የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሚካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱ ተገለፀ።
ከ3.1 ሚሊዮን በላይ መራጮች ይሳተፉበታል የሚል ቅድመ ግምት በተቀመጠበት የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ ህዝበ ውሳኔ 3,756 ጣቢያዎች፣18,885 የምርጫ አስፈፃሚዎች እንደሚያስፈልጉ ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ክንውኑን በተመለከተ ዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓም በኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል እያካሄደ ባለው የውይይት መድረክ ላይ አስታውቋል።
ለህዝበ ውሳኔ ማስፈፀሚያ የሚውል 541.2 ሚሊዮን ብር በጀት ጥያቄ ለመንግስት ማቅረቡን ቦርዱ ገልጿል::