Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየጥበብ ባለሙያዎችን ያግዛል የተባለው የመገበያያ ዓውድ ይፋ ሆነ

የጥበብ ባለሙያዎችን ያግዛል የተባለው የመገበያያ ዓውድ ይፋ ሆነ

ቀን:

የጥበብ ሥራዎችን ያግዛል የተባለው በክፍያና በማስታወቂያ አማራጮች መከታተል የሚያስችል አዲስ መተግበሪያ ወደ ሥራ መግባቱን ‹‹ቱ ኤፍ ካፒታል›› አስታወቀ፡፡

መተግበሪያው የጥበብ አፍቃሪያን፣ ጥበባዊ ሥራዎችን ካለ ክፍያ ከማስታወቂያ ጋርና በክፍያ ካለ ማስታወቂያ መከታተል የሚያስችላቸው መሆኑን መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በተደረገው ስምምነት ላይ ተገልጿል።

የቱ ኤፍ ካፒታል የሰዋስው የሙዚቃ ክፍል ኃላፊ አቶ ሀብቱ ነጋሽ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የሥነ ጥበብ ሰዎች ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የሚገጥማቸውን ችግርም የሚቀርፍ ነው። 

የዚህ የሥራ ሒደት የጥበብ ባለሙያዎች፣ ተስፈኛ ባለተሰጥዖ ወጣቶችንና የጥበብ አፍቃሪያንን ሁሉ ተጠቃሚ  የሚሆኑበት ዓውድ መሆኑን ገልጸዋል።

አዳዲስ የሙዚቃ ተሰጥዖ ያላቸውን ልጆች መልምሎ በድምፅ የተሰጥዖ ውድድር ወደ ዘርፉ ለማስገባትና የሙዚቃ ኢንዱስትሪውን በአዳዲስ ድምፆች ለማጠናከር በዝግጅት ላይ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከሌሎች አገሮች ጋር ተወዳዳሪ  የሚሆንበት  ሥርዓት መዘርጋቱንና ሰፋ ያሉ ሥራዎች በመሥራት አኅጉርና ዓለም አቀፍ ዕውቅና  እንዲያገኙ  ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል።

በሰዋስው መልቲ ሚዲያ መተግበሪያ ላይ የአዳዲስ አልበም ሥራዎቻቸውን ለመልቀቅ ከ79 አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ጋር መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

በዚህም ከ1,000 በላይ ሙዚቀኞችን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖድካስቶችንና ሌሎች የኪነ ጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የሰዋስው መተግበሪያ ወደ ሥራ መግባት ኢትዮጵያ የያዘችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታና የግሉ ዘርፍ ተዋናይ እንዲሆን የተያዘውን ዕቅድ የሚደግፍ ነው።

የክፍያ ሥርዓቱም በቴሌ ብርና በእናት ባንክ አማካይነት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ መተግበሪያው ዓለም አቀፋዊ መሆኑ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግም ያስችላል ብለዋል፡፡ 

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸው፣ ከፍተኛ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ የተለየው የአይሲቲና የጥበብ ዘርፍ ተቀናጅቶ ወደ ሥራ መግባቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። 

‹‹በራይድ ቴክኖሎጂ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ለ46 ሺሕ ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥረናል፤›› ያሉት የራይድ ቴክኖሎጂ ባለቤትና የሰዋስው ቦርድ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ፣  ፈጠራ መር ኢኮኖሚን ለመገንባት በትኩረት እንሠራለን ብለዋል። 

የጥበብ ሰዎች ከሥራዎቻቸው የሚገባቸውን እንዲያገኙ በማድረግ ዘርፉ እንዲነቃቃ ያደርጋል ተብሏል። 

ከዚህ መተግበሪያ ጋር ለመሥራት አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን፣ የሙዚቃ አቀናባሪዎችና የግጥምና የዜማ ደራሲያንም  ከሰዋስው ጋር ለመሥራት ስምምነት አድርገዋል።

ስምምነት ካደረጉት መካከል ድምፃዊ ፀጋዬ እሸቱ እንደተናገረው፣ ስምምነቱ በዋናነት የድምፃውያንን ችግር የሚቀርፍና ከዚህ ቀደም የነበረውን ኋላቀር አሠራር የሚያስቀር በመሆኑ በሙዚቃ ሥራ ላይ የተሰማሩትን ሁሉ የሚጠቅም ነው፡፡

አዲስ አልበም ለማውጣት ስምምነት ያደረገው ድምፃዊ ግርማ ተፈራ በሰጠው አስተያየት፣ ስምምነቱ ለነባርና ወደ ሙዚቃ ዓለም ለሚገቡ አርቲስቶች ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ፣ አቀናባሪና ድምፃውያኑ ሁሉ የልፋታቸውን የሚያገኙበትና ሁሉንም በአንድ ላይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብሏል፡፡

የሙዚቃ መተግበሪያ ዓውድ፣ የሙዚቃ የገበያ ዕድል በማስፋት፣ በሥነ ጥበብ፣ በሙዚቃ ሥራዎች ላይ ተሳትፎ ያለው ሁሉ እንደ አበርክቶውና ድርሻው በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚሆንበት (ሮያሊቲ) ክፍያውን ዕውን የሚያደርግ፣ ፈጠራ መብት ባለቤትነትን የሚያስከብር መሆኑን ተቋሙ በመድረኩ ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...