Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት የሚፈልገው የአዕምሮ ጤና ሕክምና

ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት የሚፈልገው የአዕምሮ ጤና ሕክምና

ቀን:

የአዕምሮ ጤና እንደ ሌሎች የጤና ዘርፎች እኩል አስፈላጊነቱን አሳይቷል፡፡ በዚህም የተነሳ በዕቅድ ተይዞ እየተተገበረ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደ አገር ቀውሶችንና የአዕምሮ ጤና ችግር ቢያጋጥምም የአዕምሮ ጤና ችግርን በማሻሻል ረገድ ውጤታማ ሥራዎች እንደተከናወኑ የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

‹‹ዓለም አቀፋዊ ትኩረት የአዕምሮ ጤናና ደኅንነት ለሁሉም›› በሚል መሪ ቃል የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተከበረበት ሥነ ሥርዓት ላይ ሚኒስትሯ እንደገለጹት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ 310 ጤና ጣቢያዎች መለስተኛ የአዕምሮ ሕሙማን ጤና አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

በቀጣይም ለማኅበረሰቡ በአዕምሮ ጤና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መሥራትና ለአዕምሮ ጤና ችግር አምጪ ሁኔታዎችን መቅረፍና መከላከል ላይ፣ እንዲሁም በሰው ኃይል ግንባታና በጥናትና ምርምር ላይ እንደሚሠራ አክለዋል፡፡ ከአዕምሮ ሕመምና ተያያዥ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ በ952 የነፃ ጥሪ መስመር ነፃ የምክር አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻልም ነው የተናገሩት፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይህ መሪ ቃል የተመረጠበት ዋናው ዓላማ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በመላው ዓለም ከፍተኛ ሞትና የጤና ችግር ያስከተለ ሲሆን፣ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ አዕምሯዊና ሥነ ልቦናዊ ጤንነት ላይ ተፅዕኖ በማሳደሩ እንደሆነ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአዕምሮ ጤና እንደ ሌሎች የጤና ዘርፎች እኩል አስፈላጊነቱን ያሳየ ሲሆን፣ ወረርሽኙን ተከትሎ ባሉት ወራትና ዓመታት በተለይ የድባቴ፣ የከፍተኛ ጭንቀትና የሱስ ሕመም መጠን ሊጨምር እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት መጠቆሙን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ባለው ግጭት የተነሳ ዜጎቻችን በሥነ ልቦናዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች የተነሳ ለአዕምሮ ጤና መታወክ ተጋላጭ የሆኑበት ጊዜ በመሆኑ ያለውን ተፅዕኖ ከፍ ያደርገዋል፤›› ብለዋል፡፡

የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀንን የሚከበርበት ዋናው ዓላማ፣ የአዕምሮ ጤና ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር፣ በአዕምሮ ጤናና ደኅንነት ላይ የበለጠ ለመሥራትና ድጋፍ ለማሰባሰብ፣ የሚመለከተው አካል ለአዕምሮ ጤና ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው ለማስቻል ሲሆን፣ በተጨማሪም ከአዕምሮ ጤና ጋር የሚያያዘውን ሥር የሰደደ አድልኦና መገለል ለመቅረፍ በጋራ ለመሥራት ውይይት የሚደረግበት የጋራ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የአዕምሮ ጤና ስትራቴጂ ቀርጾ በመተግበር ላይ ሲሆን፣ በስትራቴጂውም ላይ ትኩረት የሚሰጥባቸው ሥራዎች በቂና ብቃት ያለው የሰው ሀብት ልማት ማፍራት፣ የአዕምሮ ጤና ላይ ግንዛብ መስጠትና አጋላጭ መንስዔዎችን መከላከል መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዳኦ ፈጆ ሆስፒታሉ በተመለከተ፣ በተኝቶ ሕክምናና በድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸው በሰብ ስፔሻሊስት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከተቋቋመ 80 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ አንጋፋ ሆስፒታል የአሁኑን ስያሜ ከማግኘቱ በፊት ‹‹ተክለሃይማኖትና አካባቢው ሆስፒታል›› ተብሎ ይጠራ የነበረ ሲሆን ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከሆስፒታሉ ጎን ከነበረው አማኑኤል ቤተክርስቲያን በመነሳት የአሁኑን ስያሜውን ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

እስከ 1960ዎቹ ድረስ ከህንድ፣ ከአርጀንቲና፣ ከእንግሊዝና ከቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ በተለያየ ጊዜ በበጎ አድራጎት ተግባር እየመጡ የሕክምና አገልግሎት በመስጠትና በማስተዳደርም ጭምር በሆስፒታሉ ትልቅ አሻራቸውን ያኖሩ ሐኪሞች እንደነበሩ መረጃዎች ያትታሉ፡፡

በ1970ዎቹ መጀመርያ ላይ የቀድሞ የዩጎዝላቪያ ተወላጅ የሆኑት ዶ/ር ማሪንኮ ፖቪቼቪች ለረዥም ጊዜ ሆስፒታሉን በዳይሬክተርነትና በሐኪምነት እንዳገለገሉ፣ በኚህ የሕክምና ዘመን የኤሌክትሪክ ንዝረት ሕክምና መጀመሩ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...