ልጅ: ‹‹አባዬ፤ በጣም አዋቂ ማን ነው፡- አባት ወይስ ልጅ?››
አባት: ‹‹አባት እንጂ››
ልጅ: ‹‹አይደለም፤ ልጅ ነው በጣም አዋቂ››
አባት: ‹‹እንዴት?››
ልጅ: ‹‹በእንፋሎት የሚሠራውን ሞተር ማን ፈለሰፈው?››
አባት: ‹‹ጀምስ ዋስ››
ልጅ: ‹‹ታዲያ ለምን አባቱ አልፈለሰፈውም?››
* * *
አንድ ወኔው በድንገት የከዳው ወታደር ወደኋላ ሲሸሽ አንድ መኮንን ያስቆመውና ‹‹ወዴት ነው እባክህ እንደዚህ የምትፈረጥጠው?›› ቢለው ‹‹ምን ያገባሃል? ይልቅስ ዘወር በል ከፊቴ›› ይለዋል፡፡ መኮንኑም ‹‹ከማን ጋር እንደምትነጋገር ታውቃለህ? እኔ ጄነራል እኮ ነኝ›› አለው፡፡ ወታደሩም ‹‹የፈጣሪ ያለህ ይህን ያህል ወደ ኋላ ሸሽቻለሁ ማለት ነው?›› ብሎ መለሰ ይባላል፡፡