Sunday, January 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትባለሁለተኛው ደረጃ የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን በቺካጎ ማራቶን

ባለሁለተኛው ደረጃ የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን በቺካጎ ማራቶን

ቀን:

በተለያዩ የዓለም አገሮች እየተከናወኑ የሚገኙት የጎዳና እንዲሁም የማራቶን ውድድሮች አዳዲስ ክስተቶችን ማስተናገዳቸውን ቀጥለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ዓመታት የሚፈጀው የማራቶን ክብረ ወሰን፣ አሁን በቀናት ልዩነት ውስጥ ሰዓታት እየተሻሻሉና ክብር ወሰኖች እየተሰበሩ ይገኛል፡፡

ከዚያም ባሻገር በወንዶች ብቻ ሲሻሻል የሚስተዋለው የርቀቱ ሰዓት በሴቶቹም እየተሻሻለ የሁለቱ ፆታ ሰዓት እየተቀራረበ መጥቷል፡፡ እሑድ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በቺካጎ በተደረገ የማራቶን ውድድር ኬንያዊቷ ሩት ቼፕንጌቲች በታሪክ ሁለተኛውን ዓለም ፈጣን የሴቶች ክብረ ወሰን መጨበጥ ችላለች፡፡

አትሌቷ በ2፡14፡18 የቺካጎ ሻምፒዮን በመሆን የቻለች ሲሆን፣ ከዓለም ክብረ ወሰን በ14 ሰከንድ ብቻ ዘግይታ ገብታለች፡፡

‹‹የዓለም ክብረ ወሰን መስበር እፈልግ ነበር፡፡ ሆኖም በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ግን አያመልጠኝም፤›› ስትል ቼፕንጌቲች ከውድድሩ በኋላ አስተያየቷን ለጋዜጠኞች ሰንዝራለች፡፡

ከዚህ ቀደም በ42 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እ.ኤ.አ. በ2019 በአገሯ ልጅ ብሪጊድ ኮስጌ 2፡14፡04 በሆነ ጊዜ የዓለም ክብረ ወሰን መስበሯ ይታወሳል፡፡ ሌላዋ አሜሪካዊቷ ሲሰን በ2፡18፡29 ሁለተኛ በማጠናቀቅ የአገሯን ክብረ ወሰን መጨበጥ ችላለች፡፡

አትሌቷ ባለፈው ጥር ወር በሂዩስተን በተከናወነው የማራቶን ውድድር ላይ በአገሯ ልጅ በኬይራ ዲአማቶ ተይዞ የነበረውን 2፡19፡12 ሰዓት ነበር ማሻሻል የቻለችው፡፡ የ30 ዓመቷ ሲሰን ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ካቋረጠች በኋላ የመጀመሪያውን ማራቶን ሮጣለች።

‹‹በእርግጥ በሁሉም ጊዜ ውስጥ ምን ያህል ፈጣን እንደሆንኩ አላውቅም ነበር ። ከአቅሜ በላይ እንዳልሄድና ስለጊዜ እንዳላስብ መመርያ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ስለዚህ በምን ያህል ፍጥነት እንደምሮጥ ምንም ፍንጭ አልነበረኝም፤›› በማለት ስለውድድሩ አስረድታለች፡፡

ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋ 2፡21፡41 አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ በወንዶች ቤንሰን ኪፕሩቶ 2፡04፡24 በሆነ ጊዜ አሸንፏል፡፡ ኬንያዊው ቤንሰን ባለፈው ዓመት በቦስተን ካስመዘገበው ድል ማግሥት ሌላውን ታላቅ የማራቶን ሻምፒዮን መሆን ችሏል፡፡

ኢትዮጵያዊው እሼቱ ቱራ 2፡04፡49 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሽፈራው ታምሩ 2፡07፡53 በሆነ ሰዓት አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

አሜሪካዊው ኮነር ማንትዝ ለመጀመርያ ጊዜ ባደረገው የማራቶን ውድድር በ2፡08፡16 በመግባት ሰባተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ በታሪክ ሰባተኛው ፈጣን የአሜሪካ ሰዓት ሆኖ መመዝገቡ ሌላው የውድድሩ ክስተት ነበር፡፡

በቀናት ልዩነት እየተሻሻለ የመጣው የማራቶን ውድድር ኬንያዊቷ ኮሲጌ ባለፈው መጋቢት በተደረገው የቶኪዮ ማራቶን 2፡16፡02 በሆነ ሰዓት ስታሸንፍ፣ ኢትዮጵያዊቷ ትዕግሥት አሰፋ ባለፈው መስከረም ወር ላይ በተደረገው የበርሊን ማራቶን በ2፡15፡37 አሸንፋለች።

ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ያለም ዘርፍ የኋላው በሀምቡርግ ባደረገችው የመጀመሪያዋ ማራቶን ተሳትፎ 2፡23፡17 እንዲሁም ከሳምንት በፊት በለንደን ባደረገቸው ሁለተኛ የማራቶን ተሳትፎዋ 2፡17፡26 በሆነ ጊዜ በማራቶን ማሸነፏ ይታወሳል፡፡

 እነዚህ ሁሉ ሰዓቶች የምንጊዜም 12 ምርጥ የማራቶን ሰዓት ውስጥ ይመደባሉ፡፡ የፊታችን እሑድ በአምስተርዳም በሚከናወነው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አልማዝ አያና (የ2016 የኦሎምፒክ የ10 ሺሕ ሜትር ሻምፒዮና) እና ገንዘቤ ዲባባ (የ1,500 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት) ለመጀመርያ ጊዜ የማራቶን ውድድር ያደርጋሉ።

 ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ (የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ የ5,000 ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ) በኒው ዮርክ ከተማ የምታደርገው የማራቶን ውድድርም ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...