Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከቀረጥ ነፃ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን የሚመለከት መረጃ ተጣርቶ ለገንዘብ ሚኒስቴር ቀረበ

ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን የሚመለከት መረጃ ተጣርቶ ለገንዘብ ሚኒስቴር ቀረበ

ቀን:

የገንዘብ ሚኒስቴር ባስጠናው ጥናት መሠረት ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ለተፈለገው ዓላማ እየዋሉ አለመሆናቸው በመረጋገጡና እሱንም ተከትሎ የወጣውን ደንብ ተግባር ላይ ለማዋል፣ ደንቡ ከመውጣቱ በፊት ተጀምረው የነበሩትን፣ ከቀረጥ ነፃ ለማስመጣት በሒደት ላይ የሚገኙ የተወሰኑ ድርጅቶችን የፒክ አፕና የስቴሽን ዋገን ተሽከርካሪዎችን መረጃ፣ አጣርቶ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለገንዘብ ሚኒስቴር መላኩ ታወቀ፡፡

ሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር 517/2014 አንቀጽ 13 መሠረት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ሊፈቅድ የሚችለው ከፒክ አፕና ከስቴሽን ዋገን ውጪ ያሉ ተሽከርካሪዎች እንደሆነ ተደንግጓል፡፡

ይህ ደንብ ከመውጣቱ በፊት ሁለቱን ዓይነት ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት በሒደት ላይ የሚገኙ ባለሀብቶች ቅሬታ ማቅረባቸውን፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በደብዳቤ መግለጹ ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የገንዘብ ሚኒስቴር መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚመለከታቸው አካላት በላከው ደብዳቤ፣ ደንቡ ከመውጣቱ በፊት የፒክ አፕና የስቴሽን ዋገን ተሽከርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ የማስገባት ሒደት ላይ የነበሩ ባለሀብቶች ክንውን ተጣርቶ እስከ መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ እንዲያሳውቁ ጠይቆ ነበር፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ይመለከታቸዋል ብሎ የጠቀሳቸው የመንግሥት አካላት የማዕድን ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የክልል ኢንቨስትመንትና ማዕድን ቢሮዎች፣ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሮች ኢንቨስትመንትና የማዕድን ቢሮዎች ናቸው፡፡

በተጨማሪም ሕግ ሲቀየር በባለሀብቶች ላይ ያልተጠበቀ ወጪና ጫና እንዳይፈጥር፣ ደንቡ ከመውጣቱ በፊት በሒደት ላይ የሚገኙ የቀረጥ ነፃ ማመልከቻዎችን ማስተናገድ ተገቢ መሆኑን ደብዳቤው ጠቅሷል፡፡

ለዚህም ደንቡ ታትሞ ሥራ ላይ ከዋለበት ከሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. በፊት ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ማቅረባቸውን በማስረጃ እንዲረጋገጥ፣ ተሽከርካሪዎቹ ከተጠቀሰው ቀን በፊት ተገዝተው የተጓጓዙ መሆኑን በማስረጃ እንዲረጋገጥ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጠይቋል፡፡

መረጃውን የማጣራት ተግባር ካከናወኑ ተቋማት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተወሰኑ ድርጅቶችን መረጃ በማጣራት ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መላኩን፣ በኮሚሽኑ የቀረጥ ነፃ አገልግሎት ዲቪዥን ዳይሬክተር አቶ ውበቱ መሰለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

‹‹ገንዘብ ሚኒስቴር የድርጅቶቹን መረጃ እንዲላክ በጠየቀው መሠረት ልከናል፡፡ መረጃው ተጣርቶ የተላከው ግን የሽግግር ጊዜ ይሰጠን ብለው ጥያቄ ያቀረቡት ብቻ ናቸው፡፡ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ቅሬታቸውን ያቀረቡ ድርጅቶችን አላስተናገድንም፤›› ሲሉ አቶ ውበቱ ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከቀረጥ ነፃ እንዲፈቀድ መረጃዎችን የማጣራት ሥራ ብቻ እንደሚያከናውን የገለጹት አቶ ውበቱ፣ የቀረጥ ነፃ ፈቃድ መስጠት እንደማይችልና ባለሀብቶቹ ፈቃድ ማግኘት የሚችሉት ከገንዘብ ሚኒስቴር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ደንቡ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ በኋላ በርካታ ቅሬታ የሚያቀርቡ ባለሀብቶችን በተመለከተ፣ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር የተለያዩ ንግግሮችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር የተለያዩ መረጃዎችን ሲለዋወጥ የቆየው ኮሚሽኑ፣ በላካቸው የድርጅቶቹ መረጃ መሠረት ውሳኔ የሚሰጠው የገንዘብ ሚኒስቴር መሆኑን አቶ ውበቱ ተናግረዋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢንቨስትመንት አዋጅ 1180/2020 አንቀጽ 17 እና በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2014 አንቀጽ 129 (6) መሠረት፣ ‹‹የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ›› አውጥቷል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ 517/2014 አንቀጽ 13 ለኢንቨስትመንት ዓላማ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው የሚገቡበት ሁኔታ፣ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ዓይነትና ባህሪ መሠረት በማድረግ ገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያ እንደሚወሰን ያስታውቃል፡፡ ሚኒስቴሩ በአንቀጽ 13 መሠረት ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ሊፈቅድ የሚችለው፣ ከፒክ አፕና ከስቴሽን ዋገን ውጪ ያሉ ተሽከርካሪዎችን መሆኑን ያክላል፡፡

ለኢንቨስትመንት ዓላማ ለሚውሉ ፒክ አፕና ስቴሽን ዋገን ተሽከርካሪዎች ፈቃድ ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ባስጠናው ጥናት መሠረት ከቀረጥ ነፃ የሚገቡት ተሽከርካሪዎች ለተፈለገው ዓላማ እየዋሉ ባለመሆኑ ዕድሉ መከልከሉን አቶ ውበቱ አስረድተዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር ምን ዓይነት ውሳኔዎች እንደተላለፉ ለሚመለከታቸው ኃላፊዎች የስልክና የጽሑፍ መልዕክት በመላክ ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...