Wednesday, February 28, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ላይ የሚሠሩ ተቋማት የሚመክሩበት ሁነት ሊካሄድ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ላይ ሚና ያላቸው ተቋማት የሚመክሩበት፣ እንዲሁም የፈጠራና ቴክኖሎጂ ውጤቶቻቸውን ለዕይታ የሚቀርብበት ሁነት ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በዲጂታል ፋይናንስ ዙሪያ የሚሠሩ የመንግሥትና የግል የፋይናንስ ተቋማትን በማስተሳሰር ለውስን ዓላማ በተሰባሰበ የባለሙያዎች ስብስብ (ወርኪንግ ግሩፕ) የሚዘጋጀው ሁነት፣ በመጪው ዕረቡና ሐሙስ በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።

የባለሙያዎች ስብስቡ በተለይም እያደገ የመጣውን የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግና ተቋማት አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ለማድረግ እንደተቋቋመ የቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የባለሙያዎች ቡድኑ አባል አቶ ናኤል ኃይለማርያም ተናግረዋል።

በግንቦት ወር የተጠነሰሰው ስብስብ የመንግሥትና የግል የፋይናንስ ተቋማት በጋራ እንዲሠሩ ለማስቻል፣ የፖሊሲና ስትራቴጂ ሥራዎች ላይ የተሻለ አስተዋፅኦ ለማበርከትና የድጋፍና ሥልጠና ሥራዎችን ለመሥራት በማለም የተቋቋመ መሆኑ እንዲሁ ተገልጿል።

የግል ቢዝነስ ተቋማት ከመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት ጋር ተሳስረው እንዲሠሩና ከብሔራዊ ባንክ የሚወጡ ፖሊሲዎች ለግል የፋይናንስ ዘርፉ ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ለውስን ዓላማ የተሰባሰበው የባለሙያዎች ስብስብ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ክብረት ተናግረዋል።

አቶ ዮሴፍ አክለውም፣ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሀብቶች ስለዲጅታል ፋይናንስ ጠቀሜታ በቂ እውቀት እንዲኖራቸውና ተሳታፊ እንዲሆኑ የባለሙያዎች ስብስቡ ይደግፋልም ብለዋል።

በተጨማሪም የአቅም ግንባታ ሥራን በማጎልበት የሥራ ዕድል ለመፍጠር  የመንግሥትና የግል የፋይናንስ ተቋማት በመናበብ እንዲሠሩ አጋጣሚዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝም አቶ ዮሴፍ ገልጸዋል።

የዲጂታል ፋይናንስ ሰርቪስ ወርኪንግ ግሩፕ ከቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ጋር በመሆን 40 የፋይናንስ ተቋማትን ተሳታፊ የሚያደርግ ዓውደ ርዕይ በመጪው ረቡዕና ሐሙስ በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል እንደሚያሰናዳ ታውቋል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየውና 40 የፋይናንስ ተቋማትን ተሳታፊ እንደሚሆኑበት በሚጠበቀው ሁነት በዲጂታል ፋይናንስ ላይ የሚሠሩ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያሳዩበት፣ በተጨማሪም  በዲጂታል ፋይናንስ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት የሚደረግበት መሆኑ ተጠቅሷል። ሁነቱን የተባበሩት መንግሥታት የካፒታል ልማት ፈንድ (ዩኤንሲዲኤፍ) እንደሚደግፈው ተገልጿል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች