Tuesday, April 16, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኞችን ሲጎበኙ ውለው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ድካም ተጫጭኗቸው ቢመለሱም ባለቤታቸው በነገር አላስቀምጥ ብለዋቸዋል]

 • ምነው የደከመህ ትመስላለህ?
 • በጣም ደክሞኛል። ፈተና የሚወስዱትን ተማሪዎችና የፈተና አሰጣጡን ስጎበኝ ነው የዋልኩት። 
 • የዘንደሮስ የተለየ ነው!
 • እንዴት?
 • ፈተና ይሰረቅ ይሆን ከሚል ወሬ ተማሪዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው ዋሉ ወደሚል ጭንቅ ነዋ የከተታችሁን።
 • ለትምህርት ጥራት ስንል የምንከፍለው ዋጋ ነው። በዚያ ላይ ከተማሪዎቹ ብዛት አንፃር ጉዳቱ አነስተኛ ነው። 
 • እንደ መንግሥት ሲታሰብ ሊሆን ይችላል። 
 • ምን ማለትሽ ነው? 
 • ወላጅ ቤተሰብ ግን ጉዳቱ ትንሽ አይሆንለትም ማለቴ ነው። 
 • እሱን እረዳለሁ ግን ምን ማድረግ ይቻላል። 
 • እንዴት አይቻልም?
 • ጥራቱ የወደቀ የትምህርት ሥርዓትና የፈተና ስርቆትን ተሸክመን መቀጠል ይሻላል ነው የምትይው? 
 • እንደዚያ አልወጣኝም!
 • እና ምንድነው የምትይው? 
 • የምለውማ ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ ነው። 
 • እንዴት? 
 • የፈተና ስርቆትን በማስቀረት የትምህርት ጥራትን ማሳካት አይቻልማ? 
 • ለምን አይቻልም? 
 • ጥራት የሌለው ትምህርት ሲከታተሉ የመጡ ተማሪዎችን እንዳይኮራረጁ ማድረግ እንዴት ብሎ የትምህርት ጥራትን ያመጣል? 
 • ቢያንስ ጥራት ያላቸው ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ አያደርግም? 
 • መቀጣጫ ናቸው አትለኝም!
 • ምኖቹ?
 • የዘንድሮ ተፈታኞቹ፡፡ 
 • የምን መቀጣጫ?
 • የስህተቶቻችሁ፡፡ 
 • እና ኩረጃና ስርቆት ይቀጥል ነው የምትይው? 
 • አይደለም፡፡
 • እና ምንድነው የምትይው?
 • መጀመሪያ ጥራት ላይ ሥሩ ነው የምለው። ቆይ እስኪ ልጠይቅህ?
 • እሺ? 
 • አብዛኞቹ ተፈታኞች ዝቅተኛ ውጤት ቢያመጡ ምን ልታደርጉ ነው? ሥራ አጥ? 
 • ለምን? 
 • ንገረኛ? 12ኛ የጨረሱ ሥራ አጦችን ፈጥራችሁ ምን ልታደርጉ ነው? 
 • እሱ ውጤቱ ከታየ በኋላ ወደፊት የሚወሰን ነው። 
 • ምን ልታደርጉ እንደምትችሉ መገመት የሚከብድ አይደለም።
 • ምን ልናደርግ እንችላለን? 
 • ዝቅ ማድረግ ነዋ። ሌላ ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ?
 • ምኑን?
 • ማለፊያውን፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፓለቲካ አማካሪያቸው ጋር በወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ላይ እየተነጋገሩ ነው]

 • የሰሜኑ ታጣቂ ኃይል ከዚህ በኋላ ከመደራደር ውጪ አቅምም ሆነ አማራጭ ያለው አይመስለኝም። አንተ ምን ታስባለህ?
 • እኔም እንደዚያ ነው የሚሰማኝ ግን…
 • ግን ምን?
 • የሰሜኑ ኃይል ብቻ አቅሙ ስለተዳከመ ነገሩ ያበቃል ማለት አይደለም። 
 • ሌላ ማን አለ? 
 • እስካሁን ድረስ ያቆዩት ምዕራባዊያን ናቸው። እነሱ ተስፋ አስካልቆረጡ አፈር ልሶም ቢሆን ሊነሳ ይችላል። 
 • አሁን እኮ ተንኮታኩቷል። እንዴት ብሎ ሊነሳ ይችላል? 
 • ሰሞኑን የጀመረው ሙከራ ከተሳካለት ሊነሳ ይችላል። 
 • ሰሞኑን ምን ሞከረ?
 • የውጊያ ግንባሩን ወደ አፋር ለማስፋት ጥረት እያደረገ ነው።
 • በዚያ በኩል ቢሄድ ምን ያገኛል? የጅቡቲ ኮሪደርን ለመዝጋት? 
 • አይመስለኝም።
 • እና ምን ሊያደርግ ይችላል?
 • የራሱን ታጣቂዎች አስርጎ ጅቡቲን በማጥቃት ኤርትራን መወንጀል። 
 • ራሱ ጥቃት ፈጽሞ?
 • አዎ። የመጨረሻ ጥረቱ እንደዚያ ነው የሚሆነው።
 • ጂቡቲ የምዕራባውያኑ የጦር መንደር እንደሆነች እያወቀ? 
 • በእነሱ ይሁንታ ጭምር ነው ሊያደርግ የሚችለው።
 • እንዴት? እነሱ ምን ይጠቀማሉ?
 • የጋራ ጠላታቸውን ለማጥመድና በእኛ ላይም የፈለጉትን ለመፈጸም ይረዳቸዋል። 
 • የጋራ ጠላታቸው?
 • አዎ። የቀይ ባህርን መስመርን ለመቆጣጠር የተደረገ ጥቃት አስመስለውና ጉዳዩን ዓለም አቀፍ የፀጥታ ሥጋት ብለው ጣልቃ ለመግባት ይጠቀሙበታል። 
 • የኤርትራ መንግሥት እጁ በሌለበት? 
 • አዎ። በተለያዩ አገሮች ያደራጇቸውን ታጣቂዎች አሰርገው የኤርትራ ጦር የፈጸመው ጥቃት የማስመሰል ዝግጅት አላቸው።
 • ግን ይሳካላቸዋል? 
 • በእኛ በኩል እንዲሁም በጂቡቲና በኤርትራ መካከል ጠንካራ ቅንጅት ከተደረገ አይሳካም። እንዲያውም የራሱ መጥፊያ ሊሆን ይችላል።
 • እንዴት? 
 • በጥንቃቄ እንቅስቃሴውን ማጋለጥ ከተቻለ በዙሪያው ያሉትን ምዕራባውያን የሚበትንና ድርጊቱን ዓለም አቀፍ የሚያደርግ ነው።
 • ዓለም አቀፍ ምን? 
 • ዓለም አቀፍ ሽብር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እየተከታተሉ አንዳንዴም በመገረም እየሳቁ አገኟቸው]

አንዴ? ምን አገኘሽ? ምን አገኘሽ ማለት? ለብቻሽ የሚያስቅሽ ማለቴ ነው? እ... ምን ላድርግ ብለህ ነው? ወዶ አይስቁ ሆኖብኝ ነው። እንዴት? ምንድነው ነገሩ? በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን እያዳመጥኩ ነዋ? አለቃ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር...