Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበጋምቢያ የጉንፋን ሽሮፕ ያስከተለው ሞትን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት የሰጠው ማስጠንቀቂያ

በጋምቢያ የጉንፋን ሽሮፕ ያስከተለው ሞትን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት የሰጠው ማስጠንቀቂያ

ቀን:

አራት ደረጃቸው ባልጠበቁ የጉንፋን ሽሮፖች ምክንያት በጋምቢያ በደርዘን የሚቆጠሩ ሕፃናት ማለፋቸውን ተከትሎ የዓለም የጤና ድርጅት ሰሞኑን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

ሽሮፖቹ የተመረቱት በህንድ በሚገኝ ማይደን ፋርማሲዩቲካልስ ሲሆን፣ የሽሮፖቹ መጠርያዎች ፕሮሜታዚን ኦራል ሶሉሽን  (Promethazine Oral Solution)፣ ኮፌክስማሊን ቤቢ ካፍ ሽሮፕ (Kofexmalin Baby Cough Syrup)፣ ማኮፍ ቤቢ ካፍ ሽሮፕ (Makoff Baby Cough Syrup) እና ማግሪፕ ኤን ኮልድ ሽሮፕ (Magrip N Cold Syrup) ናቸው፡፡

እነዚህን ሽሮፖች መጠቀም በሕፃናት ላይ እስከ ሞት የሚያደርስ አደጋ እንደሚፈጥር የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡

ድርጅቱ ደረጃቸውን ያልጠበቁ የሕፃናት መድኃኒቶች በሚል ባሠራጨው መረጃ በእያንዳንዳቸው የአራቱ ምርቶች ናሙናዎች ላይ በተደረገው የላቦራቶሪ ትንተና ተቀባይነት የሌላቸው ዲኤታይሊን ግላይኮልን እና ኤቲሊን ግላይኮልን ይዘዋል፡፡ መርዛማነትን ስለያዙም የሆድ ሕመምን፣ ማስታወክን፣ የኩላሊት ቁስለትን ከማስከተላቸውም በላይ ለሞት ይዳርጋሉ ብሏል፡፡

ህንድ በሽሮፑና በሟቾች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ ማስረጃን እንዲያጋራ የዓለም ጤና ድርጅትን የጠየቀች ሲሆን፣ ናሙናዎችን ግን በፌዴራል ላቦራቶሪ በኩል እየመረመረች መሆኑን መግለጿን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ማርጋሬት ሃሪስ ሪፖርቱ መቼ ለህንድ ጤና ሚኒስቴር  ሊያጋራ እንደሚችል ለሮይተርስ ጥያቄ በቀጥታ ምላሽ አልሰጡም።

የጋምቢያ መንግሥት የፓራሲታሞል ሽሮፕ ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም በምትኩ ክኒኖችን እንዲጠቀም ማሳሰቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አራቱ የሕፃናት ሽሮፕ ዓይነቶች የተሠራጩት በጋምቢያ ብቻ ነው ቢባልም መደበኛ ባልሆነ የገበያ ስንሰለት ወደ ተቀሩት ጎረቤት አገሮችም ሳይሠራጩ አይቀርም መባሉን ቢቢሲ በዘገባው አክሏል።

የሜይን ዳይሬክተር ናሬሽ ኩማር ጎያል ለሮይተርስ በስልክ እንደተናገሩት፣  የህንዱ ኩባንያ ስለሞቱት ሕፃናት የሰማው ባለፈው ሐሙስ መሆኑንና ዝርዝሮችን ለማግኘት እየሞከረ ነው።

 ‹‹በትክክል የተከሰተውን ሁሉ ለማወቅ እየሞከርን ነው፤›› ኩባንያው፣ በህንድ ውስጥ መድኃኒቶቹ እንደማይሸጡ ከመናገር ባለፈ የበለጠ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆነም።

 እ.ኤ.አ. በኅዳር 1990 ሥራውን የጀመረውና በተለያዩ ግዛቶች ሁለት የማምረቻ ፋብሪካዎች ያሉት ሜይን ሽሮፕን አምርቶ ወደ ጋምቢያ ብቻ እንደላከ የህንድ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኩባንያው በዓመት 2.2 ሚሊዮን የሽሮፕ ጠርሙሶች፣ 600 ሚሊዮን እንክብሎች፣ 18 ሚሊዮን መርፌዎች፣ 300,000 የቅባት ቱቦዎችና 1.2 ቢሊዮን ታብሌቶች የማምረት አቅም እንዳለውና  ምርቶቹን ወደ እስያ፣ አፍሪካና ላቲን አሜሪካ  እንደሚልክ ተዘግቧል፡፡  

የዓለም ጤና ድርጅት ስለ ሽሮፖቹ በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው፣ ለሰው ልጆች መርዛማ ንጥረ ነገር አላቸው ያላቸው ዲኤቲሊን ግላይኮል እና ኤቲሊን ግላይኮል ሲጠጡ  እስከሞት ሊያደርሱ ይችላሉ። የሚያስከትሉትም የሆድ ሕመም፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ ሽንት አለማሸናት፣ ራስ ምታት፣ የአዕምሮ ሁኔታ መቀየርና ለሕልፈት ሊዳርግ የሚችል የኩላሊት ቁስለትን ነው፡፡

ሁሉም የመድኃኒት ምርቶች ሕጋዊ ፈቃድ ለማግኘት የምርቶቹ ትክክለኛነትና አካላዊ ሁኔታ በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው፡፡ ማንም በሚጠራጠርበት ጊዜ ከጤና ባለሙያ ምክር መጠየቅ እንደሚገባም ይመክራል፡፡

ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶች በየአገሮቹ ከተገኙ የሚመለከታቸው የጤና ተቋማት ለዓለም ጤና ድርጅት ወዲያውኑ እንዲያሳውቁም አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...