የሒሳብ መምህር ክፍል ውስጥ ሲያስተምሩ ‹‹የሜዳው ርዝመት 200 ሜትር ነው፡፡ የባቡሩ ፍጥነት 100 ኪሎ ሜትር ነው፤ የእኔ ዕድሜ ስንት ነው?›› የጥያቄውን አደናጋሪነት የተመለከተው ጐበዝ ተማሪ እጁን አውጥቶ ‹‹50 ዓመትዎ ነው መምህር›› አለ፡፡ መልሱ ትክክል ነበርና መምህሩ ተደንቀው እንዴት አሰላኸው ቢሉት ‹‹ቀላል ነው መምህር ታላቅ ወንድሜ 25 ዓመቱ ነው፤ ሰው ሁሉ ግን ግማሽ እብድ ይለዋል›› አላቸው፡፡
– የወግ ገበታ(1990)