Saturday, April 20, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች የመገበያያ ዋጋ ጣሪያ ተነሳ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች በየሳምንቱ የዋጋ ማነፃፀሪያ ጣሪያ እየተዘጋጀላቸው ሲካሄድ የነበረው ግብይት እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉን፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጥራጥሬና የቅባት እሀሎችን የማነፃፀሪያ የዋጋ ገደብ በማስቀመጥ እስካሁን የነበረው አሠራር በግብይት ሥርዓቱ ውስጥ የራሱ በጎ ተፅዕኖ የነበረው ቢሆንም፣ አሁን ግን ይህንን አሠራር ላልተወሰነ ጊዜ ማስቀረት አስፈላጊ በመሆኑ ያለ ምንም የዋጋ ገደብ ግብይቱ እንዲፈጸም ሚኒስቴሩ ወስኗል፡፡

ይህንን ውሳኔ በተመለከተ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጣው ደብዳቤ፣ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች የወጪ ንግድ የመስከረም 2015 ዓ.ም. ክንውን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመቀነሱ፣ ላልተወሰነ ጊዜ የዋጋ ጣሪያ ገደቡ የተነሳ መሆኑን ይገልጻል፡፡

በውሳኔው መሠረት በጥራጥሬና በቅባት እህሎች የወጪ ንግድ የዋጋ ማነፃፀሪያ ገደብ ላልተወሰነ ጊዜ የተነሳ መሆኑን በማወቅ፣ ግብይቱን የሚያስፈጽመው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ተፈጻሚ እንዲያደርግ የተገለጸለት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትዕዛዝ ከመውጣቱ ቀደም ብሎ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ለውጭ ገበያ ሲቀርቡ ግብይታቸው እንዲፈጸም የሚደረገው፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በየሳምንቱ የግብይት መፈጸሚያ የዋጋ ጣሪያ እያወጣ እንደነበር ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች