንደሚቻልም አስረድተዋል፡፡

በስትሮክ በሽታ የተያዘ ሰው ውጤታማ ሕክምና እንዲደረግለት፣ ሥር ሳይሰድ ወደ ሕክምና መሄድ ብቻ መሆኑን ወንድወሰን (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በሕክምና አነጋገር ‹‹ፈጠን›› የሚለው ቃል በዝርዝር ሲቀመጥ ‹‹ፈ›› ፈገግታ ሲበላሽ፣ ‹‹ጠ›› ጥንካሬ ሲዳከምና ‹‹ን›› ንግግር ሲበላሽ በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ እንደሚገባ የሚያሳዩ መልዕክቶች ናቸው ብለዋል፡፡

ከሦስቱ አንዱ ካለው ስትሮክ የመጠቃት ዕድሉ 72 በመቶ እንደሆነ፣ ሁለቱ ከሆነ ደግሞ ሥር መስደዱን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ትኩረት መደረግ ያለበት ቅድመ መከላከል ላይ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ወደ ኬንያና ህንድ አገሮች ቢሄዱ በማዕከሉ ከሚያወጡት በአሥር እጥፍ እንደሚበልጥ ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የ‹‹አክሶን ስትሮክ›› እና ‹‹ስፓይን›› ማዕከል መከፈቱ በኢትዮጵያ የስትሮክ ሕክምናን አንድ ምዕራፍ ወደ ፊት የሚወስድ ነው ብለዋል፡፡

የጤናው ዘርፍ በርካታ መሻሻሎች እያሳየ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ብዙ የሚቀሩ ሥራዎችን ወደ ፊት መሥራት ይጠበቃል ብለዋል። 

ላለፋት ዓመታት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያስከትሉት ሞት እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ ችግሩን ለመቅረፍና ከመከላከል ጎን ለጎን የስፔሻሊቲ ሕክምና አገልግሎት ለማስፋፋት የአሥር ዓመት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ እየተተገበረ መሆኑንም አስረድተዋል።

የአክሶል ስትሮክና ስፓይን ማዕከል አጋር መሥራች አከዛ ጠአመ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የአክሶል ስትሮክና ስፓይን ማዕከል በኢትዮጵያ አዲስ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን፣  ለአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት አገሮች የሚመጡትም የሚታከሙበት ተቋም ነው ብለዋል፡፡

ከአሥር ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት የአሜሪካ ሜዲካል ማዕከል፣ ሰማሪታን የቀዶ ሕክምና ማዕከል፣ አክሶል የስትሮክና ስፓይን ማዕከል ጨምሮ የጤና ዘርፉን ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት የሚሠሩ ተቋማት መሆናቸው አከዛ (ዶ/ር) አስረድተዋል።

በዓለም ካለው የስትሮክ መጠን ውስጥ ሁለት ሦስተኛው የሚገኘው በታዳጊ አገሮች መሆኑን፣ አምራች የዕድሜ ክልልን እያጠቃ እንደሚገኝ የገለጹት የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወንድወሰን (ዶ/ር)፣ በሽታው በኢትዮጵያ መስፋፋቱ ለማዕከሉ መመሥረት በምክንያትነት አቅርበዋል። 

ድንገተኛ ታሞ የመጣ ታማሚ ከአምቡላንስ በድንገተኛ ክፍል ተቀብሎ ዕርዳታ የሚሰጥበት፣ ታካሚው በተኛበት ክብደቱን የሚለካና ሌሎችም አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አልጋ ያላቸው ክፍሎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

‹‹ካት ላብ›› በተሰኘ መሣሪያ የስትሮክ ሕመሙን ከመለየት እስከ ማከም የሚቻልበት አገልግሎት የሚያገኙበትና ታካሚዎች በማገገሚያ ክፍል የተለያዩ የፊዝዮቴራፒ አገልግሎት የሚሰጥበት ማዕከል እንደሆነም አክለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...