Tuesday, April 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከውጭ ይገቡ የነበሩ 38 ዓይነት ምርቶች እንዳይገቡ ዕግድ ተጣለ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 38 ከውጪ የሚገቡ ምርቶች ላይ ዕገዳ መጣሉን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ እንዳደረገው፣ ወደ አገር እንዳይገቡ ክልከላ ከተደረገባቸው 38 ምርቶች ውስጥ ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል፡፡

በዚህ ገደብ ውስጥ ከተካተቱት ሌሎች ምርቶች መካከል ከረሜላዎች፣ ብስኩቶች፣ የለስላሳ መጠጦች፣ ሳሙናዎች፣ ሽቶዎችና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

ከሞተር ነክ ምርቶች የቤት አውቶሞቢሎችና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ይህ ዕገዳ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን አይመለከትም፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ዕገዳ የሚቆየው ላልተወሰነ ጊዜ  ነው ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች