Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናአይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የ2023 ምጣኔ ሀብት ትንበያ ወደ 5.3 በመቶ ዝቅ አደረገ

አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የ2023 ምጣኔ ሀብት ትንበያ ወደ 5.3 በመቶ ዝቅ አደረገ

ቀን:

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እ.ኤ.አ. የ2023 የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት 5.7 በመቶ እንደሚያድግ ተንብዮ የነበረ ቢሆንም፣ አዲስ ባወጣው የዓለም ምጣኔ ሀብት ዳሰሳ ሪፖርት ትንበያ በ0.4 ቀንሶ 5.3 በመቶ አደረገ፡፡  

ተቋሙ ሚያዝያ 2014 ዓ.ም. አውጥቶት በነበረው ሪፖርት የኢትዮጵያን እ.ኤ.አ. የ2023 የምጣኔ ዕድገት ትንበያ ቀንሶ ያስቀመጠው ትናንት ሰኞ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው አዲስ ሪፖርት ነው፡፡

አይኤምኤፍ በአዲሱ ሪፖርቱ ለኢትዮጵያ ያስቀመጠው ትንበያ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች በ2023 ያድጋሉ ብሎ ካስቀመጠው ትንበያ ጋር እኩል ነው፡፡ በሚያዝያ ወር 2014 ዓ.ም. ላይ አስቀምጦት የነበረው ትንበያ ግን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች ካስቀመጠው 5.6 በመቶ ዕድገት የሚበልጥ ነበር፡፡

- Advertisement -

ትናንት የወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ትንበያው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተብለው ከተዘረዘሩት ሰባት አገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ ጋር ሲነፃፀር፣ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የሚችል ነው፡፡ ከታዳጊ አገሮች ከፍተኛውን ዕድገት እንደሚኖራት የተተነበየላት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ስትሆን፣ የተተነበየው ዕድገት 6.7 በመቶ ነው፡፡

አይኤምኤፍ አሥራ አንደኛ ወሩ ላይ በደረሰው እ.ኤ.አ. 2022 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 3.8 በመቶ እንደሚያድግ ትንበያውንም አስቀምጧል፡፡ ተቋሙ ከአምስት ዓመታት በኋላ ስለሚኖረው የምጣኔ ሀብት ዕድገት ባስቀመጠው ትንበያ እ.ኤ.አ. በ2027 የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በሰባት በመቶ ያድጋል ብሏል፡፡ አይኤምኤፍ ስለ2022 እና 2027 አሁን ያስቀመጠው ትንበያ በሚያዝያ ወር 2014 ዓ.ም. ላይ አውጥቶት ከነበረው ትንበያ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የተጠናቀቀውን የ2014 በጀት ዓመት ሲጀምር፣ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት በ8.7 በመቶ ያድጋል የሚል ግምቱን አስቀምጦ የነበረ ቢሆንም፣ በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ይኼ እንደማይሳካ አስታውቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. የ2015 አጠቃላይ በጀትን ሲያቀርቡ፣ የ2014 በጀት ዓመት ዕድገት ከሰባት በመቶ የዘለለ እንደማይሆን ተናግረው ነበር፡፡

አይኤምኤፍ በአዲሱ ሪፖርቱ ለኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለት ትንበያውን ያስቀመጠ ሲሆን፣ እየተጠናቀቀ ባለው 2022 ጉድለቱ የጥቅል አገራዊ ምርቱን 4.3 በመቶ እንደሚሆን አስቀምጧል፡፡ በአዲሱ ሪፖርት ለ2022 የተቀመጠው ትንበያ በሚያዝያ ወር 2014 ዓ.ም. የንግድ ሚዛኑ ጉድለት 4.5 በመቶ ይሆናል ብሎ ካስቀመጠው በ0.2 በመቶ የቀነሰ ነው፡፡

እ.ኤ.አ. ለ2023 የተቀመጠው 4.4 በመቶ ትንበያ፣ በሚያዝያ ወር ላይ ወጥቶ ከነበረው ጋር ለውጥ የለውም፡፡

የተቋሙ ሪፖርት የሸቀጦች ዋጋ ንረትን በተመለከተ ሚያዝያ ላይ አስቀምጦት የነበረውን ትንበያ ዝቅ አድርጎ፣ ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት መረጃ ጋር ተቀራራቢነት ያለው ቁጥር አስቀምጧል፡፡

አይኤምኤፍ ሚያዝያ ላይ እ.ኤ.አ. የ2022 የሸቀጦች ዋጋ ንረት 34.5 በመቶ እንደሚሆን አስቀምጦ የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ ሪፖርት ወደ 33.6 በመቶ አውርዶታል፡፡ ይህ ቁጥር የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ከሐምሌ 2013 እስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም. የነበረውን ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት አስመልክቶ ካወጣው 33.7 በመቶ የሚል ቁጥር ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡

ተቋሙ ሚያዝያ ላይ 30.5 ይደርሳል በሚል ተንብዮት የነበረውን የዋጋ ንረትም እንዲሁ ወደ 28.6 በመቶ አውርዶታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...